አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ላይ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ተብሎ የተጨመረው ለምንድን ነው መጽሀፍ ቅዱስ ላይ የሉቃስ ወንጌል 11
1 እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ። ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።
2 አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
3 የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤
4 ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን…..
ሆኖ ሳለ ታዲያ ለማርያም የተጨመረው ጸሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው ወይስ መላው የአለም ህዝብ የሚጠቀምበት ነው