ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 8 May 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የማቴዎስ ወንጌል እና የሉቃስ ወንጌል ላይ የተገለጸው የኢየሱስ የዘር ሐረግ አንድ አይነት አይደለም፡፡

የማቴዎስ ወንጌል እና የሉቃስ ወንጌል ላይ የተገለጸው የኢየሱስ የዘር ሐረግ አንድ አይነት አይደለም፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

የማቴዎስ ወንጌል የሚገልፅው፡-

1
የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
2
አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤
3
ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤
4
ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤
5
ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤
6
እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤
7
ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤
8
አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤
9
ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤
10
አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤
11
አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።
12
ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤
13
ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤
14
አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤
15
ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤

16
ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።
17
እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።


የሉቃስ ወንጌል የሚገልፅው፡-


23
ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ፥
24
የማቲ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የሚልኪ ልጅ፥
25
የዮና ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ፥ የአሞጽ ልጅ፥ የናሆም ልጅ፥ የኤሲሊም ልጅ
26
የናጌ ልጅ፥ የማአት ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ የሴሜይ ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥
27
የዮዳ ልጅ፥ የዮናን ልጅ፥ የሬስ ልጅ፥ የዘሩባቤል ልጅ፥ የሰላትያል ልጅ፥ የኔሪ ልጅ፥
28
የሚልኪ ልጅ፥ የሐዲ ልጅ፥ የዮሳስ ልጅ፥ የቆሳም ልጅ፥ የኤልሞዳም ልጅ፥ የኤር ልጅ፥
29
የዮሴዕ ልጅ፥ የኤልዓዘር ልጅ የዮራም ልጅ፥ የማጣት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥
30
የስምዖን ልጅ፥ የይሁዳ ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥
31
የዮናን ልጅ፥ የኤልያቄም ልጅ፥ የሜልያ ልጅ፥ የማይናን ልጅ፥ የማጣት ልጅ፥ የናታን ልጅ
32
የዳዊት ልጅ፥ የእሴይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥
33
የነአሶን ልጅ፥ የአሚናዳብ ልጅ፥ የአራም ልጅ፥ የአሮኒ ልጅ፥ የኤስሮም ልጅ፥

34
የፋሬስ ልጅ፥ የይሁዳ ልጅ፥ የያዕቆብ ልጅ፥ የይስሐቅ ልጅ፥ የአብርሃም ልጅ፥ የታራ ልጅ፥
35
የናኮር ልጅ፥ የሴሮህ ልጅ፥ የራጋው ልጅ፥ የፋሌቅ ልጅ፥ የአቤር ልጅ፥ የሳላ ልጅ፥
36
የቃይንም ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥
37
የማቱሳላ ልጅ፥ የሄኖክ ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥
38
የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ።
Mar 3, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 3, 2011 ተመልካች ታርሟል

1 መልስ

0 ድምጾች
በማቴዎስ እና በሉቃስ ላይ የተዘረዘሩት ሁለት የኢየሱስ የዘር ሃረጎች መለያየት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎችን ለዘመናት ግራ ያጋባና ያስቸገረ ጥያቄ ነው። ይህ ክፍልም ብዙ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥቃት የሚፈልጉ ሰዎችም እንደ መሣሪያነት የሚጠቀሙበት ክፍል ነው።

ከአብርሃም እስከ ዳዊት ያለው የሁለቱ የዘር ሃረጎች እጅግ ተመሳሳይ ስለሆኑ ምንም ዓይነት ችግር አይፈጥርም። ከዳዊት እስከ ኢየሱስ ያለው ግን ከሁሉት ተመሳሳይ ስሞች በስተቀር ጨርሶ አይገናኝም። ለዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ተቃዋሚዎች የተለያየ መልስና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ተቃዋሚዎች የዘር ሃረጉ እንደዚህ ጨርሶ መለያየቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ስህተተኝነት ያሳያል ብለው ሲከራከሩ፡ በዛው መጠን ደግሞ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ይህንን ሃሳብ የማይጋሩ አሉ። ምክንያቱም በዚያን ዘመን በነበረው የአይሁድ ባህል የዘር ሃረግ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውና በጥንቃቄና በትክክል የሚጻፍ እንጂ እንዲያው በፈጠራ የሚጻፍ አለመሆኑ ነው። ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በአይሁድ ባሕል የዘር ሃረግ በጥንቃቄ ተቆጥሮና ተጽፎ የሚጠበቅ ነው። ስለዚህ ስህተት እንኳን ቢኖረው ይሄን ያህል ስህተት ይገኛል ተብሎ ስለማይታመን፤ ስህተት ነው ብለው የሚከሱ ሰዎች ሃሳብ ተቀባይነት አይኖረውም።

ታዲያ በስህተት ካልሆነ እንዴት የአንድ ሰው የዘር ሃረግ እንደዚህ ጭራሹንም እስከማይገጣጠም ድረስ ሊለያይ ይችላል? ለዚህ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች የተለያየ መልሶችንና ማብራሪዎችን ይሰጣሉ። እኔን ግን ያሳመነኝ የሚከተለው ነው።

በሉቃስ ወንጌል የዮሴፍ አባት እንደሆነ ተደርጎ የተጻፈ የሚመስለው ኤሊ ወይም በእንግሊዝኛው Heli የዮሴፍ ሳይሆን የማርያም አባት ነው። "ኢየሱስ የኤሊ ልጅ፥ የማቲ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ ወዘተ" የሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ በቅንፍ ስለ ዮሴፍ ገብቶአል። ማለትም "ኢየሱስ (እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ የሆነው) የኤሊ ልጅ፥ የማቲ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ ወዘተ" ተብሎ ሊነበብ ይገባዋል። ወይም በእንግሊዝኛው "Jesus ... was the son (so it was thought, of Joseph) of Heli."

ሉቃስ "እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ" የሚለውን ያስገባው፤ ሕዝቡ የዮሴፍ ልጅ የመሰላቸው ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ እንዳልሆነና ይልቁንም የማርያም አባት የኤሊ ልጅ እንደሆነ ለማሳየት ነው። እነርሱ ማለትም ሕዝቡ የዮሴፍ ልጅ ይምሰላቸው እንጂ ከድንግል ስለተወለደ የሥጋ ትውልዱ ከማርያም አባት ከኤሊ ነው እያለ ነው ሉቃስ።

ስለዚህ ማቴዎስ የሥጋውን ሳይሆን ሕጋዊውን የኢየሱስን አባት የዮሴፍን ትውልድ ሲዘረዝር ሉቃስ ደግሞ ሰዎች ዮሴፍ አባቱ የመሰላቸውን ነገር ግን የሥጋ የትውልድ ሃረጉ ከማርያም አባት ከኤሊ የሆነውን የትውልድ ሃረግ ነው የሚዘረዝረው።

ስለዚህ ሁለቱም ወንጌሎች የሚዘረዝሩት ሃረግ ስለ ሁለት የተለያዩ ሰዎች ነው። አንዱ ስለ ዮሴፍ አንደኛው ስለ ማርያም። ከዚህ የተነሳ የሁለቱም ሃረጎች ጭራሽ እስከማይቀራረቡ ድረስ እጅግ የተለያዩ መሆናቸው አይገርምም።

የመለጠ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Mar 4, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 4, 2011 በምሕረቱ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...