ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 9 July 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ይቅር የማይባል ኃጢያት አለ?

Aug 12, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ሰላም

መልሱ የኔ ወንድም

የማቴዎስ ወንጌል 12:31
ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።
በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ትልቅ መልህክት ተላልፎል እናሥተውል ወንድሞቼ
የዮሐንስ ራእይ 13:6
"እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።"
በዚህ ቃል ውሥጥ ካለማሥተዋል ሥህተት መንገድ ውስጥ እዳንወድቅ እንጠንቀቅ
ወደ ዕብራውያን 3:14
"የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤"

የጌታችን የኢሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
Aug 17, 2011 worku (150 ነጥቦች) የተመለሰ
Aug 17, 2011 worku ታርሟል
በተመሳሳይ ጉዳይ ከዚህ በፊት የተደረገውን ውይይት እዚህ ይመልከቱ።
ምላሹን አየሁት እንግዲህ ይቅር የማይባል ሀጢያት አለ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሌላ ጥያቄ ላይ የተመለሰውን (መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ) ለሚለው የተሰጠው መልስ ደግሞ ከዚህ የሚቃረን ሆነብኝ
አይቃረንም እኮ። ይህ መስደብ የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ Blasphemy የሚለው ቃል ነው። እናም ሰፋ ያለ ጉዳይ እንጂ እንዲሁ ቃል ብቻ ማለት አይደለም። ክርስቶስን እና መንፈሱን የሚቃወሙና በክፋት የሚያደርጉት ኃጢአት ነው እንጂ ማንም በጌታ ያለና ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚያምን የሚያደርገው ኃጢአት አይደለም። ስለዚህ በሌላ ክፍል ያለው የሚያስረዳው ምንነቱን ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ በጌታ የሚያምኑና መንፈሱም ያለባቸው ክርስቲያኖች ሰይጣን ይህንን ኃጢአት እንደፈጸሙ ሲከስሳቸው ይታያል። ይህ ግን ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ይህንን ኃጢአት ቢፈጽሙ ኖሮ አሁንም ጌታ አያጽናናቸውም፣ አይከተላቸውም መንፈሱም ከላያቸው ይሸሽ ነበር። ኢየሱስ ጌታ እንደሆነም አሁንም አያምኑንም ነበር። ስለዚህ በአማርኛው መሳደብ ተብሎ ብቻ ስለተተረጎመ የቃላት ንግግር ብቻ እንደሆነ አድርገን መውሰድ የለብንም።

ኢየሱስ ለምሳሌ ሽባውን ሰው "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" ሲለው ይህንን የሰሙ ጻፎች "ይህስ ይሳደባል" ነበር ያሉት። ማለትም እግዚአብሔርን ይሳደባል ወይም Blasphemy ነው ነበር ያሉት። ስለዚህ ይህ መንፈስ ቅዱስን የሰደበ የሚለው ቃል የሚያወራው ስለ Blasphemy ነው። ወይም ከጥላቻ የሆነ ስም ማጥፋት፣ ከክፋት የሆነ መቃወም ወዘተ ማለት ነው። በጌታ የሆነ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን በመጥላትና በክፉ ልብ ሊሳደብና ክፉ ሊናገር አይችልም።
በዚህ ዘመን አንዳንድ ፓስተሮቻንና አማኞች በስይኮሎጂና በልምምድ የሚያደርጉት "የፈውስ" ና "የልሳን" "አገልግሎት" በመንፈስ ቅዱስ(በጸጋው) እንደተደርገን አድርጎ ማታለል መንፈስ ቅዱስንና ጌታን በድፍረት መሳደብ አይደለምን? እንደነርሱ ያሉትንስ አይደለም አርነት ሳይወጡ አርነት እናወጣችዋለን የሚሉ የተባሉት።

የጌታ ሰላም ለሁሉም ይብዛ።
ገታ እየሱስ የሰደቡትን የወጉትን የሚሰርቱን አያውኩም እና ይከር በላችሀው ብለዋል መስደብ ማለት እኮ የ አምላካችን ልጅ አለመከበል ነው እሱም ቢሆን ነሰሃ የግባ ሰው ከ ሃተያት ነዛ ነው
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...