ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 8 May 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በጌታ ሰላም ይሁንላችሁ

ጌታን የአገኘሁት በልጅነት ነው አሁን ግን ወደ50ው እየተጠጋሁ ነው
አላገባሁም በመንፈሳዊ ህይወታ ላይ ጥያቄ እየፈጠረብኝ ነው ምን ላድርግ?
Mar 3, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 3, 2011 ተመልካች ታርሟል
መንፈሳዊ ሂይወት ለማንም ሰዉ አስፈላጊ ነዉ እንዲሁም ትዳር ከሁልቱ ለላ ምን አለ? አመሰግናለሁ

3 መልሶች

0 ድምጾች
ምን አደርግልህ ዝንድ ትወዳልህ?

ማር10፡51ይህንን ጥያቄ እኛ ተጠይቀን ቢሆን ኖሮ?መልሳቸን ምን ይሆን ነበር?
ጆሮ መስማት የሚፈልግው ነገር ምን ይሆን? መስማት የሚፈልገውን? ወይንስ መስማት የሚያስፈልገውን?

እየሱስ እውሩ እውር መሆኑን እያየ ..ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ብሎ መጠየቁ
በራሱ ድንቅ ንው ቢሆንም ግን መጠየቅ አስፈልጎት ነበር.

ምክንያቱም ይህ ስው የለመደው ድምጽ የተለማመደው ድምጽ የበረከተለት ስው ነበር..ያም ደግሞ እለት እለት በተቀመጠበት ወደ እርሱ የሚወረወርለትን የሳንቲም ድምጽ ነበር አንድ ቀን ግን ባለበት ሁኔታ እድሜን ባስቆጠረበት ቦታ ላይ
..በሱ ሁኔታ ላይ እየሱስ እንደ ሳንቲም ስጪ ሳይሆን እንደ ፈዋሽ እንደ እዳኘ በርሱ ዘንደ ሊያልፍ ግድ ነበር ጊዜው ነውና.ስለዚሀ ጌታ በሱ ሁኔታ ባለበት ቦታ
እንዲህ አለው..ከሌሎች የተሻለ ሊሰማ ክሚፈልግውም ቃል የበለጠ እድሜን ለቆጠረበትና ላስቆጥረው ነግር የሚሆንን ይመፍትሄ ቃል ስጠው ይሀውም...

ምን ላደርግልህ ትውዳልህ...? ያንትስ መልሰ?

ተጥያቂም ፈጥኖ እንዲህ ሲል መለስ እንዳይ ሲል መለስ...አየም..
..ተከተለውም.. ተስፋ አትቁረጥ ባንተ ሁኔታ ባለህበት ይመጣል.

በጌታ ፍቅር ተባረክ
Mar 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
Quote:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1
6እግዚአብሔርም ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበርና ጣውንትዋ ታስቆጣት ታበሳጫትም ነበር።

ሐና ልጅ ስለሌላት ፍናና ስታስቆጣትና ስታበሳጫት፡ ሐናም ስታዝንና ስታለቅስ በልብዋም ስትመረረ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ጉዳይ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ማኅፀንዋን የዘጋው ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው የሚነግረን። ስለዚህ እንኳን በእኛ በልጆቹ ይቅርና በትንሹዋ ወፍ (ድንቢጥ) ላይ እንኳን የሚደረሰውን ነገር እግዚአብሔር ሳያውቅና ሳይፈቅድ አይሆንም።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 10
29ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። 30የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
31እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።

ብዙ ጊዜ አይግባንም እንጂ እግዚአብሔር ጸሎትን ያልሰማ ቢመስለንም እንኳን በሕይወታችን ጌታ የሚያደረገው ነገር ለመልካም ነው።

እርሱን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ስጦታና በረከት ብቻ በሚፈልጉት እግዚአብሔር ደስ አይሰኝም። ኢየሱስ ክርስቶስ አምስት እንጀራንና ሁለት ዓሣን አብዝቶ ለአምስት ሺህ ሰዎች ከመገበ በኋላ ምግብ እንደሚሰጥ አይተው ምግብን ፍለጋ የተከተሉትንም ሰዎች እንዲህ ነበር ያላቸው፦
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 6
26ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።

ነፍሱን በመስቀሉ ላይ የሰጠንንና ከዘላለም ፍርድ ወደ ዘላለም ሕይወት የጠራንን የእግዚአብሔር ልጅን ኢየሱስን የምንከተለው ምግብ ስለምሰጠን፤ ከድህነት ስለሚያወጣን፤ ትዳር ወይም ልጅ ስለሚሰጠን አይደለም። እነዚህን ሁሉ ኢየሱስን የማይከተሉና የማያምኑ አህዛብም ሁሉ ያገኙታል። የእኛ ተስፋ ምድራዊ አይደለም። ተስፋችን አንድ ቀን በምድር ላይ ደልቶን የመኖር ወይም አንድ ቀን ኑሮና ትዳር ተሳክቶልን በዚህች ምድር የመኖር ተስፋ አይደለም። እንዲህም አይነት ተስፋ ጌታ አልሰጠንም። እንዲያውም በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነው ያለን። ስለዚህ የመከራውን መስቀል ተሸክማችሁ እንጂ ምድራዊ በረከቴን እየበላችሁ ተከተሉኝ አላለንም። በዚህች ምድራዊ ሕይወት ብቻ ኢየሱስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ ደግሞ ምንኛ ምስኪን ነን ይላል መጽሐፍ ቅዱስ።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
15፥19 በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።

እኛ የተጣራነው በአንደኛ ደረጃ ሰማያዊና ዘላለማዊ ለሆነ ለማይጠፋ ተስፋ ነው። በዚህች አጭር የእድሜ ዘመናችን በምድር እንግዶችና ምጻተኞች እንጂ ተመቻችቶ ነዋሪዎች አይደለንም። በዚህ የምናፈራው ሃብትም ይሁን ትዳር ሁሉም አላፊና ጊዜያው ነው። ክርስቶስ የተሰቀለልን ግን ለዘላለማዊ ማደሪያችን ነው። የዚህች ምድር በረከቱዋ ብቻ ሳይሆን መከራዋና ለቅሶዋም እንዲሁ አላፉ ነው። ለዘላለም እንባችንን ከአይናችን የሚያብስልን ጌታ ጋር ስንሄድ እንባችን ለዘላለም ይታበሳል።

ስለዚህ በዚህች አጭሩዋ ምድራዊ ሕይወታችን በጊዜያዊውና አላፊው በምድር በረከትና ስጦታ ምክንያት ዘላለማዊውንና ክርስቶስ የሞተልንን ሰማያዊውን ተስፋና በረከት እንዳናጣው መጠንቀቅ ይኖርብናል። የእግዚአብሔር ምድራዊ ስጦታ ቀረ ብለን የዘላለሙን እንዳናጣው፡ ኤሳው እንዳደረገው የከበረውን በማይረባው እንዳንለውጠው እንጠንቀቅ።

ይልቁን እንደ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎም አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ቢያድነንም ባያድነንም ላቆምከው ምስል አንሰግድም ብለው እንደቆረጡት፡ እኛም ይሄ ወይም ያ በረከት መጣ ወይም አልመጣ እኛ ግን የተሰቀለልንን የዘላለሙን ተስፋችንን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከመከተል ወደ ኋላ አንልም የሚል የልብ አቋም ይኑረን።

ወንድማችን ሆይ፦ ዘመኑ እውነተኛው ክርስትና መስቀልን ተሸክሞ ጌታን መከተል የሚለውንና እንደ ምጻተኞች በዚህች ሃላፊ ምድር የመኖር ነገር የተረሳበትና ጌታን ምግብ ለመብላት ብቻ እንደተከተሉት ሰዎች ኢየሱስ የምግብና የመኪና የትዳርና የቤት ወዘተ ሰጪ ብቻ ተደርጎ ክርስትና በዚህች አጭር ሕይወታችን የምድራዊውን ሕይወታችንን ብቻ አሳክተን የምንኖርበት ዘዴ ተድርጎ ዋናው ወንጌል የተራሳበት ዘመን ነው። ስብከቱም ትንቢቱም ከመስቀሉ ቃል ወጥቶ ወደ ይሳካልሃልና ይባርክሃል የተገባበት፤ ከዘላለማዊው ወደ ጊዜያዊው፣ ከማይጠፋው ወደሚጠፋ ፈቀቅ የተባለበት ጊዜ ነው። አማኞች ከጌታ ጋር ያላቸው ግንኙነት ምድራዊ በረከት ከመቀበልና ካለመቀበል ያልዘለቀ እየሆነ ነው። በመስቀል ላይ ነፍሱን በመስጠት የተገለጠውና ከሁሉ የሚበልጠው የጌታችን ፍቅር እንኳን በጥርጣሬ የሚታይበትና የፍቅር መለኪያ ምድራዊና ጊዜያው በረከት እየሆነ የመስቀሉ ፍቅር እየተረሳ የመጣበት ዘመን ነው። ስለዚህ ምንም እንኳን እኔ የትዳርን ፍላጎት ግፊት ጠንቅቄ ባውቀውም ከሁሉም በላይ ሃላፊው ትዳር በአንተና በነፍስህ እረኛ መካከል እንዳይገባ እንድትጠነቀቅ አጥብቄ እመክርሃለሁ።

በሌላ በኩል ደግሞ ሰው በጌታ እንጂ በትዳር ደስተኛ እንደማይሆን አሁንም ከብዙዎች ልምድ እውነቱን ልነግርህ እወዳለሁ። ትዳር ትዳር ብለው ለምነውና አልቀሰው ከገቡት ውስጥ ብዙዎች በትዳር ደስተኞች አይደሉም። እንዲያውም ያንን የብቸኝነትና "የነጻነት" ጊዜ የሚናፍቁ ጥቂቶች አይደሉም።

ስለዚህም ይመስለኛል ሐዋርያው ጳውሎስ ሲመክር ከትዳር ውጪ ያሉትን ትዳር መታሰር እንደሆነና ብዙ ፈተናም እንዳለው ስለሚያውቅ ይሄን ያክል ትዳርን እንዳይመኙት የሚያሳስበው። እንዲያውም ወደ ትዳር የሚገቡ ሰዎች በዚህ አለም ብዙ ችግር እንደሚገጥማቸውና ጳውሎስም ይህ እንዳይሆንባቸው እንደሚፈልግ ይገልጻል። በትዳር ውስጥ ያሉት ደግሞ በሰበብ ባስባቡ ከትዳር የመውጣትና "ነጻ" ለመሆን የመፈለግ ፈተና እንዳለ ተረድቶ፡ መፋታታን እንዳይፈልጉ ይመክራል።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
27በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ።
28ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
28 ነገር ግን የሚያገቡ ሰዎች በዚህ ዓለም ብዙ ችግር ይገጥማቸዋል፤ እኔም ይህ እንዳይደርስባችሁ እወዳለሁ።

እግዚአብሔር አባታችን ነው። አባት ደግሞ ለልጆቹ መልካምን ነገር ነው የሚያስብላቸው። ልጁን የሚወድ አባት ሁሉ ልጁ የሚለምነውን ሁሉ አይሰጠውም። መማር ያለበትን ይስተምረዋል፤ መቀረጽ ያለበትን ይቀርጸዋል። ልጆቹ የለመኑትን አሁን ባይሰጣቸው ወይም ጭራሹን ቢከለክላቸው፡ ለእነርሱ አስቦ እንጂ ጠልቶአቸው ወይም ሊጎዳቸው ስለፈለገ አይደለም። ለእኛ አስቦ እንጂ እንኳን ምድራዊና ጠፊ ስጦታ ይቅርና አንድያ ልጁንም እንኳን ሰጥቶናል። የእግዚአብሔር ፍቅር ልክ እንደ ማንኛውም መልካም አባት ሁሉ በመስጠት ብቻ ሳይሆን በማዘግየትና በመከልከልም ይገለጻልና።
Mar 4, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
My question is what are you doing about it?
1. Have you prayed about it? If so, has God said something about it? What did He say? Did He tell you to wait? If He told you to wait, it is a right thing to wait. But if He hasn't said anything, you should keep praying.
2. Is there a curse that disrupts marriage in your family that you know of? Explore and resolve it if so.
3. If you are a guy, have you prayed and started a walk of faith to start a relationship?
People, we got to do a lot on our part! Don't waste your time, do all the necessary steps that is required of you first. And by the way, so many things in our lives could come that could shake our faith. But Jesus is much more valuable than all of those things. As the end draws closer, life for the believer becomes more & more difficult, brother or sister run to Him, tell Him that you don't want your faith to be shaken because of this. Ask Him to give you His grace to keep your faith. He's there to help you keep your faith.

የሉቃስ ወንጌል 22፥31-32 ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።

He's able to give you the strength and grace to say:
ትንቢተ ዳንኤል 3:16 - 18
ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡንም። ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም። የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።
We serve a mighty and true God! He is Lord!
0 ድምጾች
መፅሃፍ ቅዱስ በ እዩ 10.22 ላይ ሲናገር...''
እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር''ይህ ማለት ማንም ሰው በምድር በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በህይውቱ ላይ ስርዓት ያለው ነገር ከሌለ ወይም disorderness ካለ በጨለማ ፈቃድ ስር ነው ማለት ነው።
ነገር ግን ከእ/ር ዘንድ የሆነ ነገር ሁሉ ሰላም ደስታ በጎ ስቶታ ፅድቅ ያለበት ነው።''በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያቆ 1.17''
ደግሞም የእ/ር ፈቃድ ምን እንደሆነ ሲናገር በ ሮሜ 12.2''የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ''

ስለዚህ ይህ በህይወትህ/ሽ እየሆነ ያለው የ እ/ር ፈቃድ አይደለም ጠላት ህይወትህን/ሽን disordered ሊያደርግ ያቀደው ነው ስለዚህ አምላካችን የእንደገና አምላክ ነው እንደገና በህይወትህ/ሽ ላይ እ/ር አዲስ ነገርን ያደርጋል።አሁንም መግባት ትችላለህ/ሽ
Feb 16, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...