በመጀመሪያ ጥያቄህን ማድነቅ ፈልጋለሁ!! ትክክለኛና ተገቢ ጥያቄ ጠይቀሃል።
ወደ መልሱ ልሂድ፦
ዮሓንስ 10፤8 እንዲህ ይላል፦
Quote:
ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
ይህ ንግግሩ በዋናነት ጌታ ባገለገለው ትውልድ ዘመን ሌሎች በጌታ ስም የመጡ እንደነበሩ ያሳያል። ይህም ከሚከተለው ክፍል ጋር የሚሰማማ ነው።
ሓዋ ሥራ 5፤36-37
Quote:
36 ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።
37 ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።
እነዚህ የተጠቀሱት ሰዎች ብቻ ናቸው ለማለት ባልደፍርም፤ የጌታ ንግግር በዋናነት እነዚህንና ሌሎች መሰል ሰዎችን የሚጠቁም እንጂ የቀድሞ ነብያትን (ሙሴን፣ ዳዊትን፣ ዳንኤልን፣ ኢሳያስንና ሌሎች የብሉይ ኪዳን ነብያትን ወይም የአዲስ ኪዳኑ መጥምቁ ዮሓንስን) የማይጭምር መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል ባይ ነኝ። ምክንያቱም ኢየሱስ እነዚህ ሁሉ ስለእርሱ ትንቢት የተናገሩ መሆናቸውን እንዲህ ሲል መስክሯል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 11፥13
ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤
አመሰግናለሁ!!!