ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ኢየሱስን ትወደዋለህ ወይ??

Mar 4, 2011 መንፈሳዊ ቢኒያም ተኸልቁ (220 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ነብሴ እስኪተፋ ነዋ.ያለ እርሱ ማን አለ ለኔ
Mar 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ጥያቄውን ያቀረብው ጌታ ይባርከው። አጠር ያለ በሶስት ቃለት የተገነባ ቀላል ጥያቄ ይመስላል።

ይህ ጥያቄ የቀረበለት ወይም ሲባል ለሰማ አማኝ በጣም ደስ የሚያስኝ ልብን የሚንካ ጥያቄ ነው። ሲባል ብሰማ ወይም የቃል ጥያቄ ሆኖ ቢቀርብለኝ ያለ ምንም መወላውልና መመቻመች "እንዴታ!" ብዬ መልስ ስሰጥ ነው እንደ ፊልም የሚታየኝ።

ነገር ግን ይህ የሰጠሁት መልስ በእጅ ውሃን መጨበት እንዳይሆንብኝ በጣም መጠንቀቅ አለብኝ። በአማርኛ መውደደና ፍቅር የሚል ቃላት እንጠቀማለን እንግሊዝኛውም ሰነፍ አይደለም እንድዚሁ የመሳሰሉ ቃላት አሉት "love & intimacy"። ይህ እየሱስን አፈቅረዋልሁ የምልበት እውነተኛ ቃል ጠለቅ ያለ ከባድ ሃላፊነትን ያዘለ ቃል መሆኑን በማስተዋል በአነጋገር ሆነ በደርጊት ልፈጽመው የሚጠበቅብኝን እንዳልረሳ ችላ እንዳልል ይገባኛል። ይሀም ስል ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ "እግዚአብሔር ሲረዳ ከሰማያት ወርዶ" የሚል መዝሙራቸውን እያሰቡክ ነው።

አምኖ ከአማኞች ጋር ጌታን ማምለክ መልካምና ተገቢ ነው። ሕብረትን ቤተ/ክንን መመስረት ወንጌል መስበክን በተለያዬ ዘርፍ ጌታን ማገልገል እጅግ መታደል ነው። ጠላት የሚመጣበት መንገድ ብዙ ነውና ራስን ከፍ ከፍ ለማድርግ ለመታየት ውድድር ውስጥ ለመግባት ሳይሆን በልባዊ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ቢሆን ደግሞ የመታደል መታደል ነው። ይህ የመታደል መታደል ዕድል ግን ባሁኑ ጊዜ ጎልቶ የማይታይበት ምክንያቱ ምን ይሆን?
ውንጌል ያለ ፍቅር ከንቱ ልፋት ነውና ጌታ ለቤተ ክርስቲያን ጻጋውን ያብዛላት እላለሁ።

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላል። ጌታ እየሱስም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱም ብሎናል ዓለም የምታውቅበት መለዮቻን ነውና። ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን 5፡8 ቀድሞ ጨለማ ነብራችሁ... ብሎናል። ጨለማ በጨለማ ውስጥ የነበርን አሁን ሌላ ለውጥ አግኝተናል ማለት ነው ግን ይህ ለውጥ እንዴት ነው ልንኖረው የሚገባን? የእግዚአብሔር ስራ የሰው እጅ ሲገባበት እጀ እጅ ነው የሚልወና በሰው ጥበብ ፈጽሞ እንደማይቻል እንወቀው። ይሀን ስነድፍ በዛብሎንና በንፍታሌም ላይ ነብዩ ኢሳያስ ያልውን ትዝ አለኝ (ማቴ 4፡15)

ቤየሱስ ያገኘነው ለውጥ ምንነት ጌታ በማቴ 5፡13 - 16 የምድር ጨው አና የዓለም ብርሃን ናችሁ ይለናል አድርጎናልም። በዚህ ጊዜ ዓለም ግራ በምትጋባብት ወቅት እየሱስን እወደዋልሁ ማለት እርፈት ነው ሌላው ሲገላበጥ እንቅልፍ አልባ ሲያደር ከልብ እየሱስን እወደዋልሁ ማለት እንዴት ያለ ዕድል ነው! እንዴት ያለ ክብር ነው! ጌታ መብራታችሁ በሰዎች ፊት ይብራ ያለው በይበለጥ ይዚህ ትውልድ ዕድሉ ሰፊ ይመስለኛል። ይህ ጊዜ ያዘመራ ወቅት ስለ ሆነ ለነፍሳት መዳን መስዋዕታችንን እናቅርብለት። ምን ዓይነት መስዋዕት? ዘሌዋውያን 16 ላይ እንዳለው የተወሰነ ጉዳይ ሳይሆን ከሰው ወደ ሰው የተለያዬ ግን ጥቅሜ ይቅርብኝ የሚያስብል ልባዊ መስዋዕት መሆን አለበት።

አማኞች! ደስ ይበላችሁ ደግሜ ደስ ይበላችሁ ይለናል ቅዱስ ጳውሎስ። እየሱስ አከበረን እሱ ከውደደን ማን ነው የሚጥለን? ስለዚህ ይህ እየሱስን እወደዋልሁ የምንለው ፍቅር ይዞት የሚመጣውን ወደን ፈቅደን የተቀበልነውን ያለብንን ሃላፊነት የምንወጣበትን የመንፈሱን ኃይል ይሙላን። አሜን!!!

ገታ ይባርካችሁ
Mar 5, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 5, 2011 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...