ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » መጽሐፍ ቅዱስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 10 December 2019
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።“
(የዮሐንስ ወንጌል 15:5-8)

rss

Today's verse

መጽሐፍ ቅዱስ

 


መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ  7
1 የይሳኮርም ልጆች፥ ቶላ፥ ፉዋ፥ ያሱብ ሺምሮን፥ አራት ናቸው።
2 የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም፥ ሽሙኤል፥ የአባታቸው የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቍጥራቸው ሀያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።
3 የኦዚም ልጆች ይዝረሕያ፤ የይዝረሕያም ልጆች ሚካኤል፥ አብድዩ፥ ኢዮኤል፥ ይሺያ አምስት ናቸው፤ ሁሉም አለቆች ነበሩ።
4 ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ።
5 ወንድሞቻቸውም በይሳኮር ወገኖች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች በትውልዳቸው ሁሉ የተቈጠሩ ሰማኒያ ሰባት ሺህ ነበሩ።
6 የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይዲኤል ሦስት ነበሩ።
7 የቤላም ልጆች፥ ኤሴቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ኢያሪሙት፥ ዒሪ፥ አምስት ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ በትውልድ የተቈጠሩ ሀያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ።
8 የቤኬርም ልጆች ዝሚራ፥ ኢዮአስ፥ አልዓዛር፥ ኤልዮዔናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያሪሙት፥ አብያ፥ ዓናቶት፥ ዓሌሜት እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
9 በየትውልዳቸው መዝገብ የተቈጠሩ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ሀያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
10 የይዲኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም ልጆች የዑስ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኪሳአር ነበሩ።
11 እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች አሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
12 ደግሞም ሳፊን፥ ሑፊም የዒር ልጆች፥ ሑሺም የአሔር ልጆችም ነበሩ።
13 የንፍታሌም ልጆች፥ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም፥ የባላ ልጆች ነበሩ።
14 የምናሴ ልጆች ሶርያይቱ ቁባቱ የወለደችለት እሥርኤልና የገለዓድ አባት ማኪር ናቸው።
15 ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእኅትዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁለተኛውም ስም ሰለጰአድ ነበረ፤ ለሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ነበሩት።“ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:3-4)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ The Amharic bible we are using for this website is the version of 1962 [የድሮው ትርጉም]. The Bible Society of Ethiopia is the owner of this bible. The electronic form of this bible was taken from bible.org and converted by iyesus.com from HTML to unicode character (UTF-8) for the purpose of the search functionality. You can find more information about the electronic form here.
Credits: We acknowledge and are grateful to the support we got from our sister Mehret Hailesilassie Woldekidan. She took the time to do the text and punctuation corrections of the entire Amharic bible. We would like to thank her in the name of all users for her dedicated service.
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2019 by iyesus.com
Terms of use | Contact us