ህም.....
ጥሩ ጥያቄዎች ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች ሁሉ ጠይቆ ሊረዳው የሚገባ አይነት ናቸው።
ጽድቅ
ጽድቅ የሚለው ቃል አማርኛ ሳይሆን ዕብራይስጥ ነው። የዕብራይስጥ ትርጓሜዎቹም "ትክክለኝነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጎ ምግባር" የሚሉ ናቸው። በስትሮንግስ መዝገበ ቃላት ውስጥ ቁጥሩ "H6666" ነው። ትርጓሜውንም እንዲህ ያስቀምጠዋል፦
Quote:
H6666
צדקה
tsedâqâh
tsed-aw-kaw'
From H6663; rightness (abstractly), subjectively (rectitude), objectively (justice), morally (virtue) or figuratively (prosperity): - justice, moderately, right (-eous) (act, -ly, -ness).
ለእነዚህ ትርጓሚዎች ትክክለኝነት ብዙ ጥቅስ ለማየት እንዲችሉ በዚሁ ድረገጽ ነጻ ዳውንሎድ የሚለው ቁልፍ ስር የሚገኘውን የአማርኛ ጥቅስ መፈለጊያ ሶፍትዌር ወደ ራስዎ ኮምፒውተር ገልብጠው ይጫኑ። ከዚያም "ጽድቅ" የሚለውን ቃል ይፈልጉ። 294 የሚያህሉ የመጽሓፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ ይኸው ቃል ይገኛል። በዚሁ መልክ የትርጓሜውን ትክክለኝነት ባሻዎ ጥቅስ ያረጋግጡ።
የሰው ጽድቅና የእግዚአብሔር ጽድቅ
የሰው ጽድቅ የሚባለው፣ ሰው አምላክን ለማስደሰት ብሎ በራሱ ዓቅምና ተነሳሽነት ሲጥርና ሲደክም የሚሰራው መልካም ስራ ነው። ለምሳሌ
ማቴ 18
Quote:
...ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥
10 እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
11 ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
12 በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
13 ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
14 እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።
በዚህ ክፍል ውስጥ ፈሪሳዊው ምንም ክፋት አላደረገም። የዚህ ሰው ችግር ግን ሁሉን ያደረገው ጥሮ ግሮ ስለሆነ በገንዛ ሥራው ራሱን አጽድቋል። ስለዚህም "ራሱን ከፍ የሚያደርግ" የሚለው ሓረግ የዋለው ለእርሱ ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ ግን እንዲህ አይደለም። ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም!!
Quote:
ኤፌሶን 2
8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ቀደም ሲል በጠቀስኹት በማቴዎሱ ክፍል ላይ፣ ቀራጩ ኃጢያተኛ ሆኖ ሳለ ያለ ምንም መልካም ስራ እግዚአብሔር አጽድቆት ተመለሰ። ስለዚህ ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንጂ የሰው አይደለም። የእግዚአብሔር ፅድቅ ላይ የሰው የሥራ አስተዋጽኦ የለበትም። እንዲሁ በምህረት የሚሰጥ ነው እንጂ ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም።
Quote:
ሮሜ 9፤16
እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 1፥17
ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች
3፥21
አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥
3፥22
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
ይህን ለማጠቃለያ ልጥቅስና ልጨርስ
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 10፥3
የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።
ከጻፍኹት ሁሉ ያልገባዎ ነገር ካለ ከዚህ በታች "አስተያየት ይስጡበት" የሚለውን መጫን ይችላሉ።
አመሰግናለሁ!!!