ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 23 May 2018
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በክርስቶስ በማመን የምንድነዉ ከስጋ ሞት ብቻ ነዉ ወይንስ ከዘላለም ሞት ጭምር ?

በክርስቶስ በማመን የምንድነዉ ከስጋ ሞት ብቻ ነዉ ወይንስ ከዘላለም ሞት ጭምር ?
ከዘላለም ሞት የዳን ከሆነ መንግስተ ሰማይ እንገባለን ማለት ነዉ ! ጥሩ መንግስተ ሰማያት ለመግባት በማመን ብቻ የሚገኝ ከሆነ የሚያምንበት ሁሉ መግባት አለበት! አይደለ? መግባት ካለበት ደግሞ በክርስቶስ አምላክነት እያመነ መልካም ስራ ብቻ ስለሌለዉ መንግስቱን አይወርስም የተባለለት ደግሞ አለ ! ያም በያዕ መልዕክት ም 2 - ቁ 19-20 ተገልፃል እምነቱ አማኝ ነኝ ከሚለዉ ሰዉ ጋራ አንድ ቢሆንም ከንቱ ሰዉ እንዳሰኘዉ መፀሀፍ ይነግረናል ያምናል የተባለለተ ሰይጣን እንኮን መልካም ስራ መስራት ስላልቻለ ማመኑ ብቻ መንግስተ ሰማያት ሊስገባዉ አልቻለም ስለዚህ
የኔ ጥያቄ 1 በክርስቶስ ሰናምን የምንድነዉ መዳን ከምንድን ነዉ?
2 “እስከመጨረሻዉ የሚጸና ይድናል” ሲል ስናምን ከዳንን! በሆላ ለ ሁለተኛ ጊዜ ጸንተን ስንቆይ የምንድነዉ መዳን አለ ማለት ነዉ? ካለስ ከምን?
3 “ያመነ የተጠመቀም ይድናል” ሲል ምን ማለቱ ነዉ? ደግሞ ሲጠመቅም ሌላ መዳን አለ?
4 “ካመንበት ጊኤ ይልቅ መዳናችን ወደኛ ቀረቦል” ሲልስ? ስናምን አልዳንም እንደዉም ወደኛ እየቀረበ ያለ መዳን አለ?
5 “የሚአድነንን ከሰማይ እንጠብቃለን”ም ይላል ምን ማለት ነዉ ?--- ፓዉሎስ
በሌላ በኩል ደግሞ እንዲ ይላል
1 “በበጎ ስራ በመጽናት መንግስቱን ትወርሱ ዘንድ አላችሁ”
2 “በእግዚአብሔር ፊት ህግን የሚያደርጉ ይፀድቃሉ”
3 “ሰዉ በእምነት ብቻ ሳይሆን በስራ እንዲፀድቅ ታያላችሁ”
4 ጌታ ለፍርድም ሲመጣ ብናይ . . . .እንዲህ አድርጋችሆልና መንግስቴን ዉረሱ ይላል እነጂ ሌላ አይልም
ለመልስ መስጠቱ እንዲረዳን ለአንዱ ለመረጣችሁት ጥያቄ ብቻ መልስ ሰጡኝ
ስለመዳን ስትጠቅሱ ከስጋ በሽታ መዳን ከሆነ ስለነፍስ ከሚጠቀሰዉ ጋራ እንዳትቀላቅሉ
ስለ ህግ ስናወራ በመፅሀፍ ቅዱሰ ከ 300 ህግጋት በላይ አሉ ከ 10ቱ ህግ ጋት ጋራ ይጋጭ እንደሆነ መጀመሪያ ያጣሩ
ለምሳሌ መገረዝ ህግ ነበረ መገረዝ በጥምቀት ተተክቶል መገረዝ አለመገረዝ አይጠቅምም እና ይህ ግንዛቤ የሌለዉ አንድ ሰዉ ገላትያን ጠቅሶ “ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በህግ ሥራ ስለማይፀድቅ “ የምትለዋን ብቻ እንደመልስ እንዳያቀርብልኝ ስል እለምናለሁ
አመሰግናለሁ
ግብዣ
“ መርምሩ መልካሙን ያዙ ” ለሚጠይቆችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋቻችሁ ሁኑ
መንፈሳዊዉን በመንፈሳዊ ነገር ለመረዳት ሞክሩ እንጂ በአለም እዉቀት ለማስረዳት እንዳትሞክሩ ቆላ 2፣2
"...እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችው? አላቸው " ማቴ 16፣15-16
"በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ፣ የእግዚአብሔርንም ምስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ::" ቆላ 2፣2
የሰነፎችን ምክር አትስማ እግዚአብሔር የአዋቂዎች አምላክ ነዉ አንዳነዶች መጽህፍ ቅዱስን ጠቅሰዉ አለማስተዋልን አለመመርመርን የሚመክሩ አሉ
Aug 19, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

4 መልሶች

0 ድምጾች
ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ ጥያቄዎች የተሰጡትን መልሶችና አስተያየቶች የሚከተሉትን ሊንኮች በመጫን እንድታነብብ እጋብዝሃለሁ፦
ጌታ ይባርክህ
Aug 19, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ሰላም ላንተ/ላንቺ የሁን
1)በክርስቶስ ማመን ምንድነው? ከስጋሞት ብቻ ነው ወይስ ከዘላለም ሞት? ለሚለው ትያቄ
ከስጋሞት የሚቀር የለም የምንድነው ከሁለተኛውን ከዘላለም ሞት ነው።

"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።" ዮሃ3፡16-18

2) የያቆብ2፡19-20 ላለው
እስቲ ያቆብ ለማን ይህን መልእክት እደጻፈ እንመልከት፦
"የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።" ያቆብ1፡1 እዘህ ላይ እንደምናይው የጻፈው በጌታ ለሆኑ እንጂ ጌታን ለማያውቁ አይደላም ታዲያ ያዕቆብ ምንእያለን ነው ያለው 2፡17 ብንጀምር እምነት ያልው ሰው ስራው ያስታውቃል እምነታችሁ ከእውቀት ያለፈ የሁን የመፋስ ፍሬ ይገኝባችሁ አለበለዝያ አማኞች አይደላችሁም እምነታችሁ ፍሬ ያለው የሁን ነው።
ጌታም ከያቆብ በፊት ይህን አዞአል
"ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።" ዮሀ14፡15
በጌታ አምኖ የሚኖር ወንድሙን ይወዳል ከፍቅር የለጠ ነገር የለም ። ፍቀር የህግ ፍጻሜ ነው።
3)"እስከ መጨረሻዉ የሚጸና ይድናል" ምን ማለት ነው?
በመከራ ሰአት ጌታውን የማይከድ፦
"ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤
ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።" ማቲ 14፡4-13 እንግዲህ በደንብ ላነበበ ነገሩ ግልጽ ነው።
4) "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" ምን ማለት ነው?
ሙሉ አርፍተ ነገሩ እናንብብ
"ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።" ማር16፡16
አዎ ያመነሰው ከክርስቶስ ጋር በሞቱ እና በትንሳኢው እተባበራለሁ ስል ይጠመቃል ያ የእምነታችን ምስክርነት ነው። ሳናምን መጠመቅ ዉሃ ውስጥ መዘፈቅ ነው ቃሉ እንደ ሚል ያላመነ ግን ይፈረድብታል።
5) " ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" ምን ማለት ነው?
ለዚህ ሙሉ ቃሉ እንመልከት
"ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" ሮሜ13፡11
እንቅልፍ የሚለው ቃል ትርጉም "መንፈሳዊ እንቅልፍ" ማለት ሲሆን የጌታ መምጫው ቀርቦአል አሁን የለበስነው ስጋ ተወግዶ የክብሩ የትንሳኢ ለኛ ለሆን ነውና የነቃችሁ ኑሁ
የጌታ መምጣት በደጅ ነው የህ ስጋ ተውግዶ የዘላለሙን እንልብሳለን።
ወገኖች ይህን ካልኩ ይበቃል
እንግዲይ በመስቀሉ ላይ የተከፈለው ዋጋ አልበቃ ካለ እናንት ፈረዱ
የሃጢያት ዋጋው ሞት ነው እኻን613 አስሩን መጠበቅ ላቃታቻው እስራኤልዊዎች ዋጋ ተከፈለ ለኛ ደግሞ ቃል ኪዳን እንኻን ለሌለን መዳን ሆነልን ህግ የተሰጠው ለ እስራኤል አንተ/አንች ኑ በጸጋው ዳኑ ስትባሉ እንቢ አሻፈርኝ ለ እስራእል የተስጠ ህግ እኔንም ይግዛኝ ካላቹ ስራችሁ ያውጣችሁ እኔና ቤቴ ግን በክርስቶስ ያለውን ደንነታችን ተቀብለን ኑ እናንተም ከዘላልም ሞት አምልጡ ዳኑ መዳን በክርስቶስ ነው እንላለን።

"ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።" ዮሃ10፡7-9
የዘላለም ጨለማ ሳይመጣ አምልጡ
"ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።" ዮሃ 8፡12


ወገኖቼ የመዳን ቀን ዛሬ ነው እና ለባችሁን ለጌታ ሰጡ።
Aug 21, 2011 YaelD (8,180 ነጥቦች) የተመለሰ
Nov 25, 2011 YaelD ታርሟል
0 ድምጾች
እንደምገምተዉ ጠያቂዉ መንፈሳዊ አና መላሹ እሚ ዳን የተግባባችሁ አትመስሉም አንደኛ ከከንቱ ጥላቻ እና ከከንቱ ፈቅር መለየት ያስፈልጋል ሁለተኛ በራሴ ወይም እስከዛሬ እዉነት መስሎኝ በተመላለስኩበት ትምህርት ወይም እዉቀት እግዚአብሔር የማይከብርበት ከሆነ ያለሁበትን ለመመርመር ከተቻለ ለመመለስ አላመነታም ሶስተኛ የሚፈርስ ትምህርት ይዜ መኖር የለብኝም ያ ትምህርቴን ያፈረሰዉ ትምህርት ለራሴ አድርጌዉ ልኖር ይገባኛል የሚል አቆም አለኝ
ወደ ሁለታችሁ ዉይይት ስሔድ ስጀምር እንዳልኩት ጠያቂዉ መንፈሳዊ - ስለ እምነት እና ስራ ከተናገረ በሽላ ሁለቱም ለየብቻቸዉ ማዳን እንደሚችሉ ብሎም እነዚህን ሁለቱን ትልልቅ ጉዳዮች ባሉበት ሁኔታ እንደሚፀድቁን ተናግረሐል ማመን እንዳለብን ተገንዝቤለሁ ነገር ግን ሁለቱም የማዳን ችሎታቸዉ ቢታወቅም ሁለቱን አጣምሮ በመኖር ለመንግስተ ሰማያት እንደሚአበቃ አይቻለሁ
ሁለተኛዉ መላሹ እሚ ዳን - ባስቀመጠዉ ሀሳብ ስነሳ ስራ የእምነታችን መገለጫ ወይም መታያ እንጂ ለመጽደቅ ሲበል ህግጋትን አልጠብቅም የሚል ይመስላል ማስረጃ ብታክልበት ደስ ይለኛል በነገራችን ላይ ሥራን የእምነት መገለጫ ብቻ እንጂ ዋጋ እንደማናገኝበት ማለትም መልካም ሥራ ከዘላለም ህይወት ጋራ ተነጻጽሮ መንግስቱን ሊያሰጠን እንደማይችል ያስመስላል ዋጋ ከሌለዉ ደግሞ (NGO)ነን ማለት ነዉ ?
ጠያቂዉ መንፈሳዊ - ክርስቶስ ያዳነን ማዳን ከአዳም ሐጥያት ብቻ ነዉ ወይ ? ያሰኛል ትምህርትህ ! ስለዚህ ዛሬ በአዳም ሐጥያት አልጠየቅም ለማለት ነዉ ok ከአዳም ሐጥያት ማዳኑ ለአንተ ወይም ለአዳም ልጆች ጥቅሙ ምኑ ላይ ነዉ? አሁንስ እለት እለት የምትሰራዉ በምን ይደመሰሳል ?ይሔን መልስልኝ እንደገና ያላመኑትም ሁሉ ከአዳም ሐጥያት ድነዋል ብለህ ታምናለህ?
Aug 22, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ሰላም ወገኔ ሰላምህ ይብዛ
በመጀመሪያ ጠያቂው ስም መንፈሳዊ ሳይ ሆን ስም-አልባ ነው።
ወደ ሃሳብህ ስንገባ
የኔ ሀሳብ ሳይ ሆን የ እ/ግ ቃል የሚለውን እይጠቀስሁ ነው መልሱን የስጠሁት።
"ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።" ሮሜ3፡23-24
እንገዲ ሁሉ ሲል እኛ ሁላችን አይደለም እን? በእ/ግዚ ፊት ስራችን የሚያጽድቀን ከሆነ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
"ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።"ሮሜ4፡24-25
"
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤"ሮሜ5፡8-10
"የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።" ሮሜ6፡23
ሁላችን ህግን ሁሉ በሙሉ መፈጸም ካልቻልን የአንዲታ ውሸት እንኻን ዋጋ ሞት ነው ያውም የዘላለም ሞት። "ጸጋ" ማለት ነጻ ስጦታ ነው በያጥያት ሆነን መየት የማይችል አምላክ ከሃጥያት መውጫውን አዘጋጀልን። መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው።
በትችል የጳውሎስን መልእክት ወደ ሮሜ ስዎች አንብብ መናልባት ሙሉን በታነብ ግልጽ የሆንልን የሆናል ። ሃሳብ ካልገባን ግን እባክህ ጠይቅ
ተባረክ
3 ታችሁም ያነሳቸሁት የተለያየ አመለካከት እና ትምህርት ነዉ ብራዘሮቼ ሁላችሁም እዉነት አላችሁ ያልገባችሁም ነገር አለ ከጥያቄዉ ስነሳ ከስጋ ሞት የሚቀር የለም ። ባይሆን ፤ ሞተን ከምንሞተዉ ሁለተኛ ሞት ከሆነ የምታወራዉ ሁለት አይነት መልስ ነዉ ያለዉ።
1ኛ ፦ሞት እየተባለ የሚጠራ የነበረዉ ሞትን ያመጣዉ የ አዳም ሀጥያት ነዉ ፥ ስለሆነም አለም ሁሉ ከ አዳም ሀጥያት ድኖል ።የ አዳም ሀጥያት ብቻዉን ሰዉን ሁሉ በበደለኛነት እያሳበበ የዘላለም ሞት ይጥል ነበረ አሁን ግን ማንም በዚህ በደል አይጠየቅም።
ሮሜ 5-12 ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤ ይልና ቁጥር 18 ላይ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።
በነገራቸን ላይ ከአዳም ሀጥያት አለሙን ሁሉ ነዉ ያዳነዉ! ስል የአዳም ዘር በሙሉ ማለትም ጨዋ ባሪያ ሀብታም ደሀ እስላሙም ጆሆቫዉም ሂንዱ ኦል እኛ ሀገር ያሉ ራቁታቸዉን የሚኖሩ ጭምር በአዳም ሀጥያት አይጠየቁም ነጸ ናቸዉ ማለትም ድነዋል ለዚህም ማስረጃዉ ሁሉም የሰዉ ዘር ሁሉ የ አዳም ልጆች ናቸዉ።
1ኛወደጢሞቴዎስ 1፥15 ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤
እርግጥ መዳናቸዉን እየነገርን ከአዳም ሐጥያት የተነሳ አሁን ኩነኔ የለባችሁም አሁን አምናችሁበት እንድትኖሩ ያስፈልጋል ብለን ልንነግራቸዉ ያስፈልጋል በልጁ እግዚአብሔርነት ባታምኑ እንደገና ሞትን ትሞተላችሁ እንላቸዋለን ። ባታምኑ ሀጥያት ስለሆነ፥ የሐጥያት ደሞዝ ያዉም ሁለተኛዉን ሞት ትሞታላችሁ ልንላቸዉ ይገባል ይሄ ብቻ አይደለም የክርስቶስን ህግ እየጠበቁ ካልኖሩ መጽደቅ ወይም መዳን እንደሌለ ልናዉቅ ይገባል የክርስቶስ ህግ 10 ቱ ናቸዉ ።
ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸዉ ዕብ 5-9 የምንታዘዘዉ ዋጋ ለማግኘት ነዉ እንጂ NGO አይደለንም ባልከዉ እስማማለዉ
2ኛዉ በክርስቶስ ሞት የዘለአለም ህይወት አለን የምንለዉ የአዳምን ምክንያት ሰላጠፋልን ብቻ ሳይሆን የ ህግ ትእዛዛት በእኛ በምናምንበት መፈጸም ሰለምንችል ነዉ ። አይኖ ትንሽ ይወሳሰባል 10 ቱን ህግ ያለ ምንም ሰህተት መፈጸም አንድንቸል ሀይልን ሰቶናል አንዱንም ሳናጎድል ። ብናጎድል እንኮን ያቺ ያጎደልናትን ሐጥያት ሀጥያትን ሊስወግድል ወደሚቸለዉ በመቅረብ ፥ ንሰሀ በመግባት፥ ቶሎ የሚከበንን ሐጥያት እያስወገድን ሙሉ ማለትም 10ንም ትእዛዝ ፈጽመን መንግሰቱ አንገባለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፥ 1 – 4 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።
0 ድምጾች
ሰላማችሁ የብዛ ወገኖችህ፡
let us see the difference between salvation and sanctification:-
salvation is a free gift that come from believing on the son of God that He took our sin away and pay the price on the cross. "የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።"1ዮሃ1፡7 sanctification is a process that goes on throughout our life. salvation comes 1st then sanctification, after we got saved with a help of Holy Spirit we start barring fruits of the spirit.
which are in gel5:22-24 "የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።"
those will help us to be sanctified ( በቅድስና ) ለመመላለስ እንጂ ወደ ገነት አያስገቡንም ። "እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።" 1ጲጥ1፡15-16 በክርስቶስ አምኛለሁ የሚል አንድ ሰው የነኝህ ፍሬ ዘሮች ሊኖረው ይገባል።
"ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።
ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።
አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።
ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤
በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።" 1ዮሃ2፡1-6
በሀገራችን ከክርስቶስ መወለድ በፊት የንበሩት እምንቶች ( የፈላሻ፣ የባእድ አምለኮ እና የመሳሰሉ ተቀላቅሎ ክርስትና በአገራችን ሲገባ ንጽህ የሆነውን የክርስቶስን ደም በቂ ነው እንደ ቃሉ መዳን በ እምነት ነው ቅድስና ደግሞ ቅዱስን አምላችን እንድን መስል ነው በማለት ፋንታ ክርስቶስ + ........ = ደህንነት በለው አስተማሩን። አሁን ግን እራሳችን የእግዚአብሄርን ቃል ስናነብ ለቃሉ በመታዘዝ ፋንታ የለም ከጥንት የመጣ ባህል ነው ይምፈልገው በለን ሲኦል እንወርዳለን። ለምን???????? ዋጋ ተክፍሎ ሳለ ለምን ቃሉን አንከተልም ? "እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" ሮሜ10፡17 የላለ እና ቃሉ መጸሀፍ ቅዱሱን አንብቡት ወገኖችህ።
ተባረኩ.።
Aug 25, 2011 YaelD (8,180 ነጥቦች) የተመለሰ
Aug 25, 2011 YaelD ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2018 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...