ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ዘፈን ሀጥያት ነው ለምን ?

Mar 6, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

5 መልሶች

–2 ድምጾች
ዘፈን በመሰረቱ ኃጢአት አይደለም ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን እስራኤላዊያን በዘፈን እግዚአብሔርን በዘፈን ያምሰግኑት ነበር (2 ሳሙ 6፡14 መዝ 149፡2)። ሙዚቃ ከጥንቱ እግዚአብሔር የሚወደስበት ነው ችግሩ ግን ቃላቱ ላይ ነው። የምንለው ቃል ስዕል ሳይቀር ሲታየን ኣሳባችንን ሲደፈርስ ስጋ መሰልጥን ይጀምራል በቅጽበት ካልተመታ መንሸራተቱ ከባድ የአጥንት ስብራት ስለሚያስከትል ለጠላት አመቺ ዕድል መስጠት የለብንምና እጅጉን እንጠንቀቅ።

ጌታ ይባርካችሁ
Mar 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 6, 2011 ታርሟል
በማኒኛዉም ሙዚቃ ቢሆን የሚንጠቀመው ቃላቶች ወሳኝ ናቸዉ. ሲለዚህ ቃላታችን ሁሉ ኢግአቢሄርን የሚያመሰግን መሆን አለበት.
ጌታ ይባርካችሁ!
ዘፈን ዲብን አድርጎ ሃጢያት ነው ሮሜ13፤13 ገላ5፤19 1ቆሮ10፤7 ይመልከቱ።
ኢየሱስ ያድናል
መጽሓፍ ቅዱስ ዘፋኞች መንግስተ ሰማይን አይወርሱም ይላል ገላ. 5፡21። እንዳይወርሱ የከለከላቸዉ ታድያ ዘፋኝነታቸዉ መሆኑ አይደለምን? ለዚህ ያበቃቸዉስ ታድያ ዘፈን መሆኑ አይደለምን? እንግዲያስ ዘፈን መንግስተ ሰማይን የሚያዘጋ ወይም የሚከለክል የሆነዉ ጥሩ ስለሆነ ወይስ ሓጢያት ስለሆነ ይሆን? እዉነቱ ግን ''ሐጢያት ስለሆነ ብቻ ነዉ''።
ጥያቄዉ ''ዘፈን'' ሐጢያት ነዉ? ብሎ ይጠይቃል እንጂ ''ሙዚቃ'' አይልም፡፡
ዘፈን እና ሙዚቃ ምንድን ነው የሚለያቸው እባካችሁ አብራሩልኝ
ሙዚቃ ማለት ለሁለቱ የምንተቀምበት መሳርያ ነው ፣ ዘፈን ማለት ግና እንደመጣልህ መዝፈን ማለት ነው እንደመጣልህ ማለት ለሰው መወደስ ስለ ፍቅር፣ ለእግዚአብሂር ያልሆነ ሆይሆይታ ማለት ነው
+1 ድምጽ
ሰላም የብዛላችሁ ጥያቄውን ከቃሉ መመልስ መልካም ነው1)[quote]ሮሜ13፤12-13 ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ [/quote]2)[quote]ገላ5፤19 -21 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። [/quote] ተባረኩ[code]ሰላም የብዛላችሁ
ጥያቄውን ከቃሉ መመልስ መልካም ነው1)
Quote:
ሮሜ13፤12-13
ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
2)
Quote:
ገላ5፤19 -21
የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥
መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥
መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
ተባረኩ
Aug 11, 2011 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ስለ ዘፈን ሃጢአት መሆን አለመሆን ከመወያየታችን በፊት ሙዚቃ ምንድን ነው? ብለን ብንጀምርና መዝሙርንም እንደ ሙዚቃነቱ አብረን ብናየው መልካም ይመስለኛል፡፡ ይህን ካደረግን በኋላ ስለዘፈንም እናወራለን፡፡ ዋናው ነገር ግን እግዚአብሔርን በዘፈን ማክበር ይቻላል ወይ ብለን እንጠይቅና መልሱን ለዋናው ጥያቄ መልስ አድርገን እናቅርበው፡፡
Aug 25, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
አዎ ዘፈን ሃጥእት ነው ምክንያቱም 1.......የ ዮሃንስ አንገት የተቕረጤው በ ዘፈን ምክንያት ስለሆነ የዘፈን ዉጤቱ አያምርም፤ 2.......ሰው የተፈጥረው ለምስጋና ስለሆነ(እ/ርን) ፡ባመሰገነበት አንደበት ፤በተቕደሰው ልብ እንደት ይዝፈንበት... .... ...
Sep 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
በመስረቱ ዘፈንን በብዙ ጎኑ ልናዬው እንችላለን። የፍቅር፥ የሰርግ፥ የምክር፥ የፖለቲካ፥ ፍጥረትን ማድነቂያ፥ ፈጣሪን ማመስገኛ ''''ወዘተ

መዝሙርንም ስናይ መንፈሳዊ፥ ብሔራዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ትምህርታዊ'''ወዘተ።

እነዚህን ሁሉ ዜማ በሚል እናጠቃልላቸዋለን። በመጽሓፍ ቅዱስ ዘፈን እንደዳዊት እግዚኣብሔር ሲመሰገንበት፥ እንደ ሰሎሞን ፍቅር ሲቀኙበት፥ እንደ በኣል ነቢያት ጣኦት ሲመለክበትና ገላትያ ላይ እንደተጻፈው ለስጋ ስራ ሲውል እናያለን ። ከዚህ የምንረዳው ዘፈን
1ኛ አይነት አለው
2ኛ ሙዚቃ ነው
3ኛ ሰዎች ለተለያየ ጉዳይ ያውሉታል።

በአዲስ ኪዳን የተጻፈልን ዘፋኝነት የሚለው ቃል ስለ አርቲስታዊ ሙያ ሳይሆን ስለ አንድ ስጋዊ ሰው ባህሪ ነው የሚነግረን። በሌላ አባባል ጨፋሪነትን እና ከጨፋሪንት ጋር አብረው የሚቆራኙ የስጋ ባህሪያት እነርሱም ስካር ፥ ዝሙት ፥ ርኩሰት ወዘተ በሕይወቱ ያለ ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም ነው የሚለን።

ነገር ግን ዘፈን ብለን የምንጠራቸው ዜማዎች ኃጢአትነታቸው ባዘሉት መልእክት ላይ ይወሰናሉ። " በመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ
መጠን አትለፉ ትቃጠላላችሁ " ብሎ ዘፈን ያወጣ ሰው ኃጢኣት እንደምን ሰራህ እንበለው ? ወይም " አርቆ ማሰቢያ እያለን አይምሮ
እንደምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ " ሲለን ዘፋኙ እኛን ክርስቲያኖቹንም አይዴል እንዴ የሚመክረን ?
ወይስ " ከልብ ከመነጨ ከእውነተኛ ስሜት
እኔ እወድሻለሁ አይደለም የሐሰት " ማለቱ ከ መኃልየ መኃልይ ምን ተቃርኖ አለው ? ነገር ግን "ልባርከው ጌታዬን ልባርከው " በሚል መዝሙር ናይት ክለብ ዉስጥ በሙዚቃው ተስበው የጨፈሩና የሰከሩም ጽድቅ ሰርተዋልን ? አሁን አሁን እንደውም ጨፋሪነት የተባለው የስጋ ስራ በመዝሙር ተከልሎ ቤተክርስቲያንን እየወረረ ነው እኮ።

ስለዚህ የስጋ ስራ የተገለጠ ነውና ራሳችንን እንጠብቅ። በሀገራችን ያሉ አርቲስቶቻችንን ግን መንግስተ ሰማይን አትወርሱም የምንላችው በሙያችው ምክንያት ሳይሆን ከኃጢያት የሚያንጻቸውን ኢየሱስን እንስበክላቸው። በጌታ ካመኑና ዐለምን ከካዱ ዘፋኞቻችንም የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳሉ። ለዝማሬ ከተጠሩ ይዘምራሉ፥ ካልተጠሩም ሰይጣናዊ ከሆኑ ዝሙታዊ ዘፈኖችን ተዋግተው ሚዲያዎቻችንን በመልካም ምክርና እውቅት ይሞላሉ። በሙያቸው እንዳይቀጥሉ ምንም አያግዳችውም።

በአጠቃላይ የቃሉን አላማና ትርጉም በሚገባ እንረዳና እንመለስ እንጂ ባለሙያዎችን የመንግስተ ስማይን በር አንዝጋባቸው። ጌታ አብዝቶ በእውቀትና በማስተዋል ይባርከን ፥ አሜን።
Apr 9, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...