ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 1 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ዳዊት 70 አመት ብቻ ከኖረ ለምን እድማ ጠገቦ ሞተ ይለናል መጽህፍ?

Nov 8, 2011 መንፈሳዊ መስረት ታደስ (240 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ለዳዊት ያ በቂ ነበር፤ እንዲህ ብሎ እንዳለ፦
Quote:
መዝሙረ ዳዊት
90፥10 የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና።
Nov 8, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን:: አሜን!!!

መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ሃሳባችንን የሚከፋፍል እንዳይገባን ግራ የሚያጋባን እንዲሁም ልክ ባልሆነ መንገድ ሊገባን የሚያደረግ ርኩስ መንፈስ እንዳለ ሁላችን እናውቃለን:: ለምሳሌ ጌታ በሰማርያ ሊያልፍ ግድ ሆነበትና ሲካር ወደ ምትባል ከተማ ደረሶ ከዕድለኛይቱ ሳምራዊቱ ሴት ጋር በያዕቆብ የውሃ ጉድጓድ ቁሞ ውሃ ከለመናት በኋላ ሲነጋገር ካለው ውስጥ እስቲ አንዱን አብረን እንይ:: በዮሐ 4:23 ኢየሱስ "ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል..." ይላል::

ብዙ ጊዜ ሲዘመር ከመድረክ ስብከት መሃል ሆነ እኛም ስንጠቅሰው በሌሎችም ሲባል ደጋግመን የምንሰማው ቃል ነው:: ብዙ ጊዜ በእውነትና በመንፈስ ያመልኩታል ሲባለ ሲዘመር የምንሰማው:: ታድያ ምን ልትል ፈልገህ ነው? የሚል ሰው በመሃላችን አይጠፋ ይሆናል.. እኔ ላሳስብ የፈለጉት ጉዳይማ ቃሉን ስንጠቀስ በቀጥታ ያን የምንፈልገውን ቃል እንጥቀስ:: ለምሳሌ እዚህ የቀረበው ጥያቄ ላይ ከቃሉ የራቀ እውነትን የመሰለ ግን እውነት ያልሆነ ቃል ተመርኩሶ ነው:: የሐሥ 13:36 ላይ ያለው ቃል ይመስለኛል:: ይህም የሚለው ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ ነው የሚለው እንጂ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ አይልም:: ዋናው ነገር በተሰጠን ዕድሜ የተሰጠንን መክሊት/ምናን ስራ ላይ አውለን አትርፈን ማንቀላፋቱ እንጂ በዚህ አላፊ ምድር ረጅም ዘምን መኖር አይደለም:: በዚህ አደገኛ ጊዜ የመጨረሻ ዘመን እላለሁ የተሰጣትን ሃላፊንት ለመወጣት የሚያስችል ሙሉ በሙሉ የመሰጠትን መንፈስ ለቤተ ክርስቲያን ያብዛላት::

ወንድማችችሁ
ጌታ ይባርካችሁ
Nov 9, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Nov 9, 2011 ታርሟል
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
23፥1 ዳዊትም በሸመገለ ጊዜ፥ ዕድሜንም በጠገበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።
ተባረክ የፈለኩት ጥያኪ 1 ዚና 23፣1 ነበር ነግር ገን መልሱነ ከላይ እንዳሰከመጥከው ዋናው ነግር በተስተን እድሚ ስርቶ ማለፍ ነው ማቱሳላ ምን ሰራ?
ውድ ወግውኖች:-
ስላስተማራችሁኝ የዳዊት ዕድሜ መጥገብ ጌታ ይባርካችሁ::

ማቱሳላ ያን ያህል ኑሮ ምን ሰራ ለሚለው መቸም ዘፍትረት 5 ላይ ስናነብ ወደ አባቶቹ ወደ ልጆቹ ካቶከርን በቤተስቡ የምናዬው መልካም ጉዳይ አይጠፋም:: ቤተሰቡ በጣም እግዚአብሔርን የሚፈራ የተባረከ እንደ ነበረ ማየቱ አያስቸግርም:: አባቱ እግዚአብሔር እንደ ወሰደው እናነባለን:: የልጁን ልጅ ኖኅን ስናይ ደግሞ በዚያን ጊዜ ከነበረው ሕዝብ መሃል እግዚአብሔር ፈልጎ ያገኘውን የኖኅ ቤተስብን ነበር:: ባሁን ዘመን ትልቁ ችግር እግዚአብሔርን የሚፈራ ልጅ ትውልድ ማሳደግ ነውና ማቱሳላ ፈሪሃ እግዚአብሔርን በቤተስቡ ውስጥ ትልቅ ስፍራ በመስጠት ልጆችቹን ያሳደገ እንደ ነበረ እናያለን::

ወንድማችሁ
ጌታ ይባርካችሁ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...