ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ ?

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ነው ወይስ አማላጅ ? እንዴት ?
Mar 6, 2011 መንፈሳዊ ፍቅር (140 ነጥቦች) የተጠየቀ
Mar 10, 2011 ፍቅር ታርሟል
በሁሉም አካላት ተቀባይነት ያለውና አውነተኛ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል እንመልከት፡እንግዲህ ስለምልጃ ከመናገሬ በፊት ከትርጉሙ እጀምራለሁ፡ ምልጃ ማለት ማሰታረቅ ስለሌላ አካል መለመን ማስማማት ማለት ነው፡ አንዳንድ ሰዎች የኢየሱስን አማላጅነት ላለመቀበል ሲጣጣሩና መጽሐፍ ቅዱስን ለማጋጨት ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በምድር ላይ እያለ አማልዷል ካረገ በኋላ ግን አያማልድም ይላሉ፡ የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል እንመልከት፡
በስጋው ወራት የክርስቶስ ምልጃ
ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረ ሰዓት ምልጃ ፈጽሟል ለምሳሌ በዮሐ17 ጌታ ለደቀመዛሙርቱና ከቃላቸው የተነሳ ለሚያምኑ ሁሉ አንድ እንዲሆኑና በዓለምም እንዲጠብቃቸው ጸልዮል እንደዚሁም ደግሞ በሉቃስ 22፡31-33 ጌታም «ስምዖን ስምዖን ሆይ እነሆ ሰይጣን እንደስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንደይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ»፡ ይህም ብቻ ሳይሆን እዛው ሉቃስ 23፡34 «አባት ሆይ የሚያደረጉትን አያወቁምና ይቅር በላቸው» ሲል ለሚሰቅሉት ጸልዮል፡ አንግዲህ የዕብራዊያን ጸሐፊ ስለምልጃውና ስለጸሎቱ ሲናገር እንዲህ ይላል ዕብ 7፡5 «እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ጸሎቱ ተሰማለት»ይላል፡፡
ከእርገት በኋላ የክርስቶስ ምልጃ
እንግዲህ ከላይ እንዳየነው ጌታ በምድረር ላይ ጸሎትንና ምልጃን አቅርቧል፡ የዕብራዊያን ጸሐፊ ኢየሱስ በሰማይ በሰው እጅ ባልተሰራችውና በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው ይለናል ዕብ 8፣1-2፡ ለሰማያዊው መቅደስና አውነተኛ ድንኳን ምሳሌና ጥላ በነበረችው ውስጥ ሊቀ ካህን በዓመት አንድ ጊዜ መሰዋዕት እያቀረበ ህዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ያሰታርቅ ነበር ዕብ 9 በሙሉ ፡ ነገር ግን ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን ሆኖ በሰው እጅ ወደተሰራችው ሳይሆን ወደ እውነተኛይቱ ድንኳን በእግዚአብሔር ፊት አሁን ስለአኛ ይታይልን ዘንድ ወደ እርሷ ገባ ይላል ዕብ 9፣24 አሁን የሚለው ቃል ማስተዋል አለብን ምክኒያቱም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ስለአኛ የሚታይልን ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ሮሜ 8፣34 ኢየሱስ ካረገ በኋላ ስለምልጃው ሲናገ ር፡ «የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»፡፡ አዚህ ላይ ማሰተማል ያለብን ነገር ምንድን ነው ፣የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሐላፊ ግዜን ሲሆን ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ፣ የሚለው ግን አሁንን ነው የሚያመለከክተው፣ በዚህም ላይ ጨምሮ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ይላል እንጅ ማርያም ወይንም ሌሎች ናቸው አይልም፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ለኤርሚያስ አዲስና የተሻለ ኪዳን አንደሚገባ ተናገሯል ኤር 31፣31-34 ዕብ 8፣6-13ኤርሚያስ 3፣16 ስለዚህም እየሱስ የአዲስ ኪዳን ዋስ ሆኗል ዕብ7፣22፡ ዕብራዊያን 7፣25 «ስለእነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህም ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል»፡ አሁንም ሊያማልድ እና ዘወትር የሚሉትን ቃላት ማሰተዋል ያለብን ይመስለኛል፡፡ ልክ ዕብ 9፣24 አሁን ስለእኛ ይታያል እንዳለው ሁሉ በአብ ዘንድ ጠበቃችንም ኢየሱሰ ብቻ እንደሆነ ዮሐንስ በ1ኛ መልዕክቱ 2፣1-2«ልጆቼ ሆይ ሀጢአትን እንዳታደረርጉ ይህን እጽፍላቲኋ ማንም ሀጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው» ይላል፡፡
ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ መካከለኛ ነው መንገድ ነው በር ነው
በ1ኛ ጢሞቲዮስ 2፣5 «አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ አርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»፡ ስለዚህ ወገኔ መካከለኛው ኢየሱስ ብቻ ነው ጳውሎስም የኢየሱስን መካከለኛነት ሲያበራራ እንዲህ ይላል ኤፌ 2፣15-16«እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሀደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ህግ ሽሮ በመካከል የለውን የጥል ግድግዳን በስጋው ያፈረሰ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው»፡፡
አንግዲህ ኢየሱስ ሲናገር በዮሐ 14፣6 «እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም» የዕብራዊያን ጸሐፊ ደግሞ ይህንን ሲደግመው አናያለን ዕብ 7፣25…ስለዚህም ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል»፣ሮሜ 3፣24« …በኢየሱስ ክርሰስቶስም በሆነው በዛነት እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ» በሏል ጌታም በዮሐ 10፣9« በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል ይገባል ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል» ሐዋ 4፣12« መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና»
ወስብሐት ለእግዚአበሔር
ዝናቡ zinabu2004@gmail.com
የ እግዚያብሄር ስላም ለሁላችንም ይሁን!!

ወንድማዊ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ

በኔ እምነት ይህ እርእስት ወሳኝ ነዉ። በጣም ወሳኝ። ክርስቲያኖችን ክርስቲያን ያሰኜን በ እርግጥም ክርስቲያን የተባልንለትን የጌታችን የመደሃኒታችን እና የአምላካችንን የእየሱስ ክርስቶስንን ማንነት ጠንቅቆ ክማወቅ የሚገኝም ነዉ። እኔ የሚገባኝን ለማክፈል እሞክራልሁ።

በመጀመሪያ ሁላችንም አንድ ዘላለማዊ አምላክ እንዳለን ማወቅ አለብን። የትእዛዞች ሁሉ መጀመሪያ ነዉና።

ዘጸ 20፡ 1 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።

ዘጸ 20፡ 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
ትንቢተ ሆሴዕ 14
1እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።

ለግዜው የማስታውሳቸው እነዚህ ብቻ በመሆናቸዉ እንጂ ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሶች እንደሚኖሩ አልጠራጠርም። አዎ አንድ አምላክ እግዚአብሄር ብቻ አሜን!!

ታድያ ክርስቶስ ማን ነው? ይህንን መ/ቅ እንዴት ይመልስዋል ስንል፡ ስለ ጌታችንና መድሃኒታችን እንዲሁም አምላካችን ክተባሉት ጥቂቶቹን አንን እንካችሁ

ትንቢተ ኢሳይያስ
9፥6" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"(ህያል አምላክ የዘላለም አባት)አሜን!!

ወደ ሮሜ ሰዎች
9፡ 5 "አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።"(ለዘላለም የተባረከ አምላክ)
ወደ ቲቶ 2 11 "ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔርጸጋ ተገልጦአልና፤
12-13 ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤" (የአምላካችንና የመደህኒታችን)
ወደ ዕብራውያን 1፡ 8 ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። (አምላክ ሆይ)

ስለ ጌታችን መድሃኒታችን እና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ብዙ ጥቅሶች እንደሚኖሩ አምናለሁ ሆኖም ለግዜው ያገኝሁዋቸዉ እንዚህ በቂ ናቸዉ ብየ
አምናለሁ። አዎ ጌታችን የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው የአማልክት ሁሉ አምላክ ነው። አሜን!!

ለመሆኑ እሱስ የአለም መደሃኒት ክርስቶስ እየሱስ ስለራሱ ማንነት ምን አለ?

የማቴዎስ ወንጌል 16፡13 ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
14 እርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
15 እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

አዎ ጴጥሮስ እግዚአብሄር እንደገለጸለት እና እንደመለሰዉም እሱ "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ" አዎ እግዚአብሄር ነዉ። ምን አልባት እሱ የ እግዚያብሄር ልጅ እንጂ አምላክ እግዚያብሄር አደልም የሚሉ ትክክል ኖት ቢሆንም ክላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች አልቀበልም ማለት ይሆናል። በመሰረቱ በስው ስዉኛ ወይም በ እግዚያብሄር ህግ ሁሉም የሚወልደዉ መሰሉን ነው። እኛ የሰው ልጆች የምንወልደዉ መሰላችንን ሰው ነው። በግም በግ ሌላዉም እንደዛው ስለዚህ "የህያው እግዚአቢሄር ልጅ "ም እግዚያቢሄር ነው። አሜን!!

ማጠቃለያ
እዚህ ላይ በእግዚያብሄር ፊት ወንድሜ የሆኑት ዝናቡ ክላይ ያሉትን የጌታዬን ኣና የአዳኜን የአምላኬን ክብር እላይ ባሉት ጥቅሶች እንዳሳየሁት እንጂ "ጠበቃ ዋስ እና አማላጅ" በሚሉት ለመተካት አልደፍርም አልተካምም። አለዚያ ደግሞ ሰለክርስቶስ አምላክንት የተጠቀሱትን አንቀበልም ይበሉኝ። ምክነያቱም ክላይ እንዳሳየሆት አንድ አምላክ በቻ አለን በዚሂም እንደምንስማማ አቃለሁ። ጌታችንና መደሃኒታችንን አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ለመሆኑ እጅግ ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ክላይ የተጠቀሱትም በቂ ናቸው። በዚህም እንደምንግባባ አምናልሁ።
ስለዚህ አንድ አምላክ ብቻ? አዎ። ጌታችንም እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው ?አዎ ነዉ።

1ኛ.ጌታችን አማላጅ/ጠበቃ/ዋስ ነዉ ለሚለው ? አዎ የሚሉ ከሆነ ክማ ነው የሚያማልደን?አምላክም እሱ ዋስ ጠበቃ እሱ

2ኛ. ክማን ነው የሚያማልደን? ላልኩት መልስዎ ክ አብ ነው። እንዳሉ ልገምት እና ስለዚሀ በ እርሶ አመለካክት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ከአብ/ክ አምላክ ይማለድልና/ይለምንልናል። ጥሩ። አሁን ደሞ ክላይ በተጠቀሱት ማረጋግጫ ጥቅሶቸ እንዳየነው ጌታ እይሱስ ክርስቶስም አምላክ ነው። ስልዚህ ሁለት አማልክት አሉን ማለት አደለምን? እየሱስ እና አብ?

ወንደሜ ዝናቡ
ሥለ ክርስቶስ መማለድ ሮሜ 8፤34 ጠቅሰሃል ይህንን ያነሳሁት "የሚማልደው" የምትለዋን ቃል ይዘን ፈራጅና ተመላኪ አምላክ የሆነዉን አማላጅ ካልን ብዙ ሳንርቅ በዚሁ አንቀጽ በቁ 26 "ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤" ይላል እና መንፈስ ቅዱስ ይማልዳል ማለት ነው?
በ1ኛ ጢሞቲዮስ 2፣5 «አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ አርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»፡ ስለዚህ ወገኔ መካከለኛው ኢየሱስ ብቻ ነው ብለዋል ለመሆኑ መካክልኛ ማለት አማላጅ/ጠበቃ ማለት ነዉን? በምን አይንት ቃለ መዝገብ /ማብራራት እንደደረሱበት አላቅም።

ኣሁንም ውድ ወንድሜ ክብር የሚግባዉን አምላክ አማላጅ/ጠበቃ/መካክል ክማለት መ/ቅ ምን እንደሚል እንይ፤

1 "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።" (ቃልም እግዚያብሄር ነበር)

እኛ የስው ልጆች በብሉይ ዘመን በአዳምና ሄዋን መሳሳት ያጣንውን የእግዚአብሄር ልጅነትን ሊስጠን እምላካችን እሱ በመጀምሪያ ቃል የንበረው ክርስቶስ በስጋ ተወለደ አዎ ወረድ ብሎ

የዮሐንስ ወንጌል 1፡ 14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ

አዎ እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው። አሜን!!

ክብሮች ሁሉ ለሱ ይሁኑና የእሱን አምላክነቱን ተቀብልን እና በስጋ ስው ሆኖ ያሳየውን አረአያነቱን እንደ ተምሳሌት ይዘን በዘመነ ብሉይ ያጣነውን የ እግዚአብሄር ልጅነት ሊያሰጠን መምጣቱን ሲናግር እንዲህ ይላል

የዮሐንስ ወንጌል14፤ 6 "ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" እንጂ እርሶ እንዳሉት በምን አይእነት መንገድ ኣማላጅነቱን እንደሚያሳይ እይታውቅም፡፡ ክዚህም ሌላ እንደዚህ ጫፍዋን ቆርጦ በማውጣት የመስልንን (ያልተባለን)ተብሉዋል ማለት አይግባም።
ምክነያቱም ይህንን ያለዉ ለምንድን ነው? የተክበሩ ጌታዬ በቁ 8 ላይ "ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።" ልብ ይብሉ ወንድም ዝናቡ ጥያቄ ሰለነበር ነዉ መልሱም
"9 ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?
10 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።" በተለይ (ቁ 11 ልብ ይበሉት) አሁንም ወረድ ብሉ በቁ "13 እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።" 14 ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።(በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።) ክቡር ዝናቡ አደርግዋልሁ እንጂ እንዲደረግ አማልዳለሁ አላለም፡፡

ጌታችንና መደህኒታችን አምላካችን ፈራጅ ነው "አማላጅ" ብሎ መለኮታዊ ክብሩን መቀነስ በሃጥያን የሚፈርደውን እግዚያብሄር አብን አለማክበር ነዉ፡፡

የዮሐንስ ወንጌል 22-23"ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።"

ሜደህኒያለም ክርስቶስ በእርግጥም ይፈርዳል በመሰረቱ ጥብቅና እና ምልጃ ክ መፍረድ ጋ መስረታዊ ልዩነት እንዳለው ወንሜ ዝናቡ ና ሌሎችም አይጠፋችሁም።
መድህንያለም ክርሰቶስም በብልይ የነበረዉን የእርግማን ግዜ አስታርቆ ልጅነትን አሰጥቶን ወደ አብ ሄድዋል የሚመጣው ለፍርድ ብቻ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 5፡ 27 "የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።
28-29 በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።
30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።"

ክብር የሚገባውን እናይ ዘንድ አይነ ልቦናችንን ያብራ አሜን!!!
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ነው ወይስ አማላጅ ? እንዴት ?

መልሱ፦
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡11 "ክርስቶስ ሁሉ ነው፥ በሁሉም ነው።"

ክርስቶስ ኢየሱስ ፈራጅም ነው አማላጅም ነው።

"እንዴት? አልቀበልም። ሁለቱንም ሊሆን እንዴት ይችላል?" የምትል ከሆነ እርሱ ሁሉን ቻይ አይደለም እያልክ ነው ማለት ነው። እንዲህ አይነቱን የተቃውሞ ጥያቄ ማቅረብ ያለብህ እንደ እኛ ላሉ ሰዎች ሳይሆን ለመንፈስ ቅዱስ ነው። ምክንያቱም በቅዱሳን ሰዎች ተጠቅሞ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው እርሱ ነውና። እርሱም አይሳሳትም። ሁሉንም ትክክል ጽፏል።

እንደ አማኝ "ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚሉ ግልጽ ቃላትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሰሃል። ጥሩ ነው። ነገር ግን እንደዚሁ "ኢየሱስ ሰው ነው" የሚሉ ግልጽ ቃላትን ሁሉ ወደ ጎን ትተሃል። ኢየሱስ ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው መሆኑንም ዘንግተሃል። ፍጹም ፈራጅ እና ፍጹም አማላጅ መሆኑንም ክደሃል።

ስለዚህም "ኢየሱስ በሰማይ በአብ ቀኝ ስለ እኛ የሚታይልን አማላጅ፣ ዋስ፣ ጠበቃ፣ ሊቀካህናችን ነው" የሚሉ ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን ሁሉ አልቀበልም ብለሃል። እንግዲህ ምን ይባላል? መንፈቁን (ግማሹን) ታምናለህ። መንፈቁን (ግማሹን) ትክዳለህ። መናፍቅ ማለትም ይኼው ነው።

የጌታ ጸጋ እና ሰላም፣ የቃሉም ብርሃን እንዲበዛልህ ስለ አንተ ወደ አምላኬ እለምናለሁ።
ዮሀንስ 16፡ 26 ምን ልታደርጉት ነው ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም።
ዮሀንሰ 16፡ 26 ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም

3 መልሶች

–1 ድምጽ
ጌታ እየሱስ ከማርያም ድንግል በመወልድ እንድ እኛ ሥጋ ለበሶ ያለ ምንም ኃጢአት በምድር ላይ በመላለስ እውነትን አስትምሮ በጎልጎታ መስቀል ላይ ሙቶ ክቡር ደሙን በማሰስ ዋጅቶ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን። በሦስተኛው ቀን ከሞት በመነሳት ጠላታችንን ድል ነስቶልናል። አሁን ደግሞ በአብ ቀኝ ያለው እሱ ብቻ ያማልደናል። እንዴት ያለ ለንረዳው በማንችል ከሁሉ በላይ በሆነው ፍቅሩ በወርቅ በዑንቅ ልንገዛው የማንችለው ክቡር ዕድል አግኝተናል። ሊሰርቅ ሊገድል ሊያጠፋ የማይተኛ ጠላት ስላለን ይህን ፍቅር አክብረን የመያዙ ጉዳይ የእኛው ምርጫ ነው። ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ በኋአላ የሚመጣው ከሺው ዓመታት የሰላም መንግሥቱ መጨረሻ በኋላ ግን በዙፋኑ ላይ በክብሩ ሲቀመጥ በጎችና ፍየሎችን ለይቶ በፊቱ ሲቆሙ ያኔ ደግሞ ጻድቅ ፈራጅ ነው።

በእምነት ለመጽናት ጌታ ይርዳን። ኣሜን!!!
Mar 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 6, 2011 ታርሟል
በመጀመርያ ባይብልን እንደየት፤የት፤ለምን፤መች፤በምን ሁኒታ ተታፈ የሚለውን ማስተዋል ያስፈልጋል ሃዋርያው ፓውሎስ እንዲህ ብሎ ነበር(ምንም እንኩዋን ወንግላችን የተከደነ ቢሆንም የተከደነባችው ለሚተፉት ነው)እዚህ ጋ ማስተዋል ያስፈልጋል ዝም ብለን ከላይ ከላይ እያነበብን የምንራመድ ከሆነ እንወድካለን።የሃዋርያው 2 ፒትሮስ መልእክት 1-20-21 ያለውን መመልከት ይቻላል። ስለዚህ ከላይ የተገለተው ሃሳብ ሃዋርያቶቹ ካሰፈሩት ጋር የሚስማማ ነው ብሎ መመርመር ያስፈልጋል!!ይሁን ካልን ደግሞ መንፈስ ክዱስ ያማልዳል የሚል በባይብል አለ የ ሃዋርያው ፓውሎስ መልእክት ወደ ሮም ሰዎች 8-26 እንዲሁም አብም ያማልዳል የሚል በትንቢቶች ውስት እናያለን ስለዚህ ዝም ብለን ከላይ ከላይ ብቻ እያየን እንዳንሳሳት ማስተዋል ያስፈልገናል።እየሱስ ክርስቶስ ስጋ ለብሶ በታየ ጊዚ በትክክል ከ አንዲት ሃትያት በስተከር ሰው የሰራውን ሁሉ ሰርቶዋል።ከ አብ ጋር የማስታረክ ሰራ የማማለድ ስራ ሲሰራ ኮይቶ ስራውን ሲቸርስ ወደ ክብር ዙፋኑ ተመልሶዋል።እርሱ እግዚአብሂር ነው።አብ፡ወልድ፡መንፈስ ክዱስ አንድ አምላክ በክብር ዙፋኑ ላይ አለ።ወልድ ወደ አብ አይለምንም ወይም ደግሞ መንፈስ ክዱስ ወደ አብ ወይም ወልድ አይለምንም።አለበለዚያ ወልድ ያማልዳል ካልን እኩል አይደሉም እንላለን።ስለዚህ ክርስቶስ የማማለዱን ስራ በዚህ ምድር አተናኮ አሁን በክብሩ ዙፋን ላይ አለ።ማምላካችን እውነቱን ይግለትልን አሚን!!!
ትክክለጝ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት ካለወት ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀጝ ስለ እጝ እንደሚማልድ ግልጽ በሆነ መንገድ ከላይ ለተቀመጡት እውነቶች መልስ መስጠት ይገባወታል.ግልጽ የሆነውን እውነት ካልካድን በስተቀር
ለኔ ጥያቄ መልስ የሚስጠኝ ነው ያጣሁት ክጥይቄው በፊት ግን አላማችን/ፍላጎታችን መማማር ይሁን።እኔ እንደሚገባኝ አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ስው ሆኖ ፍጽሙን የአምላክነት ባህሪዩን ክስብእና(ስው ክመሆን)ጋ ያዋሃደዉ እግዚአብሄር ኣብ ለኛ ካለው ጽኑ የአባትነት ፍቅር ነው። አዎ ታላቁ ሊቀ ካህናችን እንደግናም ፍጹሙ አምላካችን መድሃንያለም ክርስቶስ በብሉይ ዘመን ያጣነውን መለኮታዊ በረከት ያስመልስልን ዘንድ አምላክ ሰው ሁነ። (አዎ የ አምላክ ልጅ)አምላክ የሆነው ነው።

ሁላችንም እንደምንስማማበት አንድ አምላክ በሃዲስም በብሉይም አብን ያምለክታል። በተመሳሳይ መልኩ ግን የክርስቶስ አምላክነትም የሚያጠያይቅ አደለም፡፡

ስለዚህ ሁለት አማልክት አሉን ማለት ስለሆነብኝ ጉዳዩ እርስ በራሱ ይጣላብኛል። በሌላ አባባል " የኢየሱስ ቦታ ከአብ እኩል ሳይሆን በአንዱ አምላክ በአብና በሰው መካከል ነው። የአንዱ አምላክና የሰውም ባህርይ ስላለው በሁለቱ መካከል ሊቆም የሚችል እውነተኛ ሊቀካህን ነው።" የምንል "ሊቀ ካህን" ነዉ አልቀ።
አምላክ አይደለም። ማለታችን አይደልምን? ምክነያቱም 1+1=2 ነው እንጂ 1+1= 2 እና 3 ሊሆን አይችልም።

አምላክንቱን ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ያለምንም ጥያቄ እናምናለን። ግሩም ጌታችን
አምላክ ነው። መ/ቅ አንድ አምላክ ስለመኖሩ ይጠቅሳል ያዛልም። ስልዚህ አብ አምላክ ነው ጌትችንም አምላክ ነው።

ሁለት አማልክት አልኖሩንም??

በ እርግጥ ጢሞ2፤5 ን እንደሚጠቅሱ አይጠፋኝም ንገር ግን ጌታችን ክ እርግት ቡሃላ እንደሚማልድ መ/ቅ ካሳየ እርዳታዎን እፈልጋልሁ። ለፍርድ እንደሚመጣ ግን ሁላችንም አይጠፋንም።
በዚህ አጋጣሚ እውቀትን ፍለጋ እንጂ እንዱን ከዛ ጎራ እኔ ወዲህ ሆኜ የማይጠቅም
ሙግት ፈልጌ ኣደለም። ለሙግት የሚብቃም እውቀት እንዳለኝ አላቅም። ለኔ ይህ ጉዳይ መደሃኒታችንን ና አምላካችን ተገቢ የክብር ቦታውን የሚመለከት ስልሆነ ልንጠነቀቅ ና ልናቅ ይግባል።

ለጠየኩዋቸው ጥያቄወች ቀጥተኛ መልስ የሚስጡኝን አመስግናልሁ፡፡ ሰለስላሴ ያነሳሁት ነገር የለምና ለግዜው እሱን ባናነሳ።
በክብሩ ሲቀመጥ አሁን አልተቀመጠም?
0 ድምጾች
እብ7፤25 ሮሜ8፤34 ኢሳ53፤12 ኤፌ2፤18 ፣ ቆላ1፤20-23 እና ሌሎችን ጥቅሶች ይመልከቱና ስለ አማላጅነቱ ግንዛቤ ይውሰዱ።
Mar 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ከርስቶስ እርሱ ጊታ አምላክ፡ ፍራጅ ነው
Mar 11, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ye teyaqe hasb enji ye alakacen mannet wisgn ayedelam amalgim feragim lemehon ayclem yalew man nw? keqalu huletunm hono aytenewal.
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...