ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እንደ ክርስቲያን ልክ ነው ልክ አይደለም? ምን ትላላችሁ?

የጌታ ሠላም ለሁላችሁ ይሁን!!!
ይህን ጥያቄ መጠየቄ ልክ ይሁን አይሁን ባላውቅም ለትምህርት ከሆነ እንኳን ብዬ ለመጠየቅ አሰብኩ፡፡
የገጠመኝ ነገር እንደዚህ ነው
እኔ በጌታ አምኜ የዳንኩ ዳግም የተወለድኩ ወጣት ክርስቲያን ነኝ ጓደኛዬ ደግሞ ጌታን እንደ ግል አዳኝዋ አድርጋ ያልተቀበለች የሌላ ዕምነት ተከታይ ነች፡፡ ጓደኛዬ የትዳር ጓደኛ አላት ግን አላገባችውም ነገር ግን እሷ እንደነገረችኝ በአጋጣሚ ግንኙነት ያደርጉና ታረግዛለች ይሄንን ነገር ደግሞ ለኔና ለጓደኟዋ ብቻ እንደነገረችን አወራችኝ ለምን ከብዙ ጓደኞችዋ መርጣ ለኔ እንደነገረችኝ ስጠይቃት አንቺ ሚስጥሬን ትጠብቂያለሽ ብዬ ነው አላችኝ ከዛ እኔም እሺ ለማንም አላወራም አንቺም አታውሪ አልኳትና በተፈጠረው ነገር ምን እንዳሰበች ጠየኳት እሷም ማስወረድ አለችኝ እኔም አዘንኩና ይሄ ነገር እኮ እግዚአብሔርን ያሳዝነዋል ደግሞም ኃጢአት ነው አልኳት እሷም አውቃለው ግን ምንም ማድረግ አልችልም አለችኝ ከዛ ብዙ ነገሮችን አዋራኋት እጮኛዋን አዋርታው አብሮው እንዲኖሩ ነገርኳት ግን እንቢ በቃ አስወርዳለው አለችኝ ስታስወርድ ግን አብሪያት እንድሆነ ጠየቀችኝ እኔም እሺ ልጸልይበት አልኳት ጸለይኩበትም ግን ግልጽ የሆነ መልስ በህልምም ይሁን በሌላ መንገድ አላገኘሁም (ምን አልባት ማስተዋል አቅቶኝ ልሆን ይችላል) በዚህ ሁኔታ ውስጥ አብሪያት ለመሄዴ ሳስብ ውስጤንም ስሰማው ምንም የስህተት ነገር አልተሰማኝም እና ጥያቄዬ አብሬያት ምታስወርድበት ቦታ “ህጋዊ ቦታ” ብሄድ እንደ ክርስቲያን ልክ ነው ልክ አይደለም? ምን ትላላችሁ መልሳችሁን እጠብቃለው ቢሆን መልሳችሁ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ቢሆን ደስ ይለኛል፡፡
ጌታ ኢየሱስ ማስተዋሉን ያብዛልን
አሜን
በጌታ በኢየሱስ ሰላም ሰላም ሁኑ!!!
በጌታ እህታችሁ
Nov 24, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

4 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም ለአንች ይሁን የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከአመጽ ይራቅ የሚለው ማሃተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሄር መሰረት ቆሞአል 2ኛ ጢሞቲወስ 2፡19 እንዲሁም ቲቶ 2፡14ን እንመልከት። ህጻንን ከእናቱ መሃጸን እያለም መግደልም አመጽ ነው ጌታንም በጣም ያሳዝነዋል ። ወደ ጌታ ልትመጣ የምትችለው አንዱ መንገድ በአንቺ ህይወትም ነው ። ውሳኔዋን እንድትለውጥና ህጻኑ እንዲተርፍ በምትችይው ተባበሪያት በጸሎትም እርጃት የሰማይና የምድር አምላክ በሁኔታው ይንገስበት። ተባረኪ
Nov 24, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የጌታ ሰላም ይብዛልሽ
የጌታን ፍቅር ማሳየትሽ መልካም ነው። ነገር ግን ቦሃላ በጣም ይቆጭሻል። ሀጥያት ነቱን እያመነች ከቀጠለችበት ለዘላለም እራስዋን ሰይጣን ሲኮን ንናት ነው የሚ ኖሮው ጌታን እኻን ተቀብላ ጌታ የቅር ቢላትም አይቀርም እና እዝህ አሚሪካ በሬድዮ ሴቶች በጣም ሰያዝኑ ለምን አደረግን በላው ሲአለቅሱ የምንሰማው። ማን ያውቃል ጌታ አንቺን ተጠቅሞ የህጻኑን ህይወት ለአድን እንደሆነ? በሙሴ ግዜ በፈሮን፤ በጌታ ግዜ በንጉሡ ሄሮድስ፤ ዛሬም ደግሞ በአስወርጅ ዶ/ክ የሚሰራ ሰይጣን ነው። እባከሽ አግዚአት ወደ እውነቱ እንድትመጣ። By the way "ህጋዊ ቦታ" ያልሽው መንግስት ህጋዊ አደረገው ማለት ልክነው ማለት እንዳልሆነ የገባሽ መሆንሽን አልጠራጠርም ከህግሁሉ በላይ የሆነ የ ሰማያዊ ህግ እንዲገዛን የታወቀ ነው። ነጻነታችን ሃጥያት ላለማረግ እጂ ሀጥያት ለማድረግ አይደለም።
በርቺ ጌታ ካንቺ ጋር ነው ሰው ህይወቱን ለጌታ እስከሞት ይሰጣል አንቺ ደግሞ ለጌታ ለሆነው እውነት እንድትቆሚ በሩ ተክፍቶ ለሻል። ምን የሆን የምተመርጭው? To stand for righteousness or be a part of ungodly? May the Lord give you wisdom and favor before your friend so she can listen to you. I am praying for you.
Nov 24, 2011 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ውርጃ ኃጢአት ነው።ይህንን አንቺም በትክክል አስቀምጠሽዋል።ጉአደኛሽ ይህንን አስከፊ ድርጊት እንዳትፈጽም በተቻለ አቅም ለማስረዳት በመሞከርስ ደግ አርገሻል፡፡የሆነ ሆኖ ግን ምክርሽን ለመስማት ፈቃደኛ ሆና አልተገኝችም። አንቺ ደግሞ ኃጢአትን በአንደበትሽ መቃወም ብቻ ሳይሆን በድርጊት ባለመተባበር አቅዋምሽ ግልጽ መሆን አለበት።ወደ ውርጃው ቦታ አትሂጂ እያልኩ ነው ያለሁት።ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡(ያዕ 2፡26)ክርስቲያን በኃጢአት ላይ ልፍስፍስ ሳይሆን ጨካኝ ነው።ምናልባት ይህ ድርጊትሽ የርስዋን ጉአደኝነት፡ሊያሳጣሽ ይችላል።ማወቅ ያለብሽ ክርስትና ዋጋ ያስከፍላል። በዚህ አጋጣሚ ስለ እምነት አርበኞት የሚናገረውን ዕብ 11 እንድታጠኚ በጌታ ፍቅር እጠይቅሻለሁ።ጸጋ ይብዛልሽ።
Nov 30, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የተከበሩ እህታችን

ይህ እግዚአብሕሔርን የሚያሳዝን ዉሎ አድሮም እርሶን የሚጸጽት ተገባር ሰለሆነ በማንኛዉም መልኩ መተባበር የለቦትም ብየ ወንድማዊ መልእክት እስጦታለሁ። አስረጂ መ/ቅዱሳዊ መረጃዎችንም ያሳዩ ክሁሉም በላይ ግን እንደምንም ብለው በማሳመን በአልትራ ሳዉንድ በመታገዝ ጽንሱን ጉዋደኛዎት እንዲመለከቱት ያድርጉዋችዉ። ይመኑኝ ውድ ጉዋደኛዎ የቱን ያክል ዘግናኘ ተገባር ሊፈጽሙ እንደተዘጋጁ ተረድተዉ ህሳባችዉን ሊቀይሩ እንደሚችሉ እምነት አለኝ። ይህ ተሞክሮ የብዙ እናቶችን ሃሳብ እንዳሰለወጠ ሰምቻለሁ። ይህንን መልእክቶን ያሰነበበኝ እና የስማሁትን እንዳካፍሎት ያደረገ እግዚአበሐር ምክነያት አለዉ ብየ አምናለሁ።

እግዚአብሐር ለበጎ ተግባር ሁሉ ይርዳችሁ!

ወንድማችሁ
Dec 7, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...