ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ግብረ ሰዶማውያን በክርስቶስ አምነው ነገር ግን በምግባራቸው ቢቀጥሉ ይጸድቃሉ?

እባካችሁ በደንብ አብራሩልኝ?
Mar 1, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
[እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።..............እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም] ሮሜ 1፣26-32
ስለዚህ ወንድም ወይም እህት ጠያቂ ለባህርያቸው የማይገባውን የሚያደርጉ ሁሉ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎች እንጂ የእግዚአብሔር አማኞች አይደሉም።
ክርስቶስን ማመን ብቻውን ድነትን አያረጋግጥም። መዳን ማለት ያመንከውን እምነት በተግባር ስትገልጠው ነው። እምነትንማ አጋንንትም አላቸው። «እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፣አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?» ያዕ 2፣19-20
መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶምን (የሰዶም ሰዎችን ሥራ) ለማጥፋት እሳት ከሰማይ ማውረዱን በግልጽ ነግሮናል። «እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል» ይሁዳ 1፣7
ስለዚህ እንኳን ግብረ ሰዶማውያን ይቅርና በግብረ ሰዶማውያን ክፋት የእግዚአብሔር ቁጣ ለሀገርና ለምድራችን ቅጣትን ያስከትላል እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ ምህረትን አያመጣም።
ይህንን የሚፈጽሙት ወዮታ አለባቸው!
«የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፥ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ክፉ ነገርን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!» ኢሳ3፣9
Mar 1, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ሰላም
በክርስቶስ ማመን እኮ ሃጥያትኝነትን አምኖ መናዘዝ ነው።
ሃጥያቱን ተናዞ ለሚተዋት ለዛ ሀይወት የሆንለታል።
ጌታም ብትወድኝስ ቃሌን አድርጉ ነው ያለው።
ግብረ ሰዶማውያን የእግዚአብሄር ቃል የሚለውን አምነው ጌታን ተቀብለው ለመኖር ሃጥያትን መተው ያስፈልጋል ነገር ግን ጌታን አምናለሁ የፈልግሁትን አደርጋለሁ የሚል ነገር በእርግጥ አለማመናቸውን ነው የሚያሳየው። ቃሉ እኮ፦
" የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።" ኤፍ4፥28 ይህ ለሁሉም ነው ይቀደሞውን ሃጥያታችን ስንተው ነው እምነታችን የሚገለጸው።
ባሃጥያታችን ሳንተው በዛው ሰመላስ ለቤዛ የታተምንበትን የመዳናችን ዋጋ የተከፈልበትን እርግጠን መንፈስ ቅዱስን ዘግተን ይልባችን ፈቃድ እየፈጸምን ነው ከዘህም የተነሳ ለራሳችን ፈቃድ አሳልፈን እንሰጣለን። just sad!!!!
"ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።" ኤፍ4፡30
Mar 2, 2012 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
ግብረ ሰዶማውያን በክርስቶስ አምነው ነገር ግን በምግባራቸው ቢቀጥሉ በክርስቶስ አለማመናቸውን ነው የሚያሳየው።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...