ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች » ኤፌሶን » ጥናት 18 (ኤፌሶን 5፣1-7) በፍቅር መመላለስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 20 October 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦“
(የዮሐንስ ራእይ 3:14)

rss

Today's verse

ጥናት 18 (ኤፌሶን 5፣1-7) በፍቅር መመላለስ

pdf version

ሀ)እግዚአብሔርን መከተል

 

ጳውሎስ ይህን ክፍል የሚጀምረው “እንግዲህ” ብሎ ነው:: ይህም ከላይ በኤፌ 4፣32 ላይ የጠቀሰውን ሃሳብ እየቀጠለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው:: በዚያ ክፍል ባለፈው ጥናታችን እንዳየነው፣ ልክ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳለን እኛም እርስ በርስ ይቅር እንድንባባል ጳውሎስ መክሮናል:: በዚህ ክፍልም በመቀጠል “እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ” ይለናል:: ማለትም ልክ ልጆች ታላቅ ወንድሞቻቸውን ወይም ወላጆቻቸውን እንደሚከተሉ ወይም እንደሚኮርጁ ወይም የእነርሱን መልካም አርአያ እንደሚከተሉና imitate እንደሚያደርጉ እናንተም እግዚአብሔርን አርአያችሁ አድርጉት ማለቱ ነው:: የሚወደዱ ልጆች ወላጆቻቸውን የሚያሳዝኑ ሳይሆኑ የወላጆቻቸውን መልካም አርአያ በመከተል ወላጆቻቸውን እያስደሰቱ በእነርሱ ፍቅር ስር ይኖራሉ:: በተቃራኒው ደግሞ ክፉ በማድረግ የወላጆቻቸውን ልብ እያሳዘኑ የሚኖሩም ልጆች አሉ:: ጳውሎስ የሚመክረን ግን እኛ በወላጆቻቸው እንደተወደዱ ልጆች ጌታን ደስ እያሰኘንና የእርሱን መልካም አርአያ እየተከተልን እንድንኖር ነው:: “አብ እንደወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፣ በፍቅሬ ኑሩ:: እኔ የአባቴን ትዕዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ::” ዮሐ 15፣9-10:: የተወደዱ ልጆች ሆኖ እግዚአብሔርን ደስ እያሰኙ በፍቅሩ ለመኖር የእርሱን ትዕዛዝ መጠበቅ ዋና ነገር እንደሆነ ጌታ አስተምሮአል::

 

ባለፈው ጥናታችን ላይ የእግዚአብሔርን የይቅርታ ባህርይ አርአያ እንድናደርግ የተመከርን ሲሆን፣ በዚህ በአሁኑ ጥናታችን ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሕይወታችን ምሳሌ እንድናደርግ እንመከራለን:: “ክርስቶስም ደግሞ እንደወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ” ቁ. 2:: በዚህ ክፍል “እንደወደዳችሁ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል agape/አጋፔ የሚለው የግሪክ ቃል ነው:: ይህም ነፍስን ሁሉ የሚያሰጥ ታላቅ ፍቅርን የሚያመለክት ነው:: የዚህን ቃል ትርጉም በይበልጥ ለመረዳት ጥናት 5ን ይመልከቱ:: መባ የሚለው ቃል offering; i.e. the act of offering, a bringing to; that which is offered, a gift, a present ማለት ነው፣ በአማርኛም ሰው ለአምላኩ የሚያቀርበው ማናቸውም ስጦታ ሁሉ መባ ይባላል:: መባው ለመስዋዕትም ሆነ ለሌላም ሊሆን ይችላል:: ክርስቶስ እንግዲህ ለእኛ ድነት ነፍሱን እንኳን ለመስዋዕት አቅርቦአል:: ይህም እጅግ ታላቅና ከመታወቅ የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ያሳያል:: “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም::” ዮሐ 15፣13:: ይህ ስለ እኛ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው መባ፣ ለእግዚአብሔር የመዓዛ ሽታ ያለው፣ እግዚአብሔር የተቀበለውና ደስ የተሰኘበት ነው:: መስዋዕት ወይም መባ ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኝምና ዘፍ 8፣20-21 ዘፍ 4፣4-5 ዘሌ 1፣9 ዘጸ 29፣18::

 

ስለዚህ ክርስቶስ ራሱን በፍቅር ስለ እኛ እንደሰጠና እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ፣ እንድሁ እኛም የክርስቶስን አርአያነት በመከተል፣ እርስ በርስ በፍቅር በመመላለስ እግዚአብሔርን ደስ እንድናሰኝ ነው የጳውሎስ ምክር:: “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት::” ዮሐ 15፣12:: በፍቅር እንድንመላለስ በመጽሐፍ ቅዱስ ተደጋግሞ እንመከራለን:: ፍቅር የእምነታችን እውነተኝነት መለኪያና የክርስቶስ መሆናችን መታወቂያ ነው ዮሐ 13፣34-35:: እርስ በርስ በፍቅር ሳይሆን በጥላቻ ከተመላለስን መንፈሳዊ ሕይወታችን፣ አገልግሎታችንና በጌታ ያለን ሩጫ ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው:: ያለ ፍቅር ሕይወታችንም ይሁን አገልግሎታችን የእግዚአብሔር ሚዛንን የማይደፋ ይልቁን በእግዚአብሔር ሚዛን ሲመዘን የሚቀልል ይሆናል 1ቆሮ 13፣1-3:: ወንድሙን የማይወድ ይባስ ብሎ የሚጠላ ሰው በጣም በአደገኛ መንገድ ላይ እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠነቅቃል “እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፣ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል:: ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፣ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ::” 1ዮሐ 3፣14-15::

 

ፍቅር ስሜት ብቻ ሳይሆን በተግባርም የሚገለጥና የሚታይም ነው:: “እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል:: ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፣ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ልጆቼ ሆይ፣ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ::” 1ዮሐ 3፣16-18::

 

ለ)ለቅዱሳን የማይገቡ ወይም ከቅዱሳን ጋር የማይሄዱ ነገሮች

 

ከፍቅርና እግዚአብሔርን ከማስደሰት ጋር በተያያዘ፣ በእግዚአብሔር የተወደዱና ጌታን ደስ የሚያሰኙ ቅዱሳን ሊለማመዱአቸው የማይገቡ አንዳንድ ኃጢአቶችን ጳውሎስ እንደሚከተለው ይጠቅሳል (ቅዱሳን የሚለውን ቃል በይበልጥ ለመረዳት ጥናት 1ን ይመልከቱ):-

 

·       ዝሙት ወይም fornication ቃሉ በግሪኩ porneia ሲሆን፣ ትርጉሙም illicit sexual itercourse in general ማለትም ማናቸውንም የተከለከለና ያልተፈቀደ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሁሉ የሚያጠቃልል ነው::

 

·       ርኩሰት የሚለው ቃል ደግሞ መንፈሳዊ ንጽሕና ማጣትንና መንፈሳዊ መቆሸሽን (uncleannes/ impurity) የሚያሳይ 

 

·       መመኘት ተብሎ በአማርኛ የተተረጎመው ቃል greediness, greedy desire to have more, coventousness, avarice ይህም ማለት ኃይለኛ የሆነ ገንዘብንና ቁሳዊ ነግሮች የማግኘት ስግብግብነትንና ምኞትን ወይም ሥስትን የሚያመለክት ነው:: እንዲያውም ይሄው ቃል በሉቃስ 12፣15 ላይ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ሁኔታ “መጎምዠት” ተብሎ ተተርጉሞአል::

 

·       የሚያሳፍር ነገር dishonor, baseness ማለትም ነውረኛ ወይም ወራዳ ነገር

 

·       የስንፍና ንግግር ወይም foolish or silly talking (without reason, sense or good judgement) ማለትም የስንፍና ወይም ያላዋቂ የሆነ ወይም ጥበብና ማስተዋል የጎደለው ንግግር:: እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን በመጽሐፍ ቅዱስ ስንፍና ወይም ሰነፍ ተብለው በአማርኛ የተተረጎሙት ክፍሎች ሁሉ የሚያወሩት ሥራ መሥራት የማይወድን ሰው የሚያመለክቱ ሳይሆኑ ጥበብና ማስተዋል የጎደለውን ሰው የሚያመለክቱ ናቸው:: ይሄው የግሪኩ ቃል በተለያዩ ክፍሎች ላይ በተለያየ ሁኔታ ተተርጉሞአል:: በሉቃ 11፣40 ላይ ደንቆሮ፣ በሉቃ 12፣20 እና በሮሜ 2፣20 ላይ ሰነፍ፣ በ1ቆሮ 15፣36 እና በ2ቆሮ 11፣16 ላይ ሞኝ:: ሁሉም ግን የማስተዋል ወይም የጥበብ ወይም የመረዳት ማነስን የሚያመለክቱ ናቸው:: ሥራ መሥራት የማይወድን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ታካች ብሎ ነው የሚጠራው ምሳ 6፣6-11::

 

·       ዋዛ የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉሙ pleasantry (ቀልደኛ፣ አስቂኝ), humor (ቀልድ), facetiousness (በሌላ ሰው ላይ እያሾፉ መቀለድ) ማለት ነው:: በዚህ ክፍል ይህ ቃል የተጠቀውሰው በመጥፎነቱ ነው:: ስለዚህም በዚህ ክፍል የዚህ ቃል ትርጉም scurrility (መጥፎና የሚጎዱ ቃላት ያሉት አነጋገር), ribaldry (ተገቢ ያልሆነ ንግግርና ቀልድ ወይም በተቀደሱ ነገሮች ላይም መቀለድ), low jesting (ተራ ቀልድ/ጆክ) የሚል ነው::

 

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ለቅዱሳን አይገቡም ወይም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነኝ ከሚሉ ሰዎች ጋር የማይሄዱ ወይም የማይስማሙ ናቸው:: በዚያ ፋንታ ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ምስጋና እንዲበዛለት ጳውሎስ ይመክራል:: ይህም ማለት እግዚአብሔር እንደ አባት ከተወደዱ ልጆች የሚጠብቀው እነዚህን እርሱ የሚያዝንባቸውን ነገሮች ሳይሆን ምስጋናን ነው:: እንደ ተወደዱ ልጆች ለመልካሙ አባታችን ክፉ ነገሮችን መስጠት አይጠበቅብንም ይልቁን በዚያ ፋንታ ምስጋናን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይገባናል::

 

ሐ)በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የሌላቸው ሰዎች:-

 

ጳውሎስ ከላይ የተዘረዘሩትን ኃጢአቶችን መለማመድ ለቅዱሳን የማይገቡ ናቸው ብሎ ብቻ አላለፈም:: አያይዞም እነዚህን ኃጢአቶች መለማመድ የሚያስከትለውንም ክፉ ውጤት ገልጿል:: በዚህ ክፍል ሶስት አይነት ሰዎች በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደሌላቸው ተጠቅሷል:: እነዚህም አመንዝራ፣ ርኩስና የሚመኝ ናቸው:: አመንዝራ ተብሎ የተጠቀሰው ቃል fornicator ወይም ዘማዊ ማለት ነው:: ይህም ከላይ ዝሙት ተብሎ የተጠቀሰውን የሚለማመድን ሰው የሚያመለክት ነው:: ርኩስ ተብሎ የተተረጎመውም ደግሞ ከላይ ርኩሰት ተብሎ የተጠቀሰውን የሚያደርግ ነው:: እንዲሁም የሚመኝ የሚለውም ቃል ከላይ መመኘት ወይም መጎምዠት ተብሎ የተጠቀሰውን የሚያደርግ ነው:: በአዲስ ኪዳን መጎምዠትና መመኘት ወይም ሥስት ጣኦትን እንደ ማምለክ የሚቆጠር ኃጢአት ነው:: በቆላ 3፣5 ላይም ይሄው ነገር እንደሚከተለው ተደግሞ እናገኛለን “...ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት”::

 

ምንም እንኳን ክርስቲያን ቢሆኑም ኃጢአቶችን ጸንተው የሚለማመዱ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ያስተምረናል 1ቆሮ 6፣9-11 ገላ 5፣19-21:: እነዚህ ሰዎች በዚህ በምናጠናው ክፍል በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደሌላቸው የተጠቀሰ ሲሆን፣ በ1ኛ ቆሮቶስና እና በገላትያ ላይ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ተጽፎአል:: ይህም የእግዚአብሔር ከሆነውና ከእግዚአብሔር ተስፋ ጋር ጨርሶ ተካፋይነትን ማጣት ነው:: ይህም ማለት ከድነት ውጪ መሆን ማለት ነው:: በጸጋ አንዴ ድኜአለሁና እንደ ፈለግሁ ኖሬ ድነትን አገኛለሁ የሚባልን ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ አያውቀውም:: በዚያ ፋንታ ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ድነት ሙሉ በሙሉ ገና ያላለቀለት ሂደት እንደሆነና ከሕይወት መጽሐፍም መሰረዝ እንዳለ ነው:: “...በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ” ፊልጵ 2፣12 “ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጎናጸፋል፣ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፣ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ::” ራእይ 3፣5::

 

ጳውሎስ በኃጢአት ጸንተው የሚኖሩ ሰዎች ምንም እንኳን ክርስቲያን ቢሆኑም ከድነት ውጪ እንደሚሆኑ ሲይስረዳ “ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ” ቁ.6 ይላል:: ማለትም በዓለማውያን ላይ እኮ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚመጣው መልካቸው ስለማያምር ወይም እንዲሁ ምንም ስላላደረጉ ወዘተ አይደለም:: ቁጣው የሚመጣባቸው እኮ እነኚህን ኃጢአቶች ስለሚለማመዱ ነው:: ከዚህ የተነሣ ነው:: ስለዚህ በእነዚህ ኃጢአቶች ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች ከሆንን፣ ከእነርሱ ጋርም የቁጣው ተካፋዮች የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም:: “እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ” ቁ.7:: ከዚህ ውጪ ግን፣ በኃጢአታቸው ከማይታዘዙ ልጆች ጋር እየተካፈሉ፣ ክርስቲያን የሚል ስም ስለያዙ ብቻ የእግዚአብሔር ቁጣ ተካፋይ ግን አልሆንም ብሎ ማሰብ፣ ወይም በአንድ ወገን ከማይታዘዙ ልጆች ጋር በኃጢአታቸው እየተካፈሉ በሌላ ወገን ግን ከእግዚአብሔር መንግሥት ጋርም መካፈል ይቻላል ብሎ ማሰብ ይህ እንደ ጳውሎስ አነጋገር “የሚያታልል ከንቱ ንግግር” ይባላል:: “...ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ” ቁ.6:: ወይም በሌላ አነጋገር፣ ማንም በባዶ ቃላቶች (empty words) አያሞኛችሁ (to cheat, deceive) ማለት ነው:: ከእንዲህ አይነቱ የሚያታልል ከንቱ ንግግር እንዲጠበቁና እንዳይታለሉ፣ ጳውሎስ ይህንን ጉዳይ ባነሳበት በ1ኛ ቆሮንቶስ ላይም ያስጠነቅቃል:: ስለዚህ ጉዳይ በ1ቆሮ 6፣9 ላይ ጳውሎስ ሲያስጠነቅቅ “አትሳቱ” የሚለውን ቃል በመጠቀም ነው:: ይህ ቃል ከመንገድ መውጣትን፣ ወደ ተሳሳተ መንገድ መሄድን፣ መሳሳትን፣ መንገድን መሳትን ወዘተ ያመለክታል:: ስለዚህ የጳውሎስ ማስጠንቀቂያ፣ ከማይታዘዙ ልጆች ጋር በክፉ ሥራቸው እየተባበራችሁና እየተካፈላችሁ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥትም እካፈላለሁ ብላችሁ በባዶ ቃላቶች አትታለሉ ወይም አትሞኙ የሚል ነው::

 

እዚህ ላይ ግን አንድ ማስተዋል የሚገባን ነገር፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም ተብለው በኤፌሶንም፣ በ1ኛ ቆሮንቶስም እንዲሁም በገላትያ መልእክቶች ላይ የተጠቀሱት ሰዎች፣ አንድ ቀን ሳት ብሎአቸው በኃጢአት የወደቁ ሰዎች ሳይሆኑ ይህ ማስጠንቀቂያ፣ ኃጢአትን በጽናት የለሚለማመዱ ስዎችን የሚመለከት ነው:: ክፍሎቹ በሙሉ የሚያወሩት አንድ ቀን በዝሙት ስለ ወደቁ ሰዎች ሳይሆን፣ ዘማዊ/አመዝራ ስለሆኑ ስዎች ነው የሚናገርው:: አንድ ቀን በስህተት ስለ ሰከሩ ሰዎች ሳይሆን፣ ሰካራም ስለሆኑ ሰዎች ነው የሚያወራው:: ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የሌላቸው፣ በኃጢአት ጸንተው የሚኖሩ ክርስቲያኖች ናቸው እንጂ፣ በስህተት አንዴ የወደቁና በንስሐ የተመለሱት አይደሉም::


“ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:3-4)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us