ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ቸር የሚለው ትምህርት ስላልገባኝ እንድታስረዱኝ ነው

ቸር የሚለው ትምህርት ስላልገባኝ እንድታስረዱኝ ነው፡ ክርስቶስ እኔ ቸር አደለሁም ሲል ምን ማለቱ ነው?
Quote:
የማርቆስ ወንጌል
10፥17 እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና። ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
10፥18 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።
Mar 2, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

+1 ድምጽ
ልብ በል ስለ ምን ቸር ትለኛለህ ይላል። ስለ ምን የሚለውን ኣሁንም ደጋግመህ ኣንብበው።ስለ ምን የሚለው የሚጠይቀው ምክንያቱን ነው።ኣሁንም ምስጢሩ ስል ምን በሚለው ሃረግ ውስጥ ነው።ራሱ መጽሃፉ አንደሚለው ቸር ኣንዱ እግዚኣብሄር ብቻ ነው።እዚህ ላይ ፈጣሪያችን ጌታችን ኣምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነው ከኛ የሚጠበቅ።መልሱም እኔስ እግዚኣብሄር ስለሆንሁ ቸር ተባልሁ ኣንተ ለምን ቸር ለመባል መጣህ ሲለው ነው። ምክንያቱም ቸር ለመባል እንደመጣ ኣስቀድሞ ጌታችን ያውቃልና።
ከኦርቶዶክሶች ጠይቄ ነው የጻፍሁት።
Mar 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የጌታ ጸጋ እና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
የማርቆስ ወንጌል10፥
17 እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና፦ ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
18 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም አለው።

አስተውል ክርስቶስ <<እኔ ቸር አይደለሁም>> አላለም። ነገር ግን <<ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም>> ነው ያለው። ይህም እውነት ነው። አሁን ጥያቄው << ያ አንዱ እግዚአብሄር እኔ መሆኔን አልተቀበልክም። ታድያ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ?>> የሚል ነው። እኔ ቸር መሆኔን ካወቅህ፣ ከአንዱም ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም እንደሌለ ካወቅህ ስለምን አታምነኝም? የሚል ነው።

የሉቃስ ወንጌል 18፡
18 ከአለቆችም አንዱ፦ ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
19 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።
20 ትእዛዛቱን ታውቃለህ፥ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህን እና እናትህን አክብር አለው።
21 እርሱም፦ ይህን ሁሉ ከሕፃንናቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለ (ሆኖም ለዘላለም ህይወት ገና ብቁ አይደለም)
22 ኢየሱስም ይህን ሰምቶ፦ አንዲት ገና ቀርታሃለች፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ (ይህም ብቁ አያደርግምና ስለዚህ)፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው (ኢየሱስን ማመንና መከተል ብቁ ያደርጋል)
23 እርሱ ግን ይህን ሰምቶ እጅግ ባለ ጠጋ ነበርና ብዙ አዘነ።
24 ኢየሱስም ብዙ እንዳዘነ አይቶ፦ ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት (የክርስቶስ መንግስት ማለት ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥5። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፥11።) መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል።
25 ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት (ወደ ክርስቶስ መንግስት) ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ሊገባ ይቀላል አለ።
26 የሰሙትም፦ እንግዲህ ማን ሊድን ይችላል? አሉ።
27 እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር (በክርስቶስ) ዘንድ ይቻላል አለ።
28 ጴጥሮስም፦ እነሆ፥ እኛ <<ሁሉን ትተን ተከተልንህ>> አለ።
29 እርሱም፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እግዚአብሔር (ስለ እኔ) መንግሥት ቤትን ወይም ወላጆችን ወይም ወንድሞችን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን የተወ፥ (ሁሉን ትቶ የተከተለኝ)
30 በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ፣ በሚመጣውም ዓለም የዘላለምን ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም አላቸው።

የዮሐንስ ወንጌል 6፡
47 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 3፡
16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

የማርቆስ ወንጌል 10፡
17 እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና፦ ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
18 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።
19 ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው።
20 እርሱም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው።
21 ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና፦ አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ <<ና፥ ተከተለኝ>> አለው። (ስለ ክርስቶስ ስም መነቀፍን እና መሰደድን ተሸክመህ ማለት ነው። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፥12። ወደ ዕብራውያን13፥13)
22 ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ።
23 ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን፦ ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል አላቸው።
24 ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ፦ ልጆች ሆይ፥ <<በገንዘብ ለሚታመኑ>> ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።
25 ባለ ጠጋ (በገንዘብ የሚታመን) ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል አላቸው።
26 እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው፦ እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል? ተባባሉ።
27 ኢየሱስም ተመለከታቸውና፦ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና አለ።
28 ጴጥሮስም፦ እነሆ፥ እኛ <<ሁሉን ትተን ተከተልንህ>> ይለው ጀመር።
29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ <<ስለ እኔና ስለ ወንጌል>> ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥ (ሁሉን ትቶ የተከተለኝ)
30 አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን፣ ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።

እንግዲህ ደማቁ እና ትልቁ መልዕክት ክርስቶስን እመኑ ክርስቶስን ተከተሉ በሀብታችሁ አትታመኑ በጽድቃችሁም (ትዕዛዛቱን ሁሉ ጠብቄአለሁ በማለት) አትታመኑ (ትንቢተ ኢሳይያስ 64፡6)፤ ኑና ክርስቶስን ተከተሉ፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት አለው የሚል ነው።
የዮሃንስ ወንጌል 20፡
31 ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።
Oct 4, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 4, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
እንዲሁም በሌላ ስፍራ ጌታ ኢየሱስ "ስለ ምን ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ትሉኛላችሁ?" ብሎ ሲጠይቃቸው እናያለን። ይሄውም "እኔ ጌታ እና አምላክ መሆኔን ከልባችሁ ሳታምኑ በአፋችሁ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ማለትን አታብዙ፤ እኔ ልባችሁን አያለሁ" ማለት ነው። ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በሌላ ስፍራ ራሱ የተናገረ ሲሆን መላው መጽሐፍ ቅዱስም ይህን ያረጋግጣል።

ስለዚህ ጌታ "ስለምን እንደዚያ ትለኛለህ?" ሲል እኔ እንደዚያ አይደለሁም ማለቱ ሳይሆን "ያልከው ትክክል ነው፤ ነገር ግን በእኔ ባለማመንህ ምክንያት ከእኔ ጋር ምንም እጣ ፈንታ የለህም" እያለ ነው።

የሉቃስ ወንጌል6
46 ስለ ምን፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ትሉኛላችሁ፥ የምለውንም አታደርጉም?
47 ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ፣ ቃሌንም ሰምቶ የሚያደርገው፥ ማንን እንዲመስል አሳያችኋለሁ።
48 ቤት ሲሠራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሠረተ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም።
49 (ቃሌን) ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በምድር ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።

ክርስቶስ እኔ ቸር አይደለሁም አላለም። እንዲሁም እኔ ጌታ አይደለሁም አላለም። እናንተ ፈጣሪያችን የምትሉት አብ እና እኔ አንድ ነን አለ እንጂ።

ጸጋው ይብዛልን። አሜን።
(G.G.A.A)
Jan 22, 2013 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...