በጌታ ስም ሰላም እንልሃለን
በዚህ የጥያቄና መልስ አምድ ተመዝግበው የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ሁሉ እርስ በርስ የግል መልእክት (private message) መጻጻፍ ይችላሉ። ይህን ለማድረግ በቅድሚያ login ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚያም በዚህ ገጽ በላይኛው ክፍል የሚገኘውን "ተሳታፊዎች" የሚለውን ሊንክ በመጫን ከተሳታፊዎች ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን ሰው በመጫንና በመምረጥ የተሳታፊውን profile መክፈት። ከዚያም "send private message" የሚለውን ሊንክ በመጫን መልእክት መጻፍ ይቻላል።
ምንም አይነት መልእክት መቀበል የማይፈልግ ሰው ደግሞ login ካደረገ በኋላ ከላይ በቀኝ በኩል ያለውን "አካውንቴ" የሚለውን ሊንክ በመጫን "Private messages" በሚለው በስተቀኝ ያለውን ሳጥን (check-box) አለመምረጥ ወይም uncheck ማድረግና በዚያው ገጽ ታች ላይ "Save Profile" የሚለውን button በመጫን ሴቭ ማድረግ ነው።
የጌታ ጸጋ ይብዛልህ!