ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜን!!!
"ኦሪት ዘፍጥረት 18፤20-21ን አብራሩልኝ...እግዚአብሔር አንድን ነገር መሆኑን ለማወቅ ወደ ቦታው መሄድ አለበት?"
መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ክፍል እንዳለው ሁላችን የምናውቀው እውነት ነው ይኸውም ብሉይ እና አዲስ ኪዳን ናቸው። ከዚህ ከፍ ብሎ አብራሩልኝ ተብሎ የተጠቀሰው ቃል መልሱንም ያካተተ ነው "...ወደ እኔ እንደ መጣች" ይላል። ታድያ ለምን መሄድ አስፈለገው የሚል ጥያቄ ይፈጠራል። በዚህ መንገዱ የሆነው ትልቅ ነገር አለ ይኸውም ከአብርሃም ጋር መነጋገሩ ነው። በዚህም እኛ የምልጃን ምስጥር እንማራለን። እግዚአብሔር መሄድ የነበረበት እግረ መንገዱን የአብርሃም ምልጃን ለመስማት ነው እላለሁ እንጂ ያልተፈጸመ ኃጢአታቸው ወደ እሱ ሊመጣ አችልም ነበር:፡
ከጥቂት ወራት በፊት የሞባይል ምስጥር ሲገለጥ ሰው ሁሉ ነው የደነገጠው ምክንያቱም እኛ ሳናውቅ ቁጥጥር ስር ነበረን። ታድያ ሰው የት እንዳለሁ በረቂቅ መንገድ ማወቅ ከቻለ በዚህ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለን አማኞችማ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያዎች የሆን ታድያ እንዴት የምናደርገውንና የምንናገረውን አያውቅም? ከጌታ መደበቅ አለመቻላችን ሲናገር ዳዊት ወደ ሲኦልም ብወርድም አንት በዚያ ነህ ይላል። እግዚአብሔር ባንዴ በሁሉ ቦታ የሚኖር አምላክ ነው።
ከዚህ ሁሉ የሚያዋጣን በፊሩ ተደፍተን ከልብ ንስሃ መግባት ብቻ ነው።
ጌታ ይባርካችሁ
ወንድማችሁ