ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች » ኤፌሶን » ጥናት 4 (ኤፌሶን 1፣3-14 ሐ) ሠራተኞችና አማኞች
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 20 October 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦“
(የዮሐንስ ራእይ 3:14)

rss

Today's verse

ጥናት 4 (ኤፌሶን 1፣3-14 ሐ) ሠራተኞችና አማኞች

pdf version

ማሳሰቢያ:- በዚህ ክፍል ውስጥ ለማየት የምንሞክረው፣ በጥናታችን ክፍል ውስጥ  የተጠቀሱትን ስብዕት/persons እና መንፈሳዊ በረከቶቹ ወደ እኛ እንዲደርሱ እነርሱ ያበረከቱትን የሥራ ድርሻ ነው:: ይሄም ማለት ለማየት የምንሞክረው በዚህ በጥናታችን ክፍል ውስጥ የተዘረዘሩትን ሥራዎቻቸውን እንጂ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ የተጠቀሱትን አይደለም::

 

በዚህ በጥናታችን ክፍል ውስጥ 4 አይነት ስብዕት/persons እና ለመንፈሳዊ በረከቶቹም እውን መሆን፣ እነዚህ ስብዕት/persons ያበረከቱት ሥራ ተገልጾአል:-

 

1.              አብ

·       ሀ)የአብ የሥራ ድርሻ

1.                  መንፈሳዊ በረከቶቹ ሁሉ ከእርሱ ነው የመጡት ወይም የመንፈሳዊ በረከቶቹ ሁሉ ምንጭና ባራኪ አብ ነው::

·       “...በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ::” ኤፌ 1፣3

·       “...በክርስቶስ መረጠን::” ኤፌ 1፣4

·       “...ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን::” ኤፌ 1፣5

·       “ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን::” ኤፌ 1፣8

·       “...የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና...” ኤፌ 1፣9

 

2.                  በክርስቶስ ለተሠሩት ሥራዎች ሁሉ እቅድና ፕላን አውጪ አብ ነው:: የተጠቀሱትም መንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ እውን የሆኑት እንደ እርሱ አሳብና ፈቃድ ነው::

·       “በክርስቶስ ለማድረግ እንደወደደ እንደ አሳቡ...” ኤፌ 1፣9

·       “...በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም...” ኤፌ 1፣10

·       “እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ...” ኤፌ 1፣11

 

·       ለ)አብ ከላይ የተጠቀሱትን ሥራዎች እንዲያከናውን ያነሳሳው ነገር (motive)

1.                  ፍቅር ኤፌ 1፣4:: በድሮው የአማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም “በፍቅር” የሚለው ቃል እኛ በፍቅር እንድንሆን የሚለውን ትርጉም የሚይዝ ቢያስመስልም፣ በኦርጂናሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ይህ ቃል የአብን ፍቅር የሚያሳይ ነው:: ስለዚህም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም በቁጥር 4-5 ላይ አብ በፍቅር እንደወሰነን ግልጽ ያደርገዋል:: “...በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን”:: ስለዚህ እግዚአብሔር በመንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ እንዲባርከን ያነሳሳው ዋና ነገር ፍቅር ነው::

 

2.                  ይህን ለማድረግ የአብ በጎ ፈቃድ ስለሆነ ወይም ይህንን ለማድረግ ስለወደደ

·       “በበጎ ፈቃዱ እንደወደደ...” ኤፌ 1፣5

·       “በክርስቶስም ለማድረግ እንደወደደ...” ኤፌ 1፣9

·       “እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ...” ኤፌ 1፣11

 

·       ሐ)አብ መንፈሳዊ በረከቶቹን የባረከበት ሁኔታ

·       ከእኛ በጎ ሥራ ወይም መልካምነት ሳይሆን ከጸጋው ብዛት ነው

·       “ዓለም ሳይፈጠር...” ኤፌ 1፣4

·       “...አስቀድሞ ወሰነን::” ኤፌ 1፣5

·       “...እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር...” ኤፌ 1፣6

·       “...እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን...” ኤፌ 1፣7

·       “ጸጋውንም ... አበዛልን::” ኤፌ 1፣8

 

·       መ)አብ መንፈሳዊ በረከቶቹን ሁሉ የባረከበት ምክንያት

·       “...እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ::” ኤፌ 1፣6

·       በዚህ ክፍል ክብር የሚለው ጥሬ ቃል ትርጉሙ:- በሌሎች ዘንድ መመስገንን፣ መከበርን፣ መወደስን፣ መሞገስን፣ መደነቅን ወዘተ የሚያነሳሳ ማናቸውም መልካም ነገር ወይም የተለየ ነገር ወዘተ ነው::

·       ጸጋው የሚያድን ወይም የሚምር መሆኑ ራሱ አንዱ የጸጋው ክብር ነው:: ጸጋው ግን ከምህረትና ከይቅርታ ያለፈ የተትረፈረፈ፣ የልጅነት ስልጣን የሚሰጥ፣ ርስትን የሚያወርስ፣ ጥበብንና ማስተዋልን የሚሰጥ ወዘተ ነው:: እነዚም ነገሮች የጸጋው ክብር ናቸው::

·       “...እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው::” ኤፌ 1፣12

·       እዚህ ላይ የተጠቀሰውን አባባል በተለያየ ሁኔታ ልንረዳው እንችላለን:: በተለይ ግን በእኛ በሠራው ሥራ እግዚአብሔር በእኛም፣ በመላእክትም በፍጥረትም ሁሉ ክብሩ እንዲመሰገን ነው:: ይሄም እኛ ራሳችን የምስጋና ምክንያት እንድንሆን:: ራእይ 5፣8-14

·       “...ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል::” ኤፌ 1፣14

·       እግዚአብሔር በሠራው ሥራ ፍጥረት ሁሉ የእርሱን ጸጋ፣ መልካምነት፣ ምሕረት ወዘተ ወይም ክብር እንዲያመሰግኑ ነው::

 

ማጠቃለያ:- አብ የመንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ ምንጭ እንዲሁም እቅድ አውጪ ነው:: ይህንን ሁሉ ያደረገውም ከፍቅሩና ከበጎ ፈቃዱ የተነሳ ነው:: በጎነቱ ስላነሳሳው፣ ጸጋው ብዙ ስለሆነ እንጂ ከእኛ ማንነትና መልካምነት አይደለም:: ስለዚህም እንዲያው ባደረገው ሥራ ሁሉ ክብሩንና ምስጋናውን ሊወስድ የሚገባው እርሱ ነው::

 

2.              ክርስቶስ/ወልድ

·       ሀ)መንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ (በዚህ ክፍል የተጠቀሱት ስድስቱም በረከቶች በሙሉ) የተባረክነው በክርስቶስ (በክርስቶስ ውስጥ፣ በክርስቶስ አማካኝነት፣ በክርስቶስ ሥራ፣ በክርስቶስ በኩል ወዘተ) ነው::

·       “በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን...” ኤፌ 1፣3

·       “...በክርስቶስ መረጠን::” ኤፌ 1፣4

·       “...በኢየሱስ ክርስቶስ...ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን::” ኤፌ 1፣5

·       “በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን ጸጋ...” ኤፌ 1፣6

·       “በውድ ልጁም...በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት::” ኤፌ 1፣7

·       “...በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን::” ኤፌ 1፣11

·       “...በክርስቶስ አምናችሁ፣ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ...” ኤፌ 1፣13

 

·       ለ)ክርስቶስ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድና ፕላን መፈጸሚያ ነው::

·       “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም፣ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው::” ኤፌ 1፣10

 

ማጠቃለያ:- ይህ በክርስቶስ ወይም በልጁ ወዘተ የሚለው ቃል ከ10 ጊዜ በላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ተጠቅሷል:: በዚህም፣ ምንም አይነት የእግዚአብሔር በረከት ከክርስቶስ ውጪ እንደሌለ ጸሐፊው ለማሳየት እንደፈለገ እንገነዘባለን:: እውነተኛው የወይን ግንድ ክርስቶስ ነውና (ዮሐ 15፣1-11):: በረከቱ ወደ ሰዎች እንዲመጣ ዋናው ቅድመ ሁኔታ የክርስቶስ የመስቀሉ ሥራ ነው:: እግዚአብሔር የአለምን ሩጫና የዘላለም ሃሳቡን የሚቋጨው በክርስቶስ ነው:: ይሄውም ሁሉም ከክርስቶስ ራስነት ስር ሲገዙ:: በዚህ ሁሉ ልንረዳ የሚገባን፣ አብ ለሰው ልጆች መፍትሔንና በረከትን ለማምጣት ያቀደውንና ያሰበውን ሁሉ የፈጸመው በክርስቶስ ነው:: እግዚአብሔር ጥንትም ቢሆን፣ አለማትንና ፍጥረታትን ለመፍጠር ሲያቅድ ይህን እቅዱን የፈጸመው ወይም ተግባራዊ ያደረገው በክርስቶስ ነበር (ዮሐ 1፣1-2 ዕብ 1፣1-2 ቆላ 1፣13-17):: ስለዚህ ክርስቶስ ማናቸውንም እቅዱን የሚፈጽምበት የእግዚአብሔር ጥበብና ዘዴ ነው:: ለዚህም ነው የእስራኤል ልጆች በበረሃ ጉዞአቸው በገጠማቸው ማናቸውም ችግር እንደ መፍትሄነት እግዚአብሔር የሚያመለክታቸው የነበረው ክርስቶስን ነበር (ዮሐ 3፣14-15 1ቆሮ 10፣4 ዮሐ 6፣31-35)::

 

3.              መንፈስ ቅዱስ

እግዚአብሔር ለእኛ ርስት እንዳዘጋጀልን የሚያረጋግጥ፣ የሚመሰክርና በረከቱን በሕይወታችን እውን እንዲሆን ወይም ለእኛ ሕይወት ትርጉም እንዲሰጥ ከሕይወታችን ጋር የሚያዛምድ ነው:: በዚህም ለእኛ ተስፋ የሚሰጠን ነው::

·       “...በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፣ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው...” ኤፌ 1፣13-14

·       “የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል::” ሮሜ 8፣16

 

ማጠቃለያ:- ያለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ አብ በክርስቶስ የሠራው ሥራ ከእኛ ጋር አይዛመድም 1ቆሮ 12፣3:: የእግዚአብሔር ሥራ ከሕይወታችን ጋር ተዋሕዶ ለእኛ ትርጉም እንዲኖረው የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው:: እርሱ ነው እግዚአብሔር የሠራልንንና ሊያደርግልን ያሰበውን ሥራ በሕይወታችን እውን በማድረግ እውነተኛ ተስፋ የሚሰጠን:: ያለ እርሱ እግዚአብሔር ያደረገልን ነገር ሁሉ ለእኛ ምንም ትርጉም አይሰጠንም::

 


 

4.              አማኞች

እግዚአብሔር የባረከን በረከት ወደ አማኞች እንዲመጣ የአማኞች ድርሻ፣ በክርስቶስ ማመን ወይም በእርሱ ተስፋ ማድረግ በቻ ነው::

·       “...በክርስቶስ...ተስፋ ያደረግን እኛ...” ኤፌ 1፣12

·       “እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፣ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፣ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ...” ኤፌ 1፣13

 

እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባው የአማኞች ዋና ድርሻ በክርስቶስ ማመን ነው:: እምነት ደግሞ ሥራ አይደለም ሮሜ 4፣1-5:: ይህ የጥናታችን ክፍል እንግዲህ በሥራና በእምነት ወይም በሠራተኞችና በአማኞች የተከፈለ ነው:: መንፈሳዊ በረከቶቹ ሁሉ ወደ እኛ እንዲደርሱ የሚያስፈልጉትን ሥራዎች ሁሉ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ተከፋፍለውት እንመለከታለን:: ለአማኞች የቀረላቸው ድርሻ ቢኖር ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ላይ ያለ እምነት ነው:: ስለዚህ ጸሐፊው ደጋግሞ አብ ከበጎ ፈቃዱ፣ ከፍቅሩና ከማንነቱ የተነሳ ለክብሩ በክርስቶስ እንደባረከን በሰፊው ሲገልጽ የአማኞችን ድርሻ ግን በእምነት ላይ ብቻ ወስኖታል:: ይህም መንፈሳዊ በረከቶችን የተባረክነው ከእኛ ማንነትና ከመልካም ሥራችን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ማንነትና ጸጋ የተነሳ መሆኑን ያስገነዝበናል:: አማኝ ሁሉ ከሁሉም በፊት በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ማረፍ አለበት:: እግዚአብሔር ያለ እኛ ሥራና ያለ እኛ ማንነት እንደተቀበለንና እንደወደደን አምነን በእርሱ መልካምነት ላይ ልንደገፍ ይገባናል:: እግዚአብሔር እንዲቀበለን ከክርስቶስ መስዋዕት ሌላ ተጨማሪ መሥዋዕት፣ እግዚአብሔር ራሱ ከምህረቱ ከሠራልን ሥራ ሌላ ተጨማሪ የእኛ ሥራ አያስፈልግም:: በጌታ ከምንሮጠው ከማናቸውም ሩጫ በፊት ይህ ለሕይወታችን መሠረት ሊሆን ይገባል:: ክርስትና ከማረፍ፣ ከመወደድ እንዲሁም ከበረከት ነው የሚጀምረው::


“ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:3-4)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us