ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን:: አሜን!!!
መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ሃሳባችንን የሚከፋፍል እንዳይገባን ግራ የሚያጋባን እንዲሁም ልክ ባልሆነ መንገድ ሊገባን የሚያደረግ ርኩስ መንፈስ እንዳለ ሁላችን እናውቃለን:: ለምሳሌ ጌታ በሰማርያ ሊያልፍ ግድ ሆነበትና ሲካር ወደ ምትባል ከተማ ደረሶ ከዕድለኛይቱ ሳምራዊቱ ሴት ጋር በያዕቆብ የውሃ ጉድጓድ ቁሞ ውሃ ከለመናት በኋላ ሲነጋገር ካለው ውስጥ እስቲ አንዱን አብረን እንይ:: በዮሐ 4:23 ኢየሱስ "ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል..." ይላል::
ብዙ ጊዜ ሲዘመር ከመድረክ ስብከት መሃል ሆነ እኛም ስንጠቅሰው በሌሎችም ሲባል ደጋግመን የምንሰማው ቃል ነው:: ብዙ ጊዜ በእውነትና በመንፈስ ያመልኩታል ሲባለ ሲዘመር የምንሰማው:: ታድያ ምን ልትል ፈልገህ ነው? የሚል ሰው በመሃላችን አይጠፋ ይሆናል.. እኔ ላሳስብ የፈለጉት ጉዳይማ ቃሉን ስንጠቀስ በቀጥታ ያን የምንፈልገውን ቃል እንጥቀስ:: ለምሳሌ እዚህ የቀረበው ጥያቄ ላይ ከቃሉ የራቀ እውነትን የመሰለ ግን እውነት ያልሆነ ቃል ተመርኩሶ ነው:: የሐሥ 13:36 ላይ ያለው ቃል ይመስለኛል:: ይህም የሚለው ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ ነው የሚለው እንጂ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ አይልም:: ዋናው ነገር በተሰጠን ዕድሜ የተሰጠንን መክሊት/ምናን ስራ ላይ አውለን አትርፈን ማንቀላፋቱ እንጂ በዚህ አላፊ ምድር ረጅም ዘምን መኖር አይደለም:: በዚህ አደገኛ ጊዜ የመጨረሻ ዘመን እላለሁ የተሰጣትን ሃላፊንት ለመወጣት የሚያስችል ሙሉ በሙሉ የመሰጠትን መንፈስ ለቤተ ክርስቲያን ያብዛላት::
ወንድማችችሁ
ጌታ ይባርካችሁ