ደካማ የተባለው " ሁሉ ተፈቅዶ ሳለ ባለማመኑ ምክንያት አሁንም የቀድሞ የብሉይ ሥርዓት የሚያስፈራራውና ፍጹም እምነት የሌለውን ሰው በተመለከተ የተሰጠ ስያሜ ነው። ደካማው አትክልት የሚበላው እግዚአብሔርን ፈርቶ ሲሆን ሌላውም ከሕግ ነጻ እንደወጣ በማመኑ ምክንያት ያለፍርሃት የሚበላው እግዚአብሔርን እያመሰገነ ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 14
1 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።
2 ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል።
3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።
በቁጥር 1 ላይ እንደሚታየው የደከመ የተባለው በእምነት ስለደከመ ነው። ስለዚህ ደካማው እምነት የጎደለው ማለት ነው።
አመሰግናለሁ
ፋንታጎንስ