ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 18 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

"ደካማው አትክልት ይበላል" ማለት ምን ማለት ነው?

ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል ሮሜ 14'2
Feb 23, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
ደካማ የተባለው " ሁሉ ተፈቅዶ ሳለ ባለማመኑ ምክንያት አሁንም የቀድሞ የብሉይ ሥርዓት የሚያስፈራራውና ፍጹም እምነት የሌለውን ሰው በተመለከተ የተሰጠ ስያሜ ነው። ደካማው አትክልት የሚበላው እግዚአብሔርን ፈርቶ ሲሆን ሌላውም ከሕግ ነጻ እንደወጣ በማመኑ ምክንያት ያለፍርሃት የሚበላው እግዚአብሔርን እያመሰገነ ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 14
1 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ
2 ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል።
3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና

በቁጥር 1 ላይ እንደሚታየው የደከመ የተባለው በእምነት ስለደከመ ነው። ስለዚህ ደካማው እምነት የጎደለው ማለት ነው።

አመሰግናለሁ
ፋንታጎንስ
Feb 23, 2012 ቤሪያ (1,200 ነጥቦች) የተመለሰ
የወንድሜን መልስ የተረዳኽው ስላልመሰለኝ ጥቂት አስተያየት ልስጥበት
    1)መጀመሪያ መልሱን አስተውለህ ደግመህ ብታነበው ደስ ይለኛል
    2)
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 14፥
1 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።2ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። 3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።

እዚህ ላይ ላሰምርበት የምፈልገው... ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ .. የሚለውን ነው ይህ በአዲስ ኪዳን ወንጌል ያመነ ሰው ባህሪይ የሚገልጽ ነው ምክንያቱም ”… ሁሉ ተፈቅዶአል ግን ሁሉም አይጠቅምም…” የሚለው አቁዋም ላይ ነውና ይህ ሰው አትክልትም ይሁን ሌላ ነገር ቢበላ ነቀፈታ ወይም ሃጢያት የለበትም ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው። ከዚህ በመቀጠልም ” ደካማው ግን አትክልት ይበላል።” ማለትም እምነቱ ጠንካራ ያልሆነው ግን አትክልት ይበላል። ይህም ሰው ከቀድሞው የ አይሁድ ህግ ሙሉ በሙሉ ነጻ ያልወጣ ወይም እምነቱ የደከመ በመሆኑ ምክንያት በቀድሞው ልማድ ውስጥ እንዳለ ያሳያል ምክንያቱም ”… ሁሉ ተፈቅዶአል ግን ሁሉም አይጠቅምም…” በሚለው አካሄድ ሳይሆን አልተፈቀደም በሚለው መመሪያ ይመራልና። ያም ሆነ ይህ "የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።"
ስለሚል ሁለቱንም ማለትም በእምነቱ የበረታውንም ይሁን የደከመውን እግዚአብሔር የተቀበላቸው መሆኑን ያሳያል። ሁላችንም እኩል የሆነ የእምነት ጥንካሬ የለንምና አንዱ የደከመ አንዱ የበረታ የመሆኑ እውነታ አያስቆጣም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 14፥1
በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።2ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። 3 የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።
ፋንታጎስ ሳይሆን ቃሉ ነው የሚለው።
ፋንታጎንስ፣ ትክክል ብለሃል። ሁሉም ቢፈቀድ ሁሉም እንደማይጠቅም የማያውቅ ያገኘውን ይበላል። የሚበላው ከደካማ እምነቱ የተነሳ ነው። ስለዚህ አንተ የምታምን በእንደዚህ ዓይነቱ የእምነት ደካማ ሰው ላይ አትፍረድ! ይልሃል ወንጌል። ሌላው ደግሞ በወንጌል ቢያምንም ሁሉ በእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው የሚለውን ለመቀበል በፊት የነበረበትን የሕግ ትዕዛዝ ፈጽሞ ለመተው ስለሚቸገር ጥያቄና የስህተትን ሃሳብ የማያስነሳበትን አትክልት ብቻ ለመብላት ይገደዳል። ይህም በእምነቱ ደካማ ሰው ነው። አንደኛው እምነት የጎደለው ሲሆን ሌላኛው እምነት ቢኖረውም በእምነቱ የበሰለ አይደለም ማለት ይመስለኛል።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...