ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 25 September 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ስእል ከፊት አድርጎ መጸለይ ጣኦት ማምለክ ነው?

የኦርቶዶክስ አማኞች ስእል ከፊታቸው አድርገው ይጸልያሉ። ኣንዳንድ ሰውች ይህን ይቃወማሉ፤ ጣኦት ማመለክ ነው ይላሉ። እውነት ነው?
Sep 20, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
Quote:
ኦሪት ዘሌዋውያን
26፥1 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ

ኦሪት ዘዳግም 4
15 እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ
16 እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥
17 በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥
18 በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥
19 ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።

ኦሪት ዘጸአት
20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብጽ ካወጣ በኋላ አንዱ የሰጣቸው ትልቁ ትእዛዝ ቢኖር ምንም አይነት ምስል ወይም የተቀረጸ ነገር በፍጹም እንዳያደርጉ ነው። የሰውም ይሁን የእንስሳ ወይም የፀሐይና ጨረቃ ወዘተ ማናቸውንም ምስል ወይም ምሳሌ ማድረግ ክልክል ነው። ስለዚህም አይሁዶች እስከ ዛሬም ድረስ በምኩራባቸው የሰውም ይሁን የሌላ ነገር ስእልና ሃውልት ወዘተ አያደርጉም። ምክንያቱም በቃሉ እጅግ የተከለከለ እና ጣኦትን እንደማምለክ የሚቆጠር ስለሆነ ነው።

በመሰረቱ እስራኤላዊ ያልሆኑ አህዛብ በሙሉ ለጣኦቶቻቸው ምሳሌ የሚሆኑ የተለያዩ ስእሎችና ሃውልቶች ይሰሩ ነበር። ለእነዚህም ምስሎች ከፍተኛ ቦታ ይሰጧቸው ነበር። በእጃቸው ለሰሯቸው ለእነዚህ ምስሎች ይሰግዱላቸውና ይሳለሟቸው ነበር። ጣኦትን ማምለክ የሚባለውም ዋናው ነገር ራሱ እንደዚህ በሰው እጅ ለተሰሩ ምስሎችና ቅርጾች ትልቅ ክብር መስጠት፣ እነርሱን ማምለክና ለእነርሱ መስገድ እንዲሁም መሳለም ነው።

ይሄ የምስል ነገር ታዲያ ከላይ በዘዳግም 4 ላይ እንደተጻፈው የእግዚአብሔርን መልክም የሚያጠቃልል ነው። ማለትም የሰውና የእንስሳት ወይም የሌሎች ነገሮች መልክና ምሳሌ ብቻ ሳይሆን የተከለከለው፤ የእግዚአብሔርን መልክም ጭምር ምስል ማድረግ የተከለከለ ነው። ለዚህ ነው በዘዳግም 4፡1 ላይ እግዚአብሔር ሲናገር "እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ" የሚለው።

የሰውም ይሁን የእግዚአብሔር ወይም የሌላ መልክና ምሳሌ ምስል ማድረግ ስለተከለከለ በዘመናችን በአንዳንድ የክርስቲያን ሃይማኖቶች ዘንድ እንደምናየው የሞቱ ቅዱሳንን ሰእልና ምስልም ቢሆን አይሁዶች አያደርጉም። የሙሴም ይሁን የኤልያስ ወይም የሌላ ታልቅ ነብይ ምስል አያደርጉም ነበር።

የመጀመሪያዎቹም የክርስቶስ ተከታዮች እንደዚሁ ምንም አይነት ምስልና ሃውልት አያደርጉም ነበር። የሰውም ይሁን የእግዚአብሔር ምስል ማድረግ የተከለከለ ስለሆነ፤ የመጀመሪያዎቹ ሃዋርያትና ደቀመዛሙርት አንዳችም ምስል አያደርጉም ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስጠነቅቀውን በመተላለፍ ስእልና ምስል ማድረግ የጀመሩት ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ150 ዓመታት በኋላ ነው። ያኔም ቢሆን እነዚህን ስእሎች ፊት ለፊት አድርጎ ለመጸለይ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት እርዳታ እንዲሆኑ ተብሎ የታሰበ አልነበረም።

እንደ አሁኑ ዘመን ለጸሎትና ለስግደት ወይም ለመሳለም የሚውሉ ስእሎችን ክርስቲያኖች መጠቀም የጀመሩት ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ400 ዓመታት ገደማ በኋላ ነው። ማለትም ይህ በኢየሱስ ወይም በማርያም ወይም በስላሴ ወይም በሌሎች ቅዱሳን መልክ ምስል ማድረግና ለጸሎትና ለመሳለም ወዘተ ጥቅም ላይ ማዋል ጨርሶ የመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖች የማያውቁት በኋላ በተለይ ክርስትና የሮማ መንግስት ኦፊሲያላዊ ሃይማኖት ከሆነ በኋላና ብዙ ጣኦት አምላኪ አህዛብ በመንግስት ተጽእኖ ብቻ ክርስቲያን መሆን ከጀመሩ በኋላ ነው። እነዚህ ዘመናቸውን ሁሉ ጣኦትን በማምለክ የኖሩና አምልኮ ያለ ምስል የሚከብዳቸው አህዛብ በስፋት ወደ ክርስትና ሲገቡ ነው እንግዲህ የራሳቸውን የጣኦት አምልኮ ባህል ወደ ክርስትና ይዘው የመጡት እንጂ የጥንቶቹ ሃዋርያትና ደቀመዛሙርት እንዲህ ያለውን የአህዛብ ባህል አይለማመዱም ነበር።

ለማጠቃለል ያህል እንግዲህ፤ አዎ ማናቸውንም ምስል ማድረግና ያንን ምስል ለጸሎትም ይሁን ለመሳለም መጠቀም በመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የተከለከለና ጣኦትን እንደ ማምለክ የሚታይ ነው። ጣኦትን ማምለክ ማለት ራሱ ቀጥተኛ ትርጉሙ በእጅ ለተሰሩ ነገሮች መስገድ ወይም እነርሱን ማምለክ ማለት ነው።
Quote:
ትንቢተ ኢሳይያስ 46
5 በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?
6 ወርቁን ከኮረጆ የሚያፈስሱ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፥ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል
7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፥ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም
8 ይህን አስቡና አልቅሱ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ።
Sep 20, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...