ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ምንድ ነው መናፍቅ?

ምንድ ነው መናፍቅ ማለት?
Sep 3, 2011 መንፈሳዊ YaelD (8,160 ነጥቦች) የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
በመሰረቱ መናፍቅ (sect) የሚለው ቃል ከዋናው የሃይማኖት መንገድ የወጡና የተለየ እምነት ያላቸውን ሰዎች ለመጥራት የሚውል ቃል ነው። ከዋናውና ከተለመደው አይነት ሃይማኖት የተለየ እምነት አላቸው የሚባሉ ሰዎች ብዙ ጊዜም የተሳሳተ እምነት አላቸው ብሎ ስለሚታሰብ ማንም ከተለመደውና በአንድ ህብረተሰብ ዘንድ ከሚታወቁ ትልልቅ ሃይማኖት እምነቶች ውጪ የተለየ እምነት ሲኖረው እንደ ስም ማጥፊያ የሚያገለግል ቃል ነው።

በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ የአይሁድ ሃይማኖት ብቻ በነበረበት ዘመን ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀመር አይሁዶች ይህ እምነት ከዋናው ከአይሁድ ሃይማኖት የወጣ ስለሆነባቸው ኑፋቄ ብሉው ይጠሩት ነበር። ጳውሎስ ስለ ራሱ ክርስትና እምነት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
Quote:
የሐዋርያት ሥራ
24፥14 ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ

በየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ከተለመዱና ከታወቁ ሃማኖቶች ውጪ አዲስ እምነት ሲመጣ በቅድሚያ የተሳሳተ ነው ተብሎ ስለሚታመን ኑፋቄ ትምህርት ነው ይባላል፤ ይህንን ትምህርት ደግሞ የሚከተሉ መናፍቃን ናቸው ይባላሉ። መናፍቅ ማለት እንግዲህ ከተለመደውና በአንድ ህብረተሰብ ተቀባይነት ካላቸው ዋና ዋና እምነቶች ውጪ የወጣ የተለየ እምነት ያላቸውን ሰዎች የሚገልጽ ነው። ቃሉ በውስጡ "የተሳሳተ እምነት ተከታዮች" ወይም ከዋናው መስመር ወጥተው የሳቱ ሰዎች የሚል መልእክት አለው።
Sep 5, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Sep 5, 2011 ታርሟል
So like Ethiopian Orthodox that is way far out of the 1st century biblical teaching with all the angel worshiping should be called Eclectic sect a combination of several religious traditions right?
It is not about having the correct doctrine or not. Otherwise the Jewish would have not called the first Christians including the Apostles as sects. It is all about being a separate and new group of religious movement. The ones who call people sects are not necessarily the ones who have the right doctrine but who are in the main stream religion. The orthodox for example used and some are still using to call and label protestant believers as sects because Orthodox religion was until recently the main stream religion.
መናፍቅ ከሀዲ ወይንም በተሳሳተ እምነት ላይ ያሉ ማለት ነው
ውዱ ሓዋርያ ጳውሎስም መናፍቅ ተብሏል። እንዲያውም ጭራሽ "የመናፍቃን መሪ" ተብሏል። በነገራችን ላይ "መናፍቅ፣ መናፍቅ" እያሉ ሰውን መሳደብ እና ማሳደድ የፈሪሳውያን ልማዳቸው ነው። ጌታችን ኢየሱስን እንኳ "ብኤል ዜቡል የአጋንንት አለቃ አለበት" ሲሉ ነበር። እባካችሁ ዛሬም ራሳችሁን የሚታጸድቁ እና ሌላውን መናፍቅ የምትሉ ተጠንቀቁ። ምናልባትም መናፍቁ እናንተው ራሳችሁ እንዳትሆኑ።

የሐዋርያት ሥራ 24
ይህ ሰው (ሓዋርያው ጳውሎስ) በሽታ ሆኖ፣ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን እና የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና፤
6 መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፥ እንደ ሕጋችንም እንፈርድበት ዘንድ ወደድን።

ዋው! ውዱ ሓዋርያ መናፍቅ ሲባል ምን ተሰምቶት ይሆን?
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...