ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 18 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እግዚአብሄር በሰው ላይ መከራ ያመጣል ( በመከራ ሰውን ይፈትናል )???

Dec 30, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

0 ድምጾች
ስላም ይሁንልወት.....እግዚአብሄር ስውን በመከራ አይፈትንም። ቅዱስ ቃሉ እንደሚለው የያዕቆብ መልእክት 1 ፡ 13 ማንም ሲፈተን በእግዚአብሄር እፈተናለሁ አይበል እግዚአብሄር በክፉ አይፈትንምና እርሱ እራሱስ ማንንም አይፈትንም። በእኔ መረዳት እዮብም በስይጣን ነው የተፈተነ። ከያዕቆብ መልእክት 4 ፡ 11 ላይ ቃሉ እንደሚነግረን ጌታ እራራለት እንጅ ፈተነው አይለንም ። በማቲወስ ወንጌል 6፡ 13 ላይ እግዚአብሔር ወልድ እንዴት እንደምንጸልይ ሲያስተምረን " ከክፉ አድነን እንጅ ወደ ፈተና አታግባን " ይህ ሃሳብ በአንድ መወስድ አለበት ነው ብየ አምናለሁ ክፉው ነው ወደ ፈተና የሚያስገባ ። ክፉ ሃሳባችን ምኞት የሰወች ክፉ ሃሳብ ክፉ መናፍስት ።
Jan 3, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
እግዚአብሄር ሰዉን በክፉ አይፈትንም ነገር ግን የሰዉ ልጅ ክፉ ስራዉ ወደ መጥፎ ፈተና ወስዶ ዋጋ ሊያስከፍለዉ የችላል።ሰዉን በክፉ የሚፈትነዉ ግን ሰይጣን ነዉ።ኢዮብ በክፉ ስራዉ ሳይሆን ለኢግዚአብሄር ታማኝ ልብ ያለዉ ሰዉ ስለነበር በሰይጣን ተፈትኖአል።
ጌታ ግን ከዚህ መከራ ሁሉ ታድጎታል አስመልጦታል።
–1 ድምጽ
አዎን ይፈትናል...

እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ እስራኤልን በመከራ እንድትገባ አድርጓል። እኛም ብንሆን "ወደ ፈተና አታግባን" ብለን የምንጸልየው እግዚአብሔር ወደ ፈተና ሊያገባን እንደሚችል ስለምናውቅ አይደለምን?? በርግጥ መከራ ውስጥ ሲያስገባን የተለያዩ መሳሪያዎችን ይጠቀማል። ለምሳሌ-- ሰይጣንን (1ኛ ቆሮ 5፤5)
Quote:
መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
ሰዎችን (በብዛት እስራኤልን በሶርያ ይቀጣ ነበር!!)
ድህነትን፤
Quote:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
2፥6
እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።
በሽታንና ሌሎችንም ይጠቀማል።

እዮብ ላይ መከራ ያመጣው እግዚአብሔር ሲሆን የተጠቀመበት ደግሞ ሰይጣንን ነው። ይህ መከራ የተዘጋጀው የእዮብን ታማኝነት ለመፈተን እንጂ ሰይጣንን ለማስደሰት አይደለም። ሰይጣንም ቢሆን ያለ እግዚአብሔር ፍቃድ አንዳች ስለማይችል ነው ወደ አምላክ በመቅረብ በእዮብ ላይ መከራ ለማምጣት ጥያቄ ያቀረበው።

ከምስጋና ጋር!!
Jan 5, 2012 ቤሪያ (1,200 ነጥቦች) የተመለሰ
Feb 4, 2013 ቤሪያ ታርሟል
0 ድምጾች
አዎ እግዚአብሔር አማኞችን በመከራ በማሳለፍ እምነታቸውን test ያደርጋል።
1)ክዚህ ጊዜ በሁአላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው( ዘፍ 22፡1-12)
2)እግዚአብሔርም ሰይጣንን እነሆ ለእርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው ነገር ግን በርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ አለው (ኢዮብ 1፡12)
ሰይጣም መልሶ እግዚአብሔርን ቁርበት ስለ ቁርበት ነው ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳብስ በውነት በፊትህ ይሰድብሃል አለው።እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በጅህ ነው አለው (ኢዮብ 2፡4-7)
3)በዚያን ጊዜ ለመክራ አሳልፈው ይሰጡአችሁአል...እስከመጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል (ማቴ 24፡9-14)
4)ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችሁአልና ስለርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም።(ፊልጵ 1፡29)
5)...ይህም ብቻአይደለም ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን...(ሮሜ 5፡3-5)
6)..ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለምስጋና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችሁአል።(1ጴጥ 1፡6-7)
7)...እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወህኒ ሊያስገባችሁ አለው አስር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ፡ እስከ ሞት ድረስ የታመክ ሁን የሕይወትንም አክሊል እ ሰጥሃለሁ።(ራዕይ 2፡10-11)
Jan 24, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Jan 24, 2012 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...