ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 20 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ቤተክርስቲያን በታላቁ መከራ ውስጥ ታልፋለች ወይስ ቀድማ ትነጠቃለች?

Mar 6, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን ማለት አንድ የተወሰነ ቦታ፣ ሕንፃ ወይም ቁሳዊ አካል አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት እኛ በእግዚሐብሔር የምናምን ሰዎት በአንድነት ስንሆን ቤተክርስቲያን እንባላለን፡፡ ስለዚህ እንደ እኔ መረዳት ቤተክርስቲያን ትነጠቃለች ወይም አትነጠቅም የሚለው ነገር የሚወስነው እንደየ ግለሰቡ ይወሰናል ማለት ነው፡፡ ታዲያ ከላይ ለመግለፅ እንደፈለኩት ይህ የኔ አመለካከት ነው፡፡፡

3 መልሶች

+1 ድምጽ
የጌታ ስም ይባረክ። አሜን!!!

ይህ ጥያቄ ብዙ አባቶች የተለያዬ አሳብ ሰጠውበታል። እኔ ግን ባጭሩ ስለማምነው አሳቤን ለመስጠት እፈልጋለሁ። ብሉይ ኪዳን የአዲሱ ኪዳን ጥላ ነው ስለዚህ ከብሉይ ብዙ የተጨበጠ ማለትም እውነት የሆነ ትምህርት እናገኛለን። ለቀረበው ጥያቄ እኔ ያለኝ መልስ ቀድማ እንደ ምትነጠቅ ነው የማምነው። ምን ማስረጃ አለህ? የሚል ጥያቄ ከመቅረቡ በፊት ያለኝን እዚሁ ላክለው። የኖኅና የቤተሰቡ ከውሃ ጥፋት መዳን እንዲሁም ሶዶምንና ጎሞራን ለመምታት ክመጡት ሁለት መላእክት እንዱ ሎጥን ቶሎ በል አንተ ሳትወጣ ምንም ማድረግ ልችልምና አለው። ሰራዬን ልሰራብት እባክህን ፈጠን በል ያለው ይመስለኛል።

የጌታን ምጻት ለማፋጠን ፍቅርና ትህትና ለወንጌላዊያን ይለቀቅላቸው። አሜን!!!
Mar 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 6, 2011 ታርሟል
ቤ/ክ ቀድማ እንደምትነጠቅ ካምኑ ታድያ የማትዮስ ወንጌል ምዕ. 24 ን እንዴተ ይመለከቱታል???
0 ድምጾች
ቤተ ክርስቲያን በመከራ ውስጥ ታልፋለች!!
መጽሐፍ ሲናገር
የዮሐንስ ራእይ 13፡ ላይ
7 ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው። 8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። 9 ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። 10 ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
በዚህ ክፍል እንደምናየው የራእይ መፅሐፍ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ የሚለው ቤተ ክርስትያንን ነው የሚመለከተው
በየማቴዎስ ወንጌል 24፡29
ዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ ሲል
በሐዋርያት ሥራ 2፡17
በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤ 18 ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ። 19 ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤ 20 ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። 21 የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።
በሌላ ስፍራ
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፥2
የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።
ከላይ እንዳየነው ከጌታ ቀን በፊት ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ በማቴ 24 ላይ ደግሞ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም ይለናል
በ2ኛ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡
1 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት። የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ፥ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን።3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና
ጊዜን የሚያመለክቱ ጥቅሶችን ብቻ ነው የምሰጠው ማብራሪያ የማልሰጠው ቃሉ በሃይል ስለሚያወራ ነው አንድ ጨምሬ ልተኛ ግን ብዙ ናቸው
በራእይ 20 ፡
4 ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ አውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ። 5 የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው።
6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
ይላል ከፊተኛው ትንሣኤ በፊት ሌላ ትንሣኤ ማምጣት አንችልም ንጥቀት ደግሞ ትንሣኤን አይቀድምም !! ጌታ ይባርካችሁ ድረ-ገጹንም ያስፋው ብዙ ጠቅሞኛል
Mar 12, 2011 kingdomized (140 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 12, 2011 kingdomized ታርሟል
ሰላም kingdomized
እንደ እኔ እንደኔ አንተ ቤተክርስቲያንና በመከራው ዘመን የሚኖሩትን ቅዱሳን ያምታታሃቸው ይመስለኛል። በራእይ መጽሐፍ በመከራውም ዘመን ቢሆን አንደኛ ወንጌልን በዓለም ሁሉ ለመስበክ የሚታተሙ 144ሺ እስራኤላውያን አሉ ራእይ 7፡1-8። ወዲያው ከቁጥር 9 ጀምሮ ደግሞ በእነዚህ አገልግሎት በመከራው ዘመን ስለ ዳኑትና "እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።" ስለተባሉት ተጽፎአል።

በመከራው ዘመን የዳኑት ቅዱሳን አንዴም ቤተክርስቲያን ተብለው በራእይ አይጠሩም። ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል በራእይ መጽሐፍ እስከ ምዕራፍ 4 በጣም ብዙ ጊዜ ቢጠቀስም፤ ከዚያ በኋላ ግን በመከራው ዘመን ማለትም ከምእራፍ 6 እስከ 19 አንዴም አይጠቀስም። ነገር ግን በምእራፍ 19 ኢየሱስ ከሰማይ ሲመጣ ሚስቱም አብራው እንደምትመጣ ተጽፎአል።

ራእይ 19
7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።

ቤተክርስቲያን የለበሰችውን ልብስ ስንመለከት ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ነው። ይሄም ደግሞ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው ይላል። ማለት ልብሱ ለመላእክት የሚሰጥ ሳይሆን ለቅዱሳን ማለትም ለሚስቱ የተሰጠ ነው። ይልና ወዲያው ክርስቶስ ከሰማይ እንዴት እንደሚመለስ ይገልጻል

ራእይ 19
11 ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።
12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
13 በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።
14 በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

በቁጥር 14 ኢየሱስን የሚከተሉት በሰማይ ያሉት ጭፍራዎች የለበሱትን ልብስ ሲናገር ያንኑ የቤተክርስቲያንን ልብስ ነው። "ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር" ነው የሚለው።

ይህ ብቻ አይደለም ከብሉይ ኪዳን ከእነ ዳንኤል ዘመን ጀምሮ በራእይም መጽሐፍ በጣም ብዙ ቦታ ግልጽ የሚያደርገው ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን እንደማታልፍ ነው። እንዲያውም ከመከራው ዘመን በፊት የራእይ መጽሐፍ ትኩረት ማለትም በመጀመሪዎቹ 5 ምእራፎች በቤተክርስቲያን ላይ ነው። በመከራው ዘመን ግን ማለትም ከምአራፍ 6 ጀምሮ ብዙ የሚናገረው ወይ ስለ እስራኤል ነው ወይም በታላቁ መከራ ስለዳኑ ቅዱሳን ነው። እነዚህ ደግሞ በሰማይ እንኩዋን በዙፋኑ ፊት ከቤተክርስቲያን የተለየ ቦታ ነው ያላቸው።

ብዙ ጊዜ ስለ መጨረሻው ዘመን ትንቢት ሲጠና ትልቁ ችግር የሚመጣው፤ እስራኤልን፣ ቤተክርስቲያንንና በታላቁ መከራ የሚድኑንትን ቅዱሳን የደበላለቅን እንደሆነ ነው። ብሉይ ኪዳንን ጨምሮ በጥንቃቄ ስናጠና ግን የመከራው ዘመን ለቤተክርስቲያን የታሰበም አይደለም። የመከራው ዘመን የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን ነው። የታሰበውም እስራኤልን ወደ ክርስቶስ ለማምጣትና በዓለማውያንን ዓመጻ ለመፍረድ ነው። ክርስቶስን ለተቀበለች ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን ማለፉና የእግዚአብሔርን ቁጣ መቀበሉ ምንም አይነት ትርጉም የለውም። ስለዚህም በራእይ ላይ ለፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ጌታ የገባላትን ተስፋ ስንመለከት "በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ" የሚለው።

ራእይ 3
10 የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።

ስለዚህ የመከራው ሰዓት ማለትም የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን ለቤተክርስቲያን የተዘጋጀ አይደለም። ለዚህ ነው አንተው በጠቀስከው በተሰሎንቄ ላይ "እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንም" የሚለው።

1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
5፥4 እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥
8 እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤
9 እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።
ወንድ ትሆን ሴት አላወቅሁም ይቅር በለኝ ስለትህትናህ ግን ጌታ ይባርክህ በዚህ ዘመን የኔ አይነት አስተሳሰብ እንደ እብድ ያስቆጥራል! በዚህ ጉዳይ ብዙ ስላጠናሁ በቃል ላይ ብቻ አተኩራልሁ ማብራሪያ ስለማይፈልግ በመጀመሪያ እኔ የሰጠኋቸውን ጥቅሶች አንዱንም አልነካሃችውም እኔ ግን ከቆምክባቸው ጥቅሶች ልጀምር ከታች ወደላይ
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
5፥4 እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥
8 እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤
9 እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።
ይህንን የተጠቀምከው የመከራውን ዘመን የእግዚአብሔር ቍጣ ነው ብለህ ስላመንክ ይመስላኛል ነገር ግን መከራው እግዚአብሔር ቍጣ ሳይሆን የዳቢሎስ ነው
የዮሐንስ ራእይ 12
12 ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።...
17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
ክፍሉን በሙሉ አንብበው የእግዚአብሔር ቍጣ በጌታ ቅን ነው የሚገለጠው ያ ደግሞ ለኛ የደህንንነት ቀን ነው
የዮሐንስ ራእይ 6
12 ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥ 13 በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፥ 14 ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፥ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ። 15 የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥ 16 ተራራዎችንና ዓለቶችንም። በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤ 17 ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።
የማቴዎስ ወንጌል 24
29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ 30 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤
የሐዋርያት ሥራ 2
20 ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። 21 የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።
ትንቢተ ኢሳይያስ 13
6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
9 እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል። 10 የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፥ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፥ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3
10 የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል። 11-12 ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤ 13 ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።
ብሉይ ላይ የእግዚአብሔር ቀን ብለህ ብታይ ብዙ ታገኛለህ ለዚህ ነው መጽሐፍ አትደንግጡ ያለው ከዚያበፊት የሚሆን ነገር ስላለ
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2
1-2 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት። የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ፥ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን። 3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና።
ወደ ሁለተኛው ልሂድ ታገሰኝ ብዙ አልፅፍም
የዮሐንስ ራእይ 3
10 የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
በመጀመሪያ ቃሉ እጠብቅሃለሁ እንጂ ከአለም አወጣሃለሁ አይልም ጌታ ቃሉን ስለጠበቁት ሲጸልይ
የዮሐንስ ወንጌል 17
6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ 7 ቃልህንም ጠብቀዋል። የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤
14 እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው። 15 ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።
አንድ ቃል ጨምሬ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ
2ኛ ተሰሎንቄ ሰዎች 1
4 ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን። 5 ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው። 6-7 ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና። 8 እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤
እግዚአብሔር አይለወጥም የመጀመሪዋ ከቤተ ክርስቲያን በምን እንበልጣለን በመከራ ላለማለፍ
ወደ ዕብራውያን 11
36 ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ 37 በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ 38 ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።
የዮሐንስ ራእይ 13
9 ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። 10 ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ”
ትህትና ጎድሎኝ ቢሆን ይቅር በለኝ የእግዚ አብሔር ቃል አስተማሪ አይደለሁም ጌታ ይባርክህ!
ሰላም kingdomized,

ጌታ ይባርክህ። ጾታዬንም በደንብ ገምተሃል ፡)

እኔም እንዳንተው ስለዚህ ነገር ብዙ አጥንቼአለሁ ብዬ ነው የማስበው። ለማናቸውም አንተ እንዳልከው በታላቁ መከራ ሰይጣንም በምድር በቁጣው ቢመጣም፤ በዋናነት ግን ታላቁ መከራ የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን ነው። ይሄን ደግሞ የሚያረጋግጡ ከብሉይም ይሁን ከአዲስ ኪዳን እጅግ ብዙ ማስረጃዎች አሉ።

- የእግዚአብሔር ወይም የበጉ ቁጣ

ራእይ 6፡16-17 ራእይ 11፡18 ራእይ 14፡19 ራእይ 15፡1 እና 7 ራእይ 16፡1 ራእይ 19፡1
1ተሰሎንቄ 1፡9-10 እና 5፡9
ሰፎንያስ 1፡15 እና 18

- የፍርዱ ሰዓት
ራእይ 14፡7 ራእይ 15፡4 ራእይ 16፡5-7 ራእይ 19፡2

- ቅጣት/መዓት
ኢሳ 26፡20-21 ኢሳ 34፡1-3 ኢሳ 24፡20-21

- የፈተና ሰዓት
ራእይ 3፡10

- የያዕቆብ መከራ ዘመን
ኤር 30፡7

- ከአምላክ የሚመጣ ጥፋት
ኢዩ 1፡15

- ጨለማ ቀን
ኢዩ 2፡2 ሶፎንያስ 1፡14-18 አሞጽ 5፡18

ስለዚህ ታላቁ የመከራ ዘመን በምድር ላይ እግዚአብሔር የሚያፈሰው የእርሱ ቁጣ ወይም ፍርድ ነው። የተጠቀሱትንም ጥቅሶች በደንብ ስናነባቸው ይህ ፍርድ ወይም ቁጣ የሚመጣውና የታሰበው በሁለት ሕዝቦች ላይ ነው። አንድ ስለ ኃጢአታቸው ብዛት ምክንያት በአሕዛብ ላይ፤ ሌላው ደግሞ ክርስቶስን ገና ባለመቀበላቸው ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነው።

በራእይ 12 ላይ ሰይጣን በክርስቶስ ምክንያት በ1ኛ ደረጃ የሚያሳድደው ቤተክርስቲያንን ሳይሆን እስራኤልን ነው። እዚህ አንብብ:: ይታይህ የክርስቶስን ወንጌል የምትሰብክ ቤተክርስቲያን ቁጭ ብላ በክርስቶስ ምክንያት እስራኤልን ሰይጣን ሲያሳድድ።

በዚህ መከራ ውስጥ ነው እስራኤል የጌታን ስም የምትጠራው። ያኔ ነው "የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" የሚለው ትንቢት የሚፈጸመው። ጌታም ራሱ "እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።" ብሎ ያስጠነቀቀው እስራኤልን ነው። ማቴ 23፥39

በራእይ መጽሐፍ በመከራው ዘመን ትኩረቱ ከቤተክርስቲያን ወደ እስራኤል ዞሮአል። የሚቀቡት 144ሺ አገልጋዮች ከእስራኤል ናቸው። ከምዕራፍ 11 ጀምሮ ብታነብ ስለ ታቦቱ፣ ስለ መቅደሱ መሰራት፤ ምዕራፍ 12 ደግሞ ስለ እስራኤል መሰደድ ነው የሚያወራው። ምዕራፍ 11 ብትመለከት ስለ ሁለቱ ምስክሮች ይናገራል። እነዚህም የሚሰሩት ምልክት የኤልያስና የሙሴን አይነት ነው። የሚመሰክሩት ግን በኢየሩሳሌም ነው "ጌታቸው የተሰቀለባት ናት" ይለዋል።

ጥያቄው ቤተክርስቲያን እያለች እንዴት በታላቁ መከራ አንደኛ አንዴም አትጠቀስም፤ ሁለተኛ ደግሞ ትኩረቱ ሁሉ ለምን ወደ እስራኤል ሆነ የሚል ነው። ይሄን በቀላሉ ግልጽ የሚያደርግልን የዳንኤል ትንቢት ነው።

ትንቢተ ዳንኤል 9
24 ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።
25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል ጥፋትም ተቀጥሮአል።
27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።

በእስራኤል ሕዝብ ላይ የተደነገገና የተቆረጠ የጊዜ ትንቢት አለ "በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል" ቁ. 24። ይሄውም በመጀመሪያ 69 ሱባኤ(1ሱባኤ=7አመት)፤ ከ69 ሱባኤ በኋላ መሲህ ይገደላል። ከዚያ በ70ኛው ሱባኤ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚነሳበትና የመከራው ዘመን የሚሆንበት ነው። ቤተክርስቲያን እስከ 69 ሱባኤ ውስጥ ተካፋይ አልነበረችም። ምክንያቱም መሲህ የሚገደለው ከ69 ሱባኤ በኋላ ነው። የቤተክርስቲያን ዘመን በ69 ሱባኤና በ70 ሱባኤ መካከል ነው። ቤተክርስቲያን በ69ኙም ሱባኤ ተካፋይና አካል ስላይደለች፤ በሰባኛውም አይደለችም። ሰባኛውም እንደ 69ኙ ሁሉ ለእስራኤል የተቀጠረና የተደነገገ ዘመን ነው።

ቤተክርስቲያን በ69ኛውና በ70ኛው ሱባኤ መካከል የምትገኝ ናት። በብሉይ ኪዳን ይህ የቤተክርስቲያን ዘመን ስለማይታወቅና ትንቢትም ስለላተነገረበት፡ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን ሚስጥር እንደሆነች የሚናገረው። አሕዛብና አይሁድ አብረው በአንድ አካል የሚገኙባት የቤተክርስቲያን ዘመን በብሉይ ኪዳን ሚስጥር ሆኖ ነው የኖረው።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3
5-6 ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።

የራእይ መጽሐፍን አከፋፈል ስንመለከት በሶስት የተከፈለ ነው።

የዮሐንስ ራእይ 1
19 እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።

አንደኛ "ያየኸውን" ይላል፤ ያም ክርስቶስ በክብሩ ተገልጦ ያየውን ነው። ከዚያም "አሁንም ያለውን" ይልና "ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን" ጻፍ ይላል። በራእይ 4፡1 ላይ ደግሞ "ከዚህ በኋላ ይሆን ዘንድ የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ" ይላል።

የዮሐንስ ራእይ 4
1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ። ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።

ስለዚህ እራይ መጽሐፍ አከፋፈሉ፡ ምዕራፍ 1 ዮሐንስ ያየውን የጌታን ክብር፤ ምዕራፍ 2 እና 3 አሁን ያለውን፤ ከምዕራፍ 4 ጀምሮ ደግሞ ከዚህ በኋላ የሚሆነው ነው። ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ሆና የምትጠቀሰው "አሁን ያለውን" በሚባለው ክፍል ውስጥ ነው። ማለትም በቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው። ያም ዘመን በዳንኤል መጽሐፍ በተጻፈው በ69ኛውና በ70ኛው ሱባኤ መካከል ማለትም መሲሁ የሚገደልበት ዘመን ውስጥ ነው። የመከራው ዘመንና የክርስቶስ ተቃዋሚ ዘመን 70ኛው ሱባኤ ውስጥ ነው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን ፕሮግራም ጨርሶ የእስራኤልን ፕሮግራም እንደገና የሚጀምርበት ጊዜ ነው።

ለዚህ ነው በቤተክርስቲያን ፕሮግራም ዘመን እስራኤል የማትጠቀሰው፤ በእስራኤል ፕሮግራም ውስጥ ደግሞ ቤተክርስቲያን የማትጠቀሰው። ሁለቱም ለየቅል ናቸው።

ቅዱሳን ወይም መዳን ወዘተ የሚሉትን የትንቢት ቃላት ሁሉ ግን ወስደን ለቤተክርስቲያን ብቻ የምንሰጥ ከሆነ፤ ነገሩ ድብልቅልቅ ይላል።

አንድ የመጨረሻ ልጨምር። ጳውሎስ በተሰሎንቄ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈሱ አሁንም እንደሚሰራ፤ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ እንዳይገለጥ የሚከለክለው እንዳለ ይናገራል፡፡ ያ የሚከለክለው ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ በበዓለ ሃምሳ በቤተክርስቲያን ስለፈሰሰና ቤተክርስቲያን በምድር እስካለች መንፈሱም በምድር ስለሚኖር፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ሊገለጥ አይችልም። መንፈሱ ግን ቤተክርስቲያንን ይዞ ከምድር የሚሄድበት ሰዓት ይመጣል። ያን ጊዜ ክፉው እንዳይገለጥ የሚከለከለው ምንም የለም።

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
2፥6 በገዛ ራሱ ጊዜም ይገለጥ ዘንድ፥ የሚከለክለውን አሁን ታውቃላችሁ።

የመከራው ዘመን ከመጀመሩ በፊት ቤተክርስቲያን በሰማይ ናት። እነዚህን ለመረዳት ለሎዶቂያ ቤተክርስቲያን የተሰጠውን የተስፋ ቃል በራእይ 3 ላይ ማንበብና፤ የ24ቱ ሽማግሌዎችን ምንነት መረዳት ይበቃል። ስለ 24ቱ ሽማጌሌዎች ቤተክርስቲያንን እንደሚወክሉ እያንዳንዱን የራእይን ጥቅሶች አንድ በአንድ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እዚህ የአስተያየት ቦታ ማንዛዝት እንዳይሆን ትቼዋለሁ።
የተባረክ ወንድሜ ሰላም ሁንልኝ
ስለ 24ቱ ሽማጌሌዎች ቤተክርስቲያንን እንደሚወክሉ እያንዳንዱን የራእይን ጥቅሶች አንድ በአንድ ማየት ይቻላል ብለሃል እውነት ዮሐንስ ራሱን በራእይ አይቶ ጠፋው ነው የምትለኝ ኪኪኪ ላስቅህ በዬ ነው
አሁን ነው የጨመርካት መልሴን እየጻፍኩ ነበር
ስሜን ነግሬህ ልለፍ ኒክ ኔም አልወድም ሔኖክ እባላለሁ ግሪክ ነው የምኖረው ወደ ጉዳዩ በቀጥታ ልግባ አሁንም ለሰጠሁህ ጥቅሶች መልስ አልሰጠህም እንደልማዴ ከታች ወደ ላይ ልውጣልህ
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
2፥6 በገዛ ራሱ ጊዜም ይገለጥ ዘንድ፥ የሚከለክለውን አሁን ታውቃላችሁ።
ለሚለው የሚከለክለው ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ብለህ አምነሃል የሚገርመው የእግዚአብሔር መንፈስ በሁሉም ስፍራ እንደሚኖር ማመንህን አልጠራጠርም ካልሄደ አይገለጥም ነው ያልከኝ እውነት የእግዚአብሔር መንፈስ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ይከለክላልን? አይከለክልም ምክንያቱም የሚልከው ራሱ ነውና
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።
ይላልና
ሁለተኛ
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
7 የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ።
መቼም ቢሆን የእግዚአብሔር መንፈስ ከመንገድ አይወገድም በመከራውም ጊዜ ቢሆን የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አለ ያለሱ ደህንነት የለምና
በተለይ ከዚህ ከቁጥር ጋር ሃሳብህ ይጣረሳል
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
1-2 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት። የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ፥ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን። 3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና።
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ ..ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና የሚለውን ገልብጠህ ኢየሱስ ክርስቶስ ካልመጣ ወደ እርሱ ካልተሰበሰብን ክህደቱ አና የዓመፅ ሰው አይገለጡም ትለኛለህ በፍጹም ማስጠንቀቂያውን ያስተዋልከው አይመስለኝም
ስቀጥል የጌታ ቀን የቁጣ ቀን መሆኑን ተማምነን ሳለ ከመጨረሻው ቀን በፊት አምጥተህ የ 3 ዓመት 1/2 ጭማሪ አድርገህለታል ምክንያቱም የመከራው ዘመን የጌታ ቀን ወይም የቁጣ ቀን ነው ያልከኝ
ትንቢተ ኢሳይያስ 2
12 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል 13 ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥ 14 በረጅሙም ተራራ ሁሉ ላይ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ 15 በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥ 16 በተርሴስም መርከብ ሁሉ ላይ፥ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል። 17 ሰውም ሁሉ ይዋረዳል፥ የሰውም ኵራት ይወድቃል፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል። 18 ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ። 19 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ሰዎች ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ። 20 በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል። 21 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።

በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል ቃሉ

ትንቢተ ዘካርያስ 141
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል፥ ብዝበዛሽንም በውስጥሽ ይካፈላሉ። 2 አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም። 3 እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል። 4 በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል። 5 የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል። 6 በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም። 7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም ሲመሽም ብርሃን ይሆናል። 8 በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል። 9 እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።
በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ....በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።
በመከራው ዘመን ግን
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች

3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና። 4 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።
ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው። ይላል እግዚአብሔር ማስተዋል በነገር ሁሉ ይስጥህ አንተ አንዳልከው በጌታ ቀን የትኛውም ሃይል ከፍ አይለም ይዋረዳል አንጂ ማንም እግዚአብሔር አይሳደብም ደብቁኝ ይላል አንጂ አስካሁን ሃሳብህን የሚቃወሙትን ጥቅሶች አልነካኋቸውም የቆምክበትን አንጂ ሃሳብህን ስልህ ይቅርታ አርግልኝ ትምህርቱን አንተ እንዳልጀመርከው አውቃሉ ቢሆንም ተቀብለህ ይዘሃልና ነው ተመልሼ አገኝሃለሁ እግዚአብሔር ይባርክህ!
ሰላም ወንድሜ ሔኖክ

የጌታ ጸጋ ይብዛልህ። በቃ እኔና አንተ መድረኩን ያዝነው አይደል። ሃሳብን በቅን ልብ ቻሌንጅ መደራረጉ የጎደለንን እንድናይና የበለጠ ቃሉን እንድንመረምር ይረዳልና፤ መልካም ነው እላለሁ።

ራእይ የትንቢት መጽሐፍ ነው። የትንቢት መጽሐፍት ደግሞ ብዙ ምሳሌያዊና ምስጢራዊ ነገሮች ይዘዋል። ራእዩን ያዩት ነብያት ብዙ ጊዜ ስለማይገባቸው የሚያዩት ነገር ይተረጎምላቸዋል። አንዳንዴም አይተረጎመም። ለምሳሌ በራእይ 1 ላይ ሰባቱ መቅረዞች፤ ምንም እንኩዋን ቤተክርስቲያንን የሚያመለክቱ ቢሆንም፤ ለዮሐንስ መተርጎም ነበረበት። ስለዚህ ዮሐንስ የቤተክርስቲያን አካል ስለሆነ ብቻ፤ በራእይ በተለያየ ሁኔታ የተመሰለችውን ቤተክርስቲያንን ወዲያው ያውቃል፤ ራሱን እንዴት ያጣዋል ማለት አይቻልም። በሎጂክ ልክ ነህ፤ "ራሱን እንዴት ያጣዋል" ማለት ትችላለህ፤ በትንቢት መጽሐፍት ግን እንዲህ አይደለም።

በቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ የምትገኘው የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የተገባላት ተስፋ "እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።" ራእይ 3፡21 የሚል ነው። ልብ በል ኢየሱስ ድል ነስቶ በአባቱ ዙፋን የተቀመጠው መቼ ነው? ስለ የትኛውስ ዙፋን ነው የሚያወራው? በሰማይ ስላለው ነው እንጂ በምድር የሺህ አመቱን ወዘተ አይደለም። ምክንያቱም "እንደተቀመጥኩ" ነው የሚለው። ያልፈ የተደረገ ነገርን ነው የሚያወራው። ታዲያ ድል ለምትንሳውም ቤተክርስቲያን የተገባላት ተስፋ ልክ ኢየሱስ ድል ነስቶ በሰማይ በአባቱ ዙፋን እንደተቀመጠ እርሱዋም በዙፋኑ እንደምትቀመጥ ነው።

ከዚህ በኋላ በራእይ 4 ላይ ዮሐንስ ወደ ሰማይ እንዲወጣ ይደረግና፤ በሰማይ የሚሆነውን ይመለከታል። በዚያም 24 ዙፋኖች ይመለከታል።

ራእይ 4
4 በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።

በዙፋኖቹ ላይ የተቅመጡት፤ አንደኛ በቁጥር 24 ናቸው። ሁለተኛ ነጭ ልብስ የለበሱ ናቸው። ሶስተኛ በራሳቸው የወርቅ አክሊል የደፉ ናቸው። አራተኛ ሽማግሌዎች ናቸው።

የመጀመሪያው ጥያቄ እነዚህ 24 ሽማግሌዎች ምንድናቸው? የሚል ነው። ሰዎች ወይስ መላእክት? ሰዎች እንጂ መላእክት ወይም ኪሩቤል ወዘተ እንዳልሆኑ የሚያስረዱ ዋና ዋና መለያዎች አሉ። አንደኛ በራሳቸው የደፉት አክሊል (stephanos) እንጂ ዘውድ አይደለም። አክሊል ደግሞ በቀድሞ በግሪኮችም ባህል (የኦሎምፒክ ማራቶን ወዘተ) ይሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ሁልጊዜ በሆነ አስቸጋሪ ነገር አልፈው ድል ለነሱ የሚሰጥ ነገር ነው እንጂ እንደ ዘውድ የሚወረስ አይደለም። እነዚህ ሽማግሌዎች እንግዲህ ድል ነስተው ያገኙት አክሊል ነው። በሆነ ሁኔታ ድል ነስተው አክሊል የተቀበሉ መላእክትም ይሁኑ ወይም ሌሎች ፍጡሮች በመጽሐፍ ቅዱስ የሉም። ለቤተክርስቲያን ግን የተለያዩ አይነት የድል አክሊሎች ቃል ተገብቶላታ። የጽድቅ አክሊል 2ኛ ጢሞ 4፡8፣ የክብርን አክሊል 1ኛ ጴጥ 5፡4፣ የሕይወት አክሊል ያዕ 1፡12 እና ራእይ 2፡10። ራእይ 3፡11 ደግሞ "ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ" ይላል። ስለዚህ አክሊል በተወሰነ ተግዳሮት ውስጥ አልፈው ያንን ድል ላደረጉ የሚሰጥ ሲሆን ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ አንዴም ለመላእክት የተነገረ አይደለም። ለቤተክርስቲያን ግን ብዙ ጊዜ ተስፋ ተገብቶላታል።

ሌላው ሽማግሌዎቹ የለበሱት ነጭ ልብስ ነው። በራእይ መጽሐፍ ነጭ ልብስ በበጉ ደም ልብሳቸውን ላነጹ ለሰዎች እንጂ ለመላእክት የሚሰጥ አይደለም።

ሶስተኛ በዙፋን ላይ መቀመጣቸው ነው። ለማንም ፍጡር፤ መላእክትን ጨምሮ ዙፋን ላይ የመቀመጥ ተስፋ አልተገባለትም። በየትኛውም ቦት መጽሐፍ ቅዱስ በዙፋን የሚቀመጡ መላእክትን ወይም ኪሩቤልን አንመለከትም። ከላይ እንደተናገርኩኝ በራእይ 3፡21 ላይ ለቤተክርስቲያን ብቻ ነው፡ ልክ ኢየሱስ ድል አድርጎ በአባቱ በሰማይ ዙፋን እንደተቀመጠ፡ ቤተክርስቲያንም በዙፋኑ እንደምትቀመጥ ተስፋ የተገባላት "እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።" የሰማይ ዙፋን ቃል የተገባላት ቤተክርስቲያን ብቻ ናት።

አራተኛ ሽማግሌ የሚለው ቃል ነው። ሽማግሌዎች የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ወይ ለብሉይ ኪዳን የእስራኤል ማሕበር ሽማግሌዎች ወይም በአዲስ ኪዳን ለቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች እንጂ ለመላእክት ወዘተ የትም ተጠቅሶ አያውቅም። ስለዚህ እነዚህ ደግሞ በበጉ ደም ልብሳቸው የነጻና የድል አክሊል የደፉ፤ በዙፋን ላይም የተቀመጡ ሽማግሌዎች ስለሆኑ፤ የሚያመለክቱት ቤተክርስቲያንን ብቻ ነው።

በመጨረሻም 24 መሆናቸው ነው። 24 ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ የካሕናት ቁጥር ነው። ልክ 12 እንደ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች የእስራኤል ቁጥር እንደሆነ ሁሉ፤ 24 ቁጥር የካህናት የአገልግሎት ምድብና ቁጥር ነው። 1ኛ ዜና 24፡1-19 ብትመለከት፤ ካህናት በ24 ምድብ ተከፍለው ነው የሚያገለግሉት። ሉቃስ 1 ላይ የኤልሳቤጥ ባል ዘካርያስም ከ24ቱ የካህናት ምድብ አንዱ ከሆነው ከአብያ ክፍል ሰለሆነ "ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ" ሉቃስ 1፡5 ይለዋል። ሉቃስ 1፡8 ደግሞ "እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል"። ይሄ የተራ ክፍል የሚለው ከ24 አንዱ ወገን ተረኛ መሆኑን ለማመልከት ነው። ስለዚህ 24 ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ የካህናት ቁጥር ነው። ዮሐንስ በራእይ 1፡5-6 ሲጽፍ "ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን" ይላል። ምንም እንኳን እስራኤልም በምድር በአሕዛብ መካከል ለክህነት የተጠራች ቢሆንም፤ በበጉ ደም ተዋጅታ ነጭ ልብስ ለብሳ ለክህነት አገልግሎት የተጠራች ግን ቤተክርስቲያን ብቻ ነች።

ወንድሜ ሔኖክ ከአንድ ጥቅስ በስተቀር፤ በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን የሚገኙ በጣም ብዙ ጥቅሶችና የትንቢት ቃሎች በሙሉ የሚመሰክሩትና የሚጠቁሙት፤ ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን እንደማታልፍ ነው። ነገር ግን አንድ ጥቅስ ግራ የሚያጋባና ተቃራኒውን የሚናገር የሚመስል እንዳለ እኔም አልክድም፡፡ ይሄውም አንተም ደጋግመህ የምታነሳው 2ኛ ተሰ 2 ላይ ያለው ነው። ከዚህ ውጪ ግን የራእይንም መጽሐፍም ጨምሮ፤ ከብሉይ እስከ አዲስ መጻሕፍት አንድም ቦታ ቤተክርስቲያን በታላቁ መከራ እንደምታልፍ የሚናገር የለም። "በበጉ የቁጣ ቀን" ሚስቱ ማለፏ ጨርሶ ምንም ትርጉም የለውምና። የተሰሎንቄውም ቢሆን፤ ብዙ የሚያከራክር ነው። አንደኛ በ1ኛ ተሰሎንቄ ጳውሎስ ራሱ "እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው" እንነጠቃለን እያለ ይናገርና፤ በ2ኛ ተሰሎንቄ ደግሞ ገና ነው፤ ገና የአመጻ ልጅ መገለጥ አለበት ወዘተ ይላል። ማለትም እርሱ ሕያው ሆኖ ሊቆይ የማይችልበትን ሁኔታ ይጽፋል። እርሱ ራሱ በመከራው ዘመን እንደሚያልፍ አምኖ ነበር አይድለም? አምኖ ከነበር፤ ትምህርቱና ጽሑፉ ሁሉ በመከራው ዘመን ላይ ማተኮር ነበረበት፤ ራሱ እንደሚያልፍ ካላመነ ደግሞ እኛ ሕያውና ሆነን የምንቀር እያለ መጻፍ አልነበረበትም። ሌላው በ1ኛ ተሰሎንቄ አንቀላፍተው ስላሉት የተሰሎንቄን አማኞች ሊያጽናና ነው የጻፈው። እነርሱም ተነስተው እንደሚነጠቁና፤ በሕይወት ያሉት እንደማይቀድሟቸው ጽፎአል። ነገር ግን በሕይወት ያሉት የመከራውን ዘመን የሚያልፉ ከሆነ፤ አንቀላፍተው ያሉቱ ንጥቀት አመለጣቸው ብለው ባላዘኑም ነበር። እንዲያውም፤ የመከራውን ዘመን እንኳን አላዩት፤ ታድለው ማለት ይገባቸው ነበር።

ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን የምታልፍ ቢሆንማ፤ ለቤተክርስቲያን የተጻፉት ብዙ ደብዳቤዎች በአብዛኛዎቹ እንደ እስራኤል የነብያት መጻሕፍት በታላቁ መከራ ላይ ባተኮሩ ነበር። የአዲስ ኪዳን መልእክቶች ግን አንዳቸውም ያንን ትኩረት ሰጥተው እንደ ዋና ነገር ቤተክርስቲያንን ለታላቁ መከራ እንድትዘጋጅ አላደረጉም።

ይህም ብቻ አይደለም። ራሱ ጌታ በራእይ መጽሐፍ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት ለእያንዳንዳቸው ድካማቸውን ያለባቸውንና ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ችግር ሁሉ ሲዘረዝርና ሲያስጠነቅቅ፤ አንዳቸውንም በታላቁ መከራ ማለፍ ስለሚገባቸውና እንዴት ሊወጡት እንደሚችሉ አልጠቀሰም። ታላቁ መከራ በራእይ መጽሐፍ እጅግ ትልቅ ስፍራ ተሰጥቶት ሳለ (14 ምዕራፎች) አንዳቸውም አብያተ ክርስቲያናት ከጌታ ለዚያ ጊዜ እንዲዘጋጁ ማስጠንቀቂያ አልተሰጣቸውም። በቤተክርስቲያን ካሉ የተለያዩ የትምህርት ጉደፈቶች፤ ድካሞች፤ ቅድስና ማጣት ወዘተ ጎን እንኳን ተጠቅሶ ማስጠንቀቂያ አልተሰጣቸውም። ለምን ቢባል መልሱ አጭር ነው? እነርሱን ስለማይመለከት ነው።

እንደሚገባኝ የአንተ አመለካከትና መረዳት የተመሰረተው በአንድ ጥቅስ ነው። ይሄውም በ2ኛ ተሰሎንቄ ላይ ባለው፤ ከዚያ ውጪ የጠቀስካቸው በአባዛኛዎቹ እስራኤልን የሚመለከቱና በቀጥታ ቤተክርስቲያን በታላቁ መከራ እንደምታልፍ የማይናገሩ ናቸው። እኔ ግን ከብሉይና ከአዲስ፤ ከራእይም በሙሉ ለማሳየት የምሞክረው፤ "የበጉ ቁጣ" ቀን ለአመጸኞች እንጂ ለሚስቱ የታሰበ አይደለም እያልኩ ነው።

እንዲያውም በዚያው በ2ኛ ተሰሎንቄ ሲናገር፤ ይሄ የክርስቶስ ተቃዋሚና የመከራው ዘመን የሚመጣው "ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ" እንዲሁም "በእውነት ላላመኑ" ነው እንጂ ታዝዘው ክርስቶስን ለተቀበሉ አይደለም።

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2
9-10 ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።
11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።
ሰላም እንዴት አለህ? የኔ ወንድም የዘገየሁት እሁድ ሆኖብኝ ነው ንግግራችን በአማርኛ ባይሆን እንዴት ደስ ባለኝ መፃፍ በዙ አልችልምና ለዚህ ነው ጥቅስ የማበዛው ኮፒ እያረኩ በአንድ ጥቅስ ብቻ እማምን እንዲመስለህ ስላረኩህ ይቅር በላኝ ስለ 2 ተሰ 2 “ግራ የሚያጋባና ተቃራኒውን የሚናገር የሚመስል ” ስላልከው በጣም ተገረሜለሁ “ይላል” ባትልም ይመስላል ማለትህ እራሱ ከብዙ ሰዎች የተለየህ ያደርግሃል ለዚህም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ለሰጠሁህ ጥቅሶች እስካሁን መልስ አትሰጠኝም የእምነትህን ትንታኔ ብቻ ነው ያደረከው በተለይ የጌታን ቀን 3 ዓመት ½ በትንሹ አሳድገሃል ብዬ ከስሼሀለሁ መልስ አልሰጠህም ስለጌታ ቀን ባህሪ የሰጠሁህን አንድም መልስ አልሰጠህም ለምሳሌ
በኢሳ 2፡17 “ሰውም ሁሉ ይዋረዳል፥ የሰውም ኵራት ይወድቃል፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል”
ዘካ 14፡ 4 በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ
ዘካ 14፡ 7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።
ዘካ 14፡ 9 እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።
እነዚህ ሁሉ የመከራውን ጊዜ አይገልጡም በዚያ ጊዜ የአውሬው ዘመን ራሱን ከአምላክ በላይ የሚያደርግበት ዘመን ነው የአስማትና የጣጎት ዘመን ነው የክርስቶስን ምስክሮችን የሚዋጋበት ዘመን ነው በድንቅ ታአምራቱ ወንጌልን ያልተቀበሉትን ለፍርድ ያሚሰብበት ነው ወዘተ
በጣም ከገረመኝ መልስህ “በራእይ 12 ላይ ሰይጣን በክርስቶስ ምክንያት በ1ኛ ደረጃ የሚያሳድደው ቤተክርስቲያንን ሳይሆን እስራኤልን ነው” አልከኝ የክርስቶስን ተቃዋሚ መንፈስ አላስተዋልከውም
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2
22 ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
ሃሰተኛውን እንዳንቀበል ማስጠንቀቂያ ያለብን እኛ ነን በክርስቶስ ለማያምኑት እይደለም በራእይ 12 ላይ ያሉት እኮ የክርስቶስን ምስክር የያዙ ናቸው
የማቴዎስ ወንጌል 24
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። 5 ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
የዮሐንስ ራእይ 12
17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤

ስለ 24 ሽማግሌዎች አመስግንሃለሁ ቀልዴን ቢሆንም ጊዜ ወስደህ የሚረባኝን ጽፈሃልና
ወደዋና ነጥቤ ልሄድ ስለ ጌታቀን የማወራህ ጊዜ ጠቋሚ ስለሆነ ነው እንጄ ጥቅስ አጥቼ አይደለም እምነቴን በአንድ ቃል ላይ መስርቼ አይደለም በል ወጋብህን ታጠቅና ለመልስ ተዘጋጅ!

አንደኛ ቤተክርስትያን ከመከራው በፊት ለመነጠቅ ጌታ ሁለት ጊዜ መምጣት አለበት አንድ በስውር አንድ በግልጽ ይህ ደግሞ በቃሉ ውስጥ የተደገፋ ሃሳብ አይደልም ጌታ በድንገት እንጂ ተደብቆ አይመጣም

የተባረከውን ተስፋችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የክብር መገለጥ ( the glorious appearing) እንጂ የስውር አይደለም
ወደ ቲቶ 2
11 ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ 12-13 ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
ዕረፍታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በክብር መገለጥ እንጂ በስውር አይደለም
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1
5 ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው። 6-7 ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።

ቤተክርስትያን ከመከራው በፊት ለመነጠቅ ትንሳኤ ለቅዱሳን ብቻ ሁለት ጊዜ መሆን አለበት አንድ ከመከራው በፊ ለሚሞቱት ሁለት በመከራ ወስጥ ለሚሞቱት ይህ ደግሞ በቃሉ ውስጥ የተደገፋ ሃሳብ አይደልም

አንደኛ ንጥቀት ትንሳኤን አይቀድምም (በዚህ የምንስማማ ይመስለኛል)
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4
16 በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ 17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
52 መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

ሁለተኛ ትንሳኤ ጌታ ሲመጣ-ከሰማይ ሲወርድ ነው (በዚህ የምንስማማ ይመስለኛል)
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4
16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

ሶስተኛ ሙታን እንዲነሱ መለከት ይነፋል (በዚህ የምንስ ማማየመስለኛል)
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4
16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
52 መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

አራተኛ መለከቱ የመጨረሻ መለከት(የኋለኛው መለከት) ነው (በዚህ አንስማማም) ምክንያቱም ከመከራው በፊት ቤተ ክርስትያን ከተነጠቅች ከመጨረሻው መለከት በኋላ ሌላ 7 መለከቶች ይነፋሉ ብለህ ለማመን ስለምትገደድ
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
51-52 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

አምስት ትንሳኤ እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል የመጀመሪያ ሁለተኛ አያለ...(በዚህ አንስማማም) ምክንያቱም ከመከራው በፊት ቤተ ክርስትያን ከተነጠቅች የመጀመሪያውን ትንሳኤ ሁለተኛ ነው ብለህ ለማመን ስለምትገደድ
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
የዮሐንስ ራእይ 20
5 የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው። 6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።

ስድስተኛ ጌታ ከመጣ በኋላ ሁለተኛ እድል የለም(በዚህ አንስማማም) ምክንያቱም ጌታ መጥቶ በስውር ከወሰዳት እና የቀረ 3 ዓመት ½ ካለ በመከራ ውስጥ የሚድኑ ስላሉ ሁለታኛ እድል ያገኙ ይኖሩበታል ብለህ ለማመን ስለምትገደድ
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3
10 የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
የዮሐንስ ራእይ 3
3 እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።
የዮሐንስ ራእይ 16
15 እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።
መቼም ቤተ ክርስቲያንን ምዕራፍ 4 ላይ መጥቶ ወስዷታል ብለህ ችል እንደማትለው አምናለሁ ጌታ እንደ ሌባ ሁለት ጊዜ አይመጣም እና
የሉቃስ ወንጌል 21
34 ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ 35 በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና። 36 እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ።
የሉቃስ ወንጌል 17
26 በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። 27 ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ። 28 እንዲሁ በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤ 29 ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ። 30 የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።
ያነሳኋችውን ነጥቦች ልብ በል ክርስቶስ አንዴ ብቻ ይገለጣል የቅዱሳን ትንሳኤ አንዴ ብቻ ይሆናል ከመጨረሻው መለከት በኋላ ሌላ መለከት አይነፋም ሁለተኛ እድል የለም የሚሉ ናቸው እንዳላበዛብህ በዚህ ላብቃ ላሁኑ ላነሳኋችው ሃሳቦች መልስ እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ እግዚአብሔር ይባርክህ
ሰላም ወንድሜ ሔኖክ

እስከ አሁን በአብዛኛው ስትጠቅስልኝ የነበሩት የጌታን ቀን የሚያሳዩ ጥቅሶች፤ አንዳቸውም ቤተክርስቲያን በዚያን ዘመን ታልፋለች ስለማይሉ ነው፤ አስተያየት ያልሰጠሁበት። ለምሳሌ ከኢሳያስና ከዘካርያስ የጠቀስካቸው፡ በጥቅሉ ስለ ታላቁ መከራ የሚናገሩ እንጂ አንድም ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን እንደምታልፍ የሚያሳዩ አይደሉም። ለእንደነዚህ አይነት ጥቅሶች ሁሉ መልስ እንስጥ ከተባለ፤ መጨረሻ የለውም። ማተኮር ያለብን፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተለይ በራእይ መጽሐፍ በእርግጥ የት የት ቦታዎች ናቸው፤ ምንም በማያሻማ መንገድ ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን እንደምታልፍ የሚናገረው? የሚለው ላይ ነው።

በመጨረሻው አስተያየትህ ላይ ያሉትን ገና አልመረመርኩዋቸውም፤ ሆኖም እንዳየሁት መከራከሪያህ የተመሰረተው፤ በእርግጥና በቀጥታ ቤተክርስቲያን በመከራው ዘመን ታልፋለች ብሎ ከሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይልቅ፤ እንዲህ ካልሆነማ ይህ እንዴት ሊሆን ነው? በሚል ላይ ነው። ማለትም ስንት ትንሳኤ ታዲያ ሊኖር ነው? ስንት ጊዜ ታዲያ ጌታ ሊመጣ ነው? ወዘተ በሚል ነው እንጂ በቀጥታ ቤተክርስቲያንና የመከራውን ዘመን በሚያገናኝ ጥቅስ አይደለም።

እኔ ግን በቀጥታ ከራእይም ስለሽማግሌዎቹና ስለ ሚስቱ ሰርግ፤ በመከራው ዘመን ውስጥ ቤተክርስቲያን አለመጠቀስዋን፤ በብሉይም በአዲስም የመከራው ዘመን እውነትን ላለማመን ለፈለጉ አሕዝብና ክርስቶስን ላልተቀበለች እስራኤል የሚመጣ ቅጣትና የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሆነ ወዘተ የጻፍኩልህን ሁሉ አንዱንም አልመለስክልኝም።

ስለዚህ እዚህ ላይ ትንሽ እረፍት ብንወስድና አንተም ስለ ራስህ መከራከሪያ ነጥብ ሳይሆን፤ እኔ ስለ ጻፍኳቸው የመከራከሪያ ነጥቦች ጊዜ ወስደህ ብታይ፤ እኔም ደግሞ አንተ ስለጻፍካቸው ነጥቦች ጊዜ ወስጄ ባይ መልካም ነው እላለሁ። የራሳችንን የመከራከሪያ ነጥቦች ላይ ብቻ የምናተኩር ከሆነ ምንም አንማርምና። ከዚህ በተለየ ግን አንተም ሆንክ እኔ፤ በደንብ ሊያሳምን የሚችል አንዳች ሃሳብና ማጠናከሪያ ቢሆረን፤ በዚሁ መጻጻፍ እንችላለን።

በተለይ በትንቢት ጥናት ትልቁ ችግር የሚነሳው፤ የእስራኤልን ትንቢትና የቤተክርስቲያንን ከመቀላቀል ነውና በዚህም እንድታስብበት አሳስብሃለሁ።

የጌታ ጸጋ ይብዛልህ።
ተባረክልኝ ለማሳሰቢያህ ነገር ግን ሃሳብህን በሚገባ እያየሁ ነው የምጽፍልህ በራእይ መጽሐፍ ቤተክርስትያን ከምዕራፍ 4 በኋላ የለችም ነው የምትለው ቤተ ክርስትያን የሚለው ቃል እንጂ ቤተ ክርስትያን አለች ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል አጠቃቀም በራእይ መጽሃፍ ላይ በሙሉ ተመልከት አጥቢያን ለመለየት እንጂ አማኞችን ቅዱሳንን በሙሉ ለመግለጥ የዋለ አይደለም አይውልም
የዮሐንስ ራእይ 2
1 በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ
የዮሐንስ ራእይ 2
8 በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ።
የዮሐንስ ራእይ 2
18 በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ።
የዮሐንስ ራእይ 2
12 በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ
የዮሐንስ ራእይ 3
1 በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ።
የዮሐንስ ራእይ 3
7 በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ።
የዮሐንስ ራእይ 3
14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ።
ስለ ሀያ አራት ሽማግሌዎች ዮሐንስ ወደ ሰማይ እንደወጣ አያቸው እንጂ ወደፊት የሚሆነው ላይ ብቻ አይደለም ያያቸው የተነጠቁ ሊሆኑ አይችልም
የዮሐንስ ራእይ 4
1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ። ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ። 2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤ 3 ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ። 4 በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
ይሁንና አርጊዩመንት ፍሮም ሳይለንስ ይሉታል ነጮቹ መጽሐፍ ቅዱስ ታልፋለች አይልም በለህ አታልፍም ብለህ የደመደምከውን ያህል አታልፍም አይልም እና ታልፋለች ልል እንደምትችል አትርሳ ይሁንንና
የማቴዎስ ወንጌል 24
9 በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። 10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ 11 ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ 12 ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። 13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። 14 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
የማቴዎስ ወንጌል 28
19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
ይላልና ቃሉ እስከመጨረሻው ጸንቼ የመንግሥቱን ወንጌል እንድንስብክ ለጌታም ከሚሰውት አንዱ እንድሆን ጌታ ይርዳኝ ላንተም እግዚአብሔር የቃሉን ደጆች እንዲከትልህ ጸሎቴ ነው በል በዚህ ይብቃኝ ኣስተያየቴንም እንዳነበብክ አረጋግጬ አነሳለሁ ቃሉን መነጋገር እንጂ በክርክር የመርታት እቅድ የለኝም እና ሰላም ሁንልኝ
–1 ድምጽ
በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን ማለት አንድ የተወሰነ ቦታ፣ ሕንፃ ወይም ቁሳዊ አካል አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት እኛ በእግዚሐብሔር የምናምን ሰዎት በአንድነት ስንሆን ቤተክርስቲያን እንባላለን፡፡ ስለዚህ እንደ እኔ መረዳት ቤተክርስቲያን ትነጠቃለች ወይም አትነጠቅም የሚለው ነገር የሚወስነው እንደየ ግለሰቡ ይወሰናል ማለት ነው፡፡ ታዲያ ከላይ ለመግለፅ እንደፈለኩት ይህ የኔ አመለካከት ነው፡፡፡
Apr 5, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...