ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 25 April 2017
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

መፀለይም ሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ አቅቶኛል ምን ይሻለኛል?

በሰራሁት ሀጥያት ምክንያት ጌታ ይቅር የሚለኝ አልመስልሽ አለኝ አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል በጣም ብዙ የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ ሰውነቴ በሀሳብ ምክነያት ከሳ ገርጥቻለሁ፡፡ ውሥጤ መፅናናት አቅቶታል፡፡ እረ ገራ ገባኝ ምን ይሻለኛል? ስለ ወደፊቱ ኑሮዬ በጣም አስባለሁ
5 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ 1 ሪፖርት

1 መልስ

+3 ድምጾች
ኢየሱስ የደም ላብ ያላበው፣ ሰውነቱ በግርፋት የተተለተለው፣ እግሮቹ በሚስማር የተቸነከሩትና ደሙን ያፈሰሰው ለምን ይመስልሻል እህቴ? እንደ አንቺ ያለውን ሰው ኃጢአተኛ በንስሀ ለማጠብና ለማንጻት አይደለምን? አንቺን ይቅር የማይልሽ ከሆነማ ኢየሱስ በከንቱ ሞተ ማለት ነው? ትንሽ አስቢ እንጂ በእርግጥ ንስሐ ገብተሽ ከሆነና ከክፉ መንገድሽም ተመልሰሽ ከሆነ ጌታ ሁል ጊዜም ይቅር ይልሻል። የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻልና። የሚከስሽን የሰይጣንን ክስ እየሰማሽ በጨለማ አትቀመጪ። ብቻ ንስሐ መግባትሽንና መመለስሽን፣ ክፉ ሥራሽንም መተውሽን እርግጠኛ ሁኚ።
Quote:
1ኛ የዮሐንስ መልእክት
1፥7 ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል

የማርቆስ ወንጌል 2
16 ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ። ከቀራ ጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው? አሉ።
17 ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።

1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
1፥15 ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤

የዮሐንስ ራእይ 12
9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
11 እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት
፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
5 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ

የተዛመዱ ጥያቄዎች

1 መልስ
1 መልስ
4 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
2 መልሶች
2 መልሶች
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2017 by iyesus.com
Terms of use | Contact us