መዝሙረ ዳዊት 136 |
1 | እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። |
2 | የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። |
3 | የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
4 | እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
5 | ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
6 | ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
7 | ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
8 | ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
9 | ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
10 | ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
11 | እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
12 | በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
13 | የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
14 | እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |
15 | ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ |