* የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የዳግም ምፅአቱን ቀኒቱንና ሰዓቲቱን ማንም አያውቅም፡፡ማቴ 21፡36-42፣ ማር 13፡32፣ የሐዋ 1፡7
* የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የዳግም ምፅአቱን ቀንና ሰዓት ባናውቅም ጊዜው እንደተቃረበና ዘመኑ እንደደረሰ በዓለም ዙሪያ ከሚታዩት ምልክቶችና የትንቢት ፍፃሜዎች ለመረዳት ይቻላል አምልኮቶቹም ውስጥ
- የሐሰት ት/ት ከእውነት መራቅና ሃይማኖትን መካድ የሚያስቸንቅ ዘመን ልጆች ለወላጆቻቸው የማይታዘዙበትና የአመፅ ዘመን ይሆናል፡፡ 1ጢሞ 4፡1-2፣ ሉቃ 18፡8
- አሕዛብ የምድርን ብርና ወርቅ የሚያከማቹበት ጊዜ ይሆናል፡፡ ያዕ 5፡1-9
- ጦርነትና የጦርነት ወሬ ይሰማል ማቴ 24፡6-7፡ ኢዮኤል 2፡1ና 3፡10
- ረሃብና የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ሥፍራ ይሆናል፡፡ ማቴ 24፡7
- የጥበብና የተመራማሪዎች መብዛት ይሆናል፡፡ ዳን 12፡4
-የመብላት የመጠጣት የማግባት የመፍታት ዘመን ይሆናል፡፡ ማቴ 24፡36-39፣ ሉቃ 17፡26-32
ጌታ ይባርካችሁ!!!!!!