አዎን ይፈትናል...
እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ እስራኤልን በመከራ እንድትገባ አድርጓል። እኛም ብንሆን "ወደ ፈተና አታግባን" ብለን የምንጸልየው እግዚአብሔር ወደ ፈተና ሊያገባን እንደሚችል ስለምናውቅ አይደለምን?? በርግጥ መከራ ውስጥ ሲያስገባን የተለያዩ መሳሪያዎችን ይጠቀማል። ለምሳሌ-- ሰይጣንን (1ኛ ቆሮ 5፤5) ፤
Quote:
መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
ሰዎችን
(በብዛት እስራኤልን በሶርያ ይቀጣ ነበር!!
)፤
ድህነትን፤
Quote:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
2፥6
እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።
በሽታንና ሌሎችንም ይጠቀማል።
እዮብ ላይ መከራ ያመጣው እግዚአብሔር ሲሆን የተጠቀመበት ደግሞ ሰይጣንን ነው። ይህ መከራ የተዘጋጀው የእዮብን ታማኝነት ለመፈተን እንጂ ሰይጣንን ለማስደሰት አይደለም። ሰይጣንም ቢሆን ያለ እግዚአብሔር ፍቃድ አንዳች ስለማይችል ነው ወደ አምላክ በመቅረብ በእዮብ ላይ መከራ ለማምጣት ጥያቄ ያቀረበው።
ከምስጋና ጋር!!