ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች » ኤፌሶን » ጥናት 3 (ኤፌሶን 1፣3-14 ለ) መንፈሳዊ በረከቶች - ክፍል 2
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 20 October 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦“
(የዮሐንስ ራእይ 3:14)

rss

Today's verse

ጥናት 3 (ኤፌሶን 1፣3-14 ለ) መንፈሳዊ በረከቶች - ክፍል 2

pdf version

ማሳሰቢያ:- መንፈሳዊ በረከቶች ብለን በሰየምነው በዚህ ጥናት ውስጥ በዝርዝር ልናይ የምንፈልገው መንፈሳዊ በረከቶቹን ብቻ ነው:: ይህም ማለት በረከቶቹን በማን በኩል እንደተባረክንና ይህንንስ ለማድረግ እግዚአብሔርን ያነሳሳው (motive) ምን እንደሆነ አሁን አንመለከትም:: እነዚህን ነገሮች በኋላ ላይ እንመለከታቸዋለንና::

 

1.              በዚህ ክፍል ውስጥ የሚከተሉት መንፈሳዊ በረከቶች ተዘርዝረዋል:-

1.    አለም ሳይፈጠር መረጠን

2.    አስቀድሞ ወሰነን (የእርሱ ልጆች እንሆን ዘንድ)

3.    ቤዛነትና የበደል ስርየት አገኘን

4.    ጸጋውን አበዛልን/አትረፈረፈልን

·       በጥበብና በአእምሮ ሁሉ

·       የፈቃዱን ምስጢር አስታወቀን

5.    ርስትን ተቀበልን

6.    በመንፈስ ቅዱስ ታተምን

 

ማሳሰቢያ:- ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት በረከቶች ውስጥ በዚህ በክፍል 2 ደግሞ ከ4-6 ያሉትን እንመለከታቸዋለን::

 

2.              ጸጋውን አበዛልን/አትረፈረፈልን

 

·       ሀ) ጸጋውን አበዛልን

·       ጸጋ

ተቀባዩ የማይገባው ሆኖ ሳለ ሰጪው በበጎ ፈቃዱ በነጻ የሚሰጠው ስጦታ፣ እንዲያው የሚያደርገው ቸርነትና መልካም ሥራ:: ከሥራ የሚገኝ ነገር ሁሉ ለሠራው ሰው ደመወዙ፣ ለአሠሪው ደግሞ ሊከፍለው የሚገባ ዕዳ እንጂ ጸጋ አይደለም (ሮሜ 4፣4):: ጸጋ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን በተለይ ሰው ከሰው ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያመለክት ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በበጎ ፈቃዱ እንዲያው በነጻ ያደረገልንና የሰጠንን ስጦታ ሁሉ የሚያመለክት ነው:: እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን ነገር ቢኖር፣ ነጻ የሆነና ምንም ሳይከፈልበት የሚገኝ ነገር ሁሉ ብዙ ጊዜ ርካሽ የሆነን ነገር ነው የሚያሳየው:: በክርስቶስ የተሰጠን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ወይም ጸጋ ግን፣ በምንም ዋጋ ሊከፈል የሚችል ያልሆነ፣ ነፍሳችንን እንኳን ብንሰጥ የማይበቃ፣ በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ ተሰብስቦ ሊገዛው የማይችል ነው:: ዋጋ የማይገኝለት ውድነቱ ራሱ እግዚአብሔር ለእኛ በነጻ እንዲሰጠን ካደረገው አንዱ ምክንያት ነው:: 1 ጴጥ 1፣18-19

 

·       ማብዛት (abound)

ከሚያስፈልገው ወይም ከሚበቃው በላይ መጨመር፣ ማትረፍረፍ፣ ማባከን

 

 

የእግዚአብሔር ጸጋ የሚያድን ብቻ ወይም የበደል ይቅርታ የሚያስገኝ ብቻ ወይም ከፍርድ የሚያስመልጥ ጸጋ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን የተትረፈረፈ ጸጋ እንጂ:: ከማዳንና ከይቅርታ በላይ የዘላለምን ክብር፣ ልጅነትና ርስትን ከጥበብና ከአእምሮ ሁሉ ጋር የሚጨምር፣ ከበቂ በላይ የሆነ የተትረፈረፈ ጸጋ ነው:: ለሰው ልጆች የኃጢአት ይቅርታና ምሕረት ራሱ በቂ ነበርና::

 

በሉቃ 15፣11-32 ላይ ባለው የጠፋው ልጅ ታሪክ ላይም የምንመለከተው ተመሳሳይ የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት ነው:: ለጠፋው ልጅ እንደ ሌሎቹ የአባቱ ባሪያዎች መሆን ብቻ በጣም በቂው ነበር:: ቢበዛ ቢበዛ ደግሞ የአባቱን ምሕረት አግኝንቶ የተማረ ልጅ መሆን ብቻ ራሱ ትልቅ ነገር ነው:: አባቱ ግን ከነቆሻሻው ከማቀፍ ጀምሮ፣ አዲስ ልብስንና ቀለበትን እንዲሁም በቤት ለነበረው ልጅ እንኳን አድርጎ የማያውቀውን ታላቅ ድግስ አደረገለት:: ይህም አባቱ ልጁን እንዲያው ይቅር ብቻ ብሎ በዚያ ብቻ ሊያበቃ እንዳልወደደና ምሕረቱና ጸጋው፣ ፍቅሩም የተትረፈረፈ እንደ ሆነ ያሳየናል::

 

·       ለ) በጥበብና በአእምሮ ሁሉ

·       ጥበብ

ጥበብ የሚለው ቃል በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ በተለያየ ሁኔታ ስለተገለጠ፣ የቃሉን ፍቺ እንደ ምንባቡና እንደ ክፍሉ መረዳት ይገባል::

እንደ ጳውሎስ አገላለጽ፣ ጥበብ ማግኘት ማለት ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ተሰውሮ የነበረው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድን ወይም ፕላንን በሙላት ማወቅና መረዳት ነው::

“...እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፣ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምስጢር እንናገራለን::” 1ቆሮ 2፣6-7

“...የእግዚአብሔርን ምስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ፣ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና::” ቆላ 2፣2-3

“...ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው:: ” 1ቆሮ 1፣30

 

በዚህም ክፍል ጥቂት ወረድ ብሎ በኤፌ 1፣9 ላይ “በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፣ የፈቃዱን ምስጢር አስታውቆናልና” ይላል:: ስለዚህ በዚህ ክፍል አገላለጽ ጥበብ የሚለው እንግዲህ የእግዚአብሔር የፈቃዱን ምስጢር ማወቅን፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ ለማድረግ ያሰበውን ዘላለማዊ ፈቃዱን መረዳት ነው::

 

·       አእምሮ

ማስተዋል፣ መረዳት፣ ማገናዘብ፣ ማመዛዘን፣ ማጤን ወዘተ

 

እግዚአብሔር እንግዲህ ከመዳንና ከይቅርታ በላይ በክርስቶስ ያለውን የእርሱን ጥበብ እንድናስተውልና እንድንረዳ፣ በመረዳትም ባለጠጎች እንድንሆን ይወዳል ማለት ነው:: የሰማያዊ ምስጢር መረዳት ድሆች እንድንሆን የእግዚአብሔር አላማ አይደለም::

 

 

·       ሐ) የፈቃዱን ምስጢር አስታወቀን

·       ምስጢር

ምስጢር ማለት:- ያለ፣ ነገር ግን ለሁሉም ያልታወቀ ወይም ያልተገለጠ ጉዳይ ማለት ነው:: ከዘመናት በፊት በእግዚአብሔር ብቻ ይታወቅ የነበረ አሁን ግን ለእኛ የተገለጠ:: ምስጢር ለቀረቡና ለታመኑ ወዳጆች የሚገለጥ ጉዳይ ነው:: እግዚአብሔርም ምስጢሩን ለእኛ ከመግለጡ በፊት እኛን ወደ እርሱ ማቅረብ ነበረበት:: ስለዚህ እግዚአብሔር የሚመቸውን ጊዜ ጠብቆ ነው ማለት ነው ምስጢሩን

የገለጸው::

 

·       የዘመን ፍጻሜ

መጽሐፍ ቅዱስ የዘመን ፍጻሜ ብሎ የሚጠራው ክርስቶስ ወደ አለም ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ያለውን ዘመን ነው:: ዕብ 1፣2 1ጴጥ 1፣20

 

·       የእግዚአብሔር አሳብ/ፈቃድ

·       በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ መጠቅለል

በእንግሊዘኛው:- head up, sum up, bring together, unify etc in christ.

በአማርኛ:- ጠቅልሎ መግዛት፣ አንድ አድርጎ መግዛት ወይም በክርስቶስ አገዛዝ፣ ራስነት፣ ሥልጣን ሥር መሰብሰብ፣ ማያያዝ፣ አንድ ማድረግ፣ ማገጣጠም፣ ማቀራረብ፣ ማዋሃድ፣ ማስማማት ወዘተ

 

እዚህ ላይ እንግዲህ ልብ ልንል የሚገባው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድና አላማ:-

1.             በምድር እና በሰማይ ያሉትን ሁሉ በክርስቶስ ራስነት ወይም ስልጣን ሥር ማድረግ ፊል 2፣9-11 ማቴ 28፣18

 

2.             እርስ በርስ ማዋሃድ፣ ማስማማት፣ አንድ ማድረግና ሰላምን መፍጠር ነው:: በክርስቶስ ራስነት ሥር የሆነ ሰላምና መስማማት (harmony) እንግዲህ አንዱ የእግዚአብሔር ዋነኛው ዘላለማዊ እቅዱ ነው:: አይሁድ ከአሕዛብ፣ ባሪያና ጨዋ፣ ሴትና ወንድ፣ ወዘተ ገላ 3፣28 ኤፌ 1፣11-17

 

 


 

3.              ርስትን ተቀበልን

·        ርስት

ርስት ብሎ እዚህ ላይ የጠቀሰው፣ ውርስን ለማመልከት ነው::

ከመዳን ባሻገር የምንወርሰው የዘላለም ርስት እግዚአብሔር እንዳዘጋጀልን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል::

“ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፣ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን...” ሮሜ 8፣17

የማይጠፋ፣ እድፈትም የሌለበት፣ የማያልፍና በሰማይ የተዘጋጀ ርስት 1ጴጥ 1፣3-5

ርስት ምንም እንኳን የተሰጠንና የተዘጋጀልን ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የምንወርሰው ግን ወደፊት ነው:: ስለዚህ ርስት የቅዱሳን ተስፋ ነው:: እግዚአብሔር ለደህንነት ብቻ አልጠራንምና ነገር ግን ለርስትና ለታላቅም ተስፋ እንጂ::

 

 

4.              በመንፈስ ቅዱስ ታተምን

·       ማኅተም

የባለቤትነት ምልክትና የእውነተኝነት ማረጋገጫ ሲሆን፣ ከማኅተም ጀርባ አንድ ሥልጣን እንዳለ ያሳያል::

 

·       መያዣ

ቀብድ (down payment)፣ እዚህ ላይ ሰለ መያዣ ወይም ስለ ቀብድ ሲናገር ሰለ ግማሽ ዋጋ ለመናገር ሳይሆን በተለይ መያዣነትን፣ ማረጋገጫነትንና ዋስትናን ለማሳየት ነው:: ስለዚህ እግዚአብሔር እንግዲህ መያዣ የሰጠን፣ ርስት ወይም ውርስ እንዳዘጋጀልንና ይህንንም ርስት በርግጥ እንደምናገኝ ለማረጋገጥና ዋስትና ለመስጠት ነው:: በሮሜ 8፣23 ላይ “የመንፈስ በኩራት ያለን” የሚለው ቃል፣ የመንፈስ የመጀመሪያ ስጦታ፣ ሊመጣ ላለው ለዋናው ስጦታ ቅምሻ ማለት ነው:: ስለዚህም እዚህ ቦታ መንፈስ ቅዱስ፣ የተስፋው መንፈስ ተብሎ ይጠራል::

ሌላው እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር፣ ይህንን መያዣ የሰጠን እግዚአብሔር እንጂ እኛ ለእግዚአብሔር የሰጠነው አይደለም:: ስለዚህ በዚህ ክፍል ጳውሎስ መያዣ የሚለውን ቃል፣ እኛ መዳናችንን ለመፈጸም የሚቀረንን ሩጫ ለማመልከት የተጠቀመበት አይደለም::

 


“ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:3-4)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us