ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ላይ የእመቤታችንን ማርያም ተብሎ የተጨመረው ለምንድን ነው

አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ላይ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ተብሎ የተጨመረው ለምንድን ነው መጽሀፍ ቅዱስ ላይ የሉቃስ ወንጌል 11
1 እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ። ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።
2 አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
3 የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤
4 ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን…..
ሆኖ ሳለ ታዲያ ለማርያም የተጨመረው ጸሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው ወይስ መላው የአለም ህዝብ የሚጠቀምበት ነው 
Mar 1, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

–1 ድምጽ
ይህ የማርያም ጸሎት ማለትም «በሰላመ ገብርኤል እና ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም» የሚባሉት የተሰባሰቡትና የተቀነባበሩት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ቃላት በማገጣጠም ማርያምን ለማመስገን እንዲሆኑ የተዘጋጁ ናቸው።
1/ በሰላመ ገብርኤል የተባለው የማርያም ጸሎት በአጭሩ ሲቀመጥ የኃጢአትን ስርየት ለሰው ልጆች እንድታሰጥ የሚጠየቅበት ነው።( ሰዓሊ ወጸልዪ ለነ ምህረተ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይስረይ ለነ ኀጣውኢነ) ሲል ይታያል።ይህም ከተወደደው ልጅሽ ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ ለምኝልን፣ ጸልይልን ማለትን ያመለክታል።
እዚህ ላይ ያሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስህተቶች እንመልከት፣
ሀ/ ማርያም የኃጢአትን ስርየት ከእግዚአብሔር ዘንድ ማሰጠት ብትችል ኖሮ የክርስቶስ ከእሷ መወለድ ባላስፈለገም ነበር። ደም ሳይፈስ ስርየት ስለሌለ ክርስቶስ ስጋ ለብሶ ለኃጢአት ስርየት ይሞት ዘንድ የግድ ስለነበር ይኼው ሆነልን። «በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት» ኤፌ 1፣7 ሆነ ይለናል። ሰው ከቀደም የኃጢአት ሞት የዳንነው ከእግዚአብሔር የሞት መስዋእት ስጦታ የተነሳ ነው።
ለ/ ሰው በዚህ ነጻ ስጦታ ካመነ በኋላ በስጋው ኃጢአትን ቢሰራ ከኃጢአቱ መንጻት የሚችለው ኃጢአቱን ይቅር ለሚለው ለእግዚአብሔር መናዘዝ ሲችል ብቻ ነው።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
1፥9
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።

ከዚህ ውጪ ሌላ የኃጢአት ስርየት መንገድ ስለሌለ «ሰላመ ገብርኤል» የተባለውን በመድገም የሚመጣ ስርየት የለም።
2/ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም የተባለው ከመደገሙ በፊት ደግሞ እንደመርገፍ የሚጸለይ ቀዳሚ ሐረግ አለው። «ሰላም ለኪ፣ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ፣ ማርያም እምነ ናስተበቁዐኪ፣ እምአርዌ ነዓዊ ተማኅጸነ ብኪ»
ሰላም እያልንና እየሰገድንልሽ የምንማጸንሽ ነገር ከአዳኝ አውሬ እንድታድኚን ነው» የሚል ሆኖ ይተረጎማል።
በመሰረቱ «አውሬ» የሚባለው ሰይጣን ነው። «ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ» ራእይ 20፣10 በማለት እንደተናገረው።
ሰይጣንን የቀጠቀጠው የሰላም አምላክ ክርስቶስ ነው። ያዳነንም እርሱ ነው።
ቆላ 1፥13-14
«እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን»
ወደፊትም የምንድንበት ተስፋችን ክርስቶስ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም።

2ኛ ቆሮ1፥10-11
«እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል»
ስለዚህ ማርያም ክርስቶስን በድንግልና በመውለዷ ብቻ ክርስቶስ ሆናለች በማለት በክርስቶስ ቦታ ከአውሬው አድኚን ማለት ትክክል አይደለም ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን አዳኝነትና አውሬውን የቀጠቀጠውን የመስቀል ላይ ሞት ዋጋ ማሳጣት ነው። ማርያም ራሷ ብትጠየቅ ከአውሬው ያዳንኳችሁና የማድናችሁ እኔ ነኝ አትልም። እርሷ ምስጉንና የምታመሰግነውን የምታውቅ ናትና።
ሉቃ 1፥47
ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ ስትል ሰምተናታል።
በአጠቃላይ ስለማርያም በዚህ ምድር አቀናባሪዎች የተጻፉት ጸሎቶች ዓይናችንን ከልጇ ላይ አንስተን ወደእርሷ እንድናዞር የሚያበረታቱና ከእውነተኛ መንፈስ ያልሆኑ ክርስቶስን የሚያዘናጉ ናቸው።
3/ ይህንን ጸሎቶች የሚጠቀሙበት፣
በአብዛኛው ማለት በሚቻልበት መልኩ ካቶሊክን ጨምሮ የምስራቅ ኦርቶዶክሶችና ምእራባውያን ኦርቶዶክሶች ይጠቀሙበታል። ለስእል ስግደትና አምልኮ ይገባል የሚሉት ሁሉ ከጥቂት የቃላት ልዩነቶች በስተቀር ይገለገሉበታል። ሐዋርያት ግን እነዚህን ጸሎቶች ይጠቀሙባቸው እንደነበር የሚያረጋግጡ አንድም አስረጂ የለም። ምናልባትም ጽሁፎቹ የተቀነባበሩት ከ4ኛው ክ/ዘመን በኋላ ነው።
Mar 1, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
ራስህ ስትጽፍ ጠንቀቅ እያልክ!! አምልኮ ማለት በራሱ ቃሉ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ?
መለከ፣ ገዛ- መለክ ገዢ ከሚለው የግስ ዘር የወጣ ነው። ግእዙ እንዳለ እግዚእ ፣ ገዢ፣ ጌታ ማለት ለወንድ አንቀጽ ሲሆን እግዝእትነ ገዢያችን፣ እመቤታችን ማለት ደግሞ ለሴት አንቀጽ የሚውል ነው። በእምነት ውስጥ ለብዙ ጌቶች የመገዛትና የማምለክ ችግር አሁን አንተ የምትከላከልላቸው ሃይማኖቶች እግዝእትነ ማርያም ገዢያችን፣ እመቤታችን «ብኪ ድኅነ ዓለም» ባንቺ ዓለም ዳነ የሚሉት በአደባባይ ነው። በእርግጥ አምላክና ፈጣሪ ናት አይሉም። ግን ደግሞ ለፈጣሪ የሚገባውን የግብር ስም አይከለክሉም። ወዳጄ አምልኮ ማለት ይሄ ነው። ብዙ ገዢዎችን የማምለክ ችግር!! በተበጠበጠ ቀለም ለተሰራ የሆነ ስእል ስትሰግድ መልእክት እያስተላለፍክና ከስእሉ ምላሽ እየጠበቅህ መሆኑን እርግጥ ነው! ስእሉ ምን ስለሆነ? ምን ስለሚናገር? ምንስ ማድረግ ስለሚችል? የሆነ ምላሽ ጠብቀህ ከሆነ ማድረግ እንደሚችል አምነሃል ማለት ነው። አምልኮ ማለት ይሄ ነው! ገባህ? ምንም እንዲያደርግልኝ አልጠብቅም ካልክ ደግሞ ለጣዖት እየሰገድክ መሆኑ ነው። በተግባር እየፈጸምክ ነገር ግን እንደአምላክ ለማምለክ አዋጅ አልነገርኩም ብትል የምታታልለው እራስህን እንጂ ስራህን አይደብቅልህም። ኦርቶዶክሳዊ ከሆንክ አባታችን ሆይ ከሚለው ጸሎት ቀጥሎ ጸሎተ ማርያምን ካልጸለይክ አንተ ጴንጤ ወይም ጸረ ማርያም ሆነሃል ተብለህ ትባረራለህ ወይም ትደበደባለህ። እግዚአብሔርንም ማርያምንም አከታትለህ ካመሰገንክ በኋላ ነው ሌላ የትኛውም የቤተክርስቲያን ጸሎት የሚጀመረው ወይም የሚፈጸመው!! እኔ ያለሁበትና የማውቀው ሲሆን ሂድና ጠይቅ ማለት ለቀባሪ ማርዳት ይሆንብሃል።
+1 ድምጽ
ሰላም

በቅድሚያ እኔ አንተን የምመክርህ ራስህ አዲስ ኪዳንን (ማለትም ስለ ኢየሱስም ይሁን ስለ ማርያም የተጻፈበትን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል) እንድታነብብና ስለ ማርያምና ባጠቃላይ ስለ አዲስ ኪዳን መልእክት የራስህ መራደት እንዲኖርህ ነው።

እኔ ለብዙ ዓመት መጽሃፍ ቅዱስን አጥንቼአለሁ፤ እናም ማርያም የአዲስ ኪዳን ታሪክ አካል ነች እንጂ አንድም ቦታ የአምልኮም ይሁን የጸሎት አካል ሆና አታውቅም። የታሪክ አካል የሆነችውም ስናነብብ ስለ ልዩ ልዩ ገድሏ ወይም ስለ ልዩ ልዩ መልካም ስራዋ ሳይሆን፤ በአባዛኛውል ጌታችንን ኢየሱስን በመውለዷ ላይ ያተኮረ ብቻ ነው።

ማርያም ስትታጭ ምናልባት ትንሼ የ15 ዓመት ልጅ ናት፤ እኛ እንደምናስባት እንዲያው ሰዎች የሚጸልዩላትና የሚያመልኳት ወይም የእምነታቸው አካል ያደረጓት የሆንች ትልቅ ሴትዮ አድርገን አንያት። ራሷ ማርያም ስለ ራሷ ስትናገር "የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቷልና" ነው ያለችው (ሉቃ 1፡48)

ማርያም ልክ እንደ የኢየሱስ ደቀመዛሙርትና ሃዋርያት ሁሉ፤ በዋናው የአዲስ ኪዳን ታሪክ ማለትም የክርስቶስ መምጣት፣ ስለ ኃጢአታችን መሞትና ከሞት መነሳት ዙሪያ ውስጥ አንድ የታሪክ አካል ናት እንጂ የአምልኮ ወይም የክርስትና እምነቱ ወይም አስተምህሮቱ አካል አይደለችም።

ይህንን ለማወቅ ከፈለግህ የክርስቶስ የቅርብ ደቀመዛሙርት የሆኑት እንደ እነ ጴጥሮስ፣ ዮሃንስ እንዲሁም ደግሞ የአዲስ ኪዳንን ከአንድ ሶስተኛ በላይ መልእክት የጻፈውን ሃዋርያው የጳውሎስን መልእክቶች አንብብ። የክርስቶስ ሃዋርያት በጻፉት መልእክት ላይ አንድም ቦታ ማርያም የክርስትና እምነት ወይም የአምልኮ ወይም የጸሎት አካል ሆና አታውቅም። ይህ ብቻ አይደለም ስሟንም እንኳን ሃዋርያቱ በመልእክታቸው አልጠቀሱም። እርሷ ልክ እንደ እነርሱና እንደ ጲላጦስ የመሳሰሉት በዚያን ጊዜ የኖሩ ሰዎች በክርስቶስ ታሪክ ውስጥ ሚና የተጫወተች የታሪኩ ተካፋይ እንጂ ልክ እንደ እነርሱ ሁሉ የክርስትና እምነቱ ወይም አስተምህሮቱ አካል አይደለችም።

የክርስትና እምነት መሠረቱ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ነው እኛ እንድናምን የተጠራነው። መዳን በክርስቶስ ነው የሚለን አዲስ ኪዳን። ክርስቶስ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ስለዚህ አዲስ ኪዳን በእግዚአብሔርና በልጁም በክርስቶስ ላይ ያለ እምነት እንጂ በሃዋርያቱ ወይም በማርያም ወይም በሌላ ሰው ላይ ያለ እምነት አይደለም።

የማርያም ጸሎት ማለት እኮ በጣም አደገኛ ነገር ነው። ማርያም የእምነታችን አካል አይደለችም። የክርስትና የታርኩ አካል እንጂ። ጸሎት በክርስቶስ ስም ወደ እግዚአብሔር የሚደረግና ወደ እግዚአብሔር ብቻ የሚደረግ ነገር እንጂ ወደ መልኣክም ይሁን ወደ ሌላ ሰው የሚደረግ ነገር አይደለም።

ለማናቸውም ቃሉ የተጻፈው ለአንተም ነውና በማንም ሰው መልስ ሳትደናገር ራስህ አንብበው። ማርያም እውነት የክርስታና የእምነቱ አካል ነች ወይስ የክርስቶስ ታሪክ አካል ብቻ ነች የሚለውን አንተው ራስህ ትመልሰዋለህ።
Mar 2, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
ምን እያልክ እንደሆነ አልገባኝም። የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚነትህ አልተገለጸልኝም። ረጅም ታሪክ መጻፉን ተውና በአጭሩ ልንገርህ። ማርያም አምላክ ወይም ፈጣሪ እንዳልሆነች እያወቁ ግን ደግሞ የፈጣሪን ቦታና ምትክ ሰጥተው የሚያመልኩና የሚሰግዱ ተቋማት አሉ። በስእል፣ በጸሎት የሚያመልኩ አሉ። በማስረጃ ላረጋግጥልህ እችላለሁ። አንተ ከወደየትኛው ነህ? የለም እያልክ ከሆነ የለም ብለህ ተከራከረኝና እኔ ማስረጃዬን ላቅርብልህ። አሉ የምትል ከሆነ ደግሞ እኔም እንደዚያ ስለምል ከእኔ ጋር የሚያጻጽፍህ ነገር የለምና በዚሁ ይብቃ።
ወገኔ

እኔ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያም አትመለከም እያልኩ ነው ያለሁት። በሙሉ የጻፍኩት መጽሃፍ ቅዱስን በተመለክተ እንጂ ከመጽሃፍ ቅዱስ ውጪ ስላሉ ሰዎች ወይም ሃይማኖቶች ድርጊት አይደለም። እንግዲህ በመጽሃፍ ቅዱስ ማርያም የማትመለክና የማይጸለይላት ከሆነ በአሁኑ ዘመን ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ይህ ድርጊታችው መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም እያልኩ ነው። እባክህ በቅድሚያ የጻፍኩትን በጥሞና ለማንበብ ሞክር መልስ ከመስጠትህ በፊት።

ጌታ ይባርክህ።
ሰላም ወንድሞች

እኔ እንደምረዳው በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማሪያም መለኮታዊ(የ አምላክነት)ክብር የላትም። ንገርግን እመቤታችን ክፍጡራን ሁሉ ከፍ ብላ ትከበራለች።
ስትጽፍ ጠንቀቅ እያልክ። ለስእል አምልኮ ይገባል የሚል ክርስትያን የለም ፤ ክተጠራጠርክ ጠይቅ። በሁሉም በጠቀስካቸው የ ሃይማኖት ቅርንጫፎች አምልኮ ለ አንድ አምላክ ነው!

ይህ አንተ ለኔ ከላይ የሰጠኸው መልስ ነው። እንደዚህ የሚያመልክ ሃይማኖት የለም ብለህ ስለሃይማኖቶች ጥቅል መልስ ሰጥተህ ስታበቃ አሁን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ወደሚለው ሌላ ሃሳብ ለመመለስ ትሞክራለህ! ለምን? እየተነጋገርን ያለነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር ውጪ ሌላ የሚመለክ አለ በሚል ነጥብ ላይ አይደለም። ለጽሁፋችን መነሻ በሆነው ጥያቄ ላይ አባታችን ሆይ ከሚለው ጸሎት ጋር የእመቤታችን ጸሎት ለምን ተጨማሪ ሆነ በሚል መነሻ ሲሆን የእኔ ምላሽ ከእግዚአብሔር ጋር ምስጋናንና አምልኮን ለማርያምም ሆነ ለስዕላ ስእል በመስጠት የሚያመልኩ አሉ በማለት ለመመለስ ሞክሬአለሁ። አንተ ደግሞ እንደዚህ የሚሉ የሉም አልክ። አሉ ስል በሚጠቀሙባቸው ጽሁፎች አስረጂነት እንጂ በፈጠራ አይደለም።
እነዚህን ተመልከት!
«ንትፈሳሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም፣ ወደመ አስካልኪ መዓድም፣ ቅድስት ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም» ኩሎሙ
ትርጉም፣ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆንሽ ቅድስት ማርያም ሆይ ጣፋጭ በሆነው በስምሽ መታሰቢያ የደምሽ ፍሬ እንደሰታለን» ማለት ነው።
ማርያም የዓለሙ ሁሉ ቤዛ ሆነች ማለት ምን ማለት ነው? የወንጌል ቃል ስፍራው የት ይሁን? «በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ»ሮሜ 3፣24
ማርያም የዓለም ቤዛ ሆነች ማለት ማምለክ አይደለምን?
ሰላም ለስእልኪ ሀፈ ማኅየዌ በጼዴንያ ወግብጽ ዘአውኀዘት በኢኅሳዌ፣ ለመጽብሐዊ ማቴዎስ እንተ ረሰኪዮ ወንጌላዌ» ትርጉም፣ በጼዴንያና በግብጽ ያለምን ሃሰት ፈዋሽ ወዝን ላመነጨው ስእልሽ ሰላም እላለሁ፣ ቀራጩ ማቴዎስንም ወንጌላዊ ያደረግሽው አንቺ ነሽ» ማለት ነው። ከስዕል የሚመነጭ ወዝና ይህም ወዝ የሚፈውስ መሆኑን በመመስከር ሰላም እለዋለሁ ማለት ምን ማለት ነው? የሰው ስእል ወይስ ክርስቶስ ነው ፈዋሽ? ወዝ ወይም ላብ ፈውሴ ነው የሚል ምንን እያመለከ ነው? ደግሞስ ማርያም መቼና እንዴት አድርጋ ነው ቀራጩ ማቴዎስን ሐዋርያ አድርጋ የመረጠችው?
«ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው» ማቴ 9፣9 ይህን የወንጌል ቃል ሰርዞ ጥዋትና ማታ ማመስገን ምን ይባላል? በክርስቶስ ቦታ ማርያምን ተክቶ ማመስገንን ምን ልትል ነው?
አምልኮ ማለት በአምላክ ስም ምስጋና ማቅረብ ነው። ለሰው ወይም ለዛፍ ወይም ለተራራ ወይም ለምስል ወዘተ በፈጣሪ ምትክ ምስጋናንና እንደሚያደርግልህ፣ እንደሚሆንልህ ካመንክለት አምልኮ ፈጸምክለት ማለት እሱ ነው።
በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ ዘጸ 20፣4
«የአምላካችንን ስም ረስተንስ ቢሆን፥ እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንሥተንስ ቢሆን» መዝ44፣20 ምን ይባላል?
ወንድሜ

አባቶቻችን ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ የሚሉት አይነት ሆንክብኝሳ። በቅድሚያ እኔ የመለስኩት ሁለተኛውን እንጂ የመጀመሪያው መላሽ እኔ አይደለሁም። ምናልባት የመጀመሪያው መላሽ መስዬ ከሆነ ተሳስተሃል። አስተያየትም ለእርሱ በመጀመሪያው መልስ ግርጌ እንጂ በሁለተኛው ማለትም በእኔ መልስ ግርጌ መጻፍ የለብህም። ሁለተኛው መልስ የእኔ ነው እናም እኔ ለጠያቂው መልስ ለሰጠው የሞክርኩት፤ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ነገር የለም፡ ስለዚህ ይህን የሚያደርጉ መጽኣህፍ ቅዱሳዊ አይደሉም ብዬ ለማለት ነው።

አንተ ደግሞ እኔ ራሴ ከጻፍኩት ሰውዬ ይበልጥ እኔ ምን እንደጻፍኩ ልትነግረኝ ስትሞክር ትንሽ እንደው ቅር አይልህም። እንዴት ሆኖ ነው እኔ ራሴው ከጻፍኩት የበለጠ አንተ እኔ ምን እንደጻፍኩ ልትነግረኝ የምትፈልገው? በምን ሂሳብ። ለምንስ ሃሳቤን እቀይራለሁ? ማንን ፈርቼ? በመጀመሪያም ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ነው የተናገረኩት ስለ ሌሎች አልተናገርኩም። አይ ተናገረሃል ወይም ደግሞ ለምን ተናገርክ ብለህ ድርቅ የምትል ከሆነ ነጥብህና ሃሳብህ ሊገባኝ አልቻለም። አሁን ሰዎች ማርያምን አያመልኩም አላልኩም። ይሄ እኮ ማስረጃ አያስፈልገውም። ምንም ማስረጃ መደርደር አያስፈልግህም። ማርያም የኦርቶዶክስና የካቶሊክ ሃይማኖት አንድ የእምነትና የአምልኮ ክፍል እንደሆነች ማንም የሚያውቀው ነው። እኔ ግን ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ነው ያወራሁት። እናም መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር የለም ማለት እንዲህ ያሟግታል እንዴ? በል ከአንተ ጋር ጨርሻለሁ።
0 ድምጾች
የሌላውን አገር ባላውቅም፣ መጸለይ የሚገባው ለአምላክ እንጂ ለሰው ባለሞሁ እንዲህ አይነቱ ጸሎት ከእውነተኛው አምለኮና ጸሎት መንገድ ህዝባችንን አስለቅቓል።

መጨምር የማያስፈልገውን ጨምረናል እና እግዚአብሄር እኛን እና አቦቶቻችን ይቅር ይበለን ምድራችንንም ይፈውስ።
Mar 2, 2012 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...