ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 21 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ያንቀላፉት የት ነው ያሉት?

ቅዱሳን የጌታ ሰላም ይብዛልን!
በዚህነዚህ ቀኖቻን አዲስ ሳምንትም መከናወንን መሳካትን መኪልታችችንን የምናተርፍበት ሳምንት ይሁንልን::

ወደ ጥያቄ ልግባና ላቅርበው ጥያቄ የሆነበኝና የጥያቄን መነሻ የሆነው ቃሉ:-

ራእይ 6:10-11 ላይ "ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከ መቸ ድረስ አትፍርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባርያዎች ባልጀራዎችቻቸውና የወንድሞቻቸው ቁጥር እስኪፈጸም ድረስ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው":: ይላል::

በዚህ ካለነው ካንባቢዎች ውስጥም ቁጥሩን የምንሞላ እንኖር ይሆናልና በሚመጣው ሁሉ ተዘጋጅተን እንድንጋፈጠው ጌታ ይርዳን:: ሱናሚ ተነስቶ የባሕሮችና የውቅያኖሶች ውሃ ምድርን ቢሸፍኑ እንድ ኖህ መርከብ የምትንሳፈፍ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናትና እንጽና::

ጥያቄ በብሉይ የነብሩት የእግዚአብሔር ቅዱሳን እንደ አብርሐም ኢሳቅና ያዕቆብ እንዲሁም ሞትን ድል አድርጎ ጌታ ተነስቶ ወደ አብ ካረገ በኋላም ያንቀላፉት ቅዱሳን እንደነ ጳውሎስ ጴጥሮስ አሁን የት ነው ያሉት? ቀደም ሲል ባነበበንው ከሆነ ባሉበት ሁነውስ ያዩናል ውይ? አለመፈረዱ ባያዩ ኑሮ በጌታ ፊት ይህን ጥያቄ እንዴት ሊያቀርቡ ደፈሩ? እባካችሁ እርዱኝ::

ጌታ ይባርካችሁ::
Nov 28, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

–1 ድምጽ
Quote:
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
5፥8 ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል

2 Corinthians 5:8
Thus we are full of courage and would prefer to be away 1 from the body and at home with the Lord.
Quote:
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1
20 ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በህይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል።
21 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና
22 ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም።
23 በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና
24 ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።

እንደ ጳውሎስ አገላለጽና ናፍቆት ከሆነ በጌታ አምነው ያንቀላፉት በጌታ ዘንድ ነው የሚሆኑት!
Nov 28, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...