ሁለት ነገር ልንገርህ። 1ኛ/ እግዚአብሔር ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አለመሆኑን እወቅ። እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ ከተፈጠረውም አንዳች ያለእርሱ የሆነ የሌለ መሆኑን ካመንክ አባት እንዳለው ታስብ ዘንድ አይቻልም። ስለዚህ ለፈጣ ፤ ፈጣሪ የለውም።
2/ 1ኛ ቆሮ13፥9
«ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና» እንዳለው የእኛ እውቀት በጣም፣ እጅግ በጣም ትንሽ ነው። ሁሉን የማወቅ ብቃት የለንም። የዚህ ዓለም እውቀት አሁን ካለበት ደረጃ የደረሰው ባንድ ጊዜ አይደለም። በእያንዳንዳችን እጅ ያለችው ትንሿ የሞባይል ስልክ እንኳን ከዛሬ 50 ዓመት በፊት አትታሰብም ነበር። እግዚአብሔር ቢፈቅድና ዓለም ብትኖር ከዛሬ 50 ዓመት በኋላ ደግሞ ዛሬ ላይ ሆነን የማናስባቸው ግኝቶች ሊመጡ ይችላሉ። ስለዚህ ሰው የሚያውቀው፤ የሚያውቀውን ያህል ብቻ ነው።
እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑን እንድናውቅ በተሰጠን እውቀት፤ የምናውቀው ተከፍሎ በተሰጠን ያህል ብቻ ነው። እናም ወንድሜ ወይም እህቴ የጠየቅኸው/ሽው ጥያቄ ሰው ማወቅ ከሚችለው በላይ ብቻ ሳይሆን እንደዚያ ዓይነት ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ ሲቀሩ «እግዚአብሔር የለም» ወደሚል ደረጃ የሚወስዱ ሊሆኑ ይችላሉ። ምክንያቱም የሰው ልጅ እውቀት ምላሽ ሊሰጥባቸው የማይችልባቸው ተመሳሳይ ጥያቄዎች አሉና።
እኛ የምናውቀው ምድርና ሰማይ ከተፈጠረ በኋላ ባለው የፍጥረት ማንነት ላይ ሲሆን ለዚያውም ከሚታወቀው ነገር ከፍለን የምናውቅ ፍጥረቶች ነን። ለእኛ በተሰጠው መጀመሪያ «በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ» ማለቱ ለእግዚአብሔር የሥራ መጀመሪያው ወይም ኅልው ነገርን የማስገኘት መጀመሪያ ወይም መጀመሪያ የሌለው እግዚአብሔር መጀመሪያ እንደሆነ አድርገን ልናስብ አንችልም። እኛ የተሰጠን ማወቅ ከሰማይና የምድር ልደት መነሻ በኋላ ያለውን ነው።
ዘፍ 2፥4
«እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ አምላክ ሰማይንና ምድርን ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው»
ከዚህ ልደት በፊት ስላለው የተነገረን ነገር የለም።