ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መጽሀፍ ቅዱስ ላይ በሴት ሆኖ የተተነበየ ትንቢት ወይም ቃል በቀጥታ ከማርያም ጋር ይያዛል

ውድ ክርስቲያኖች ብዙጊዜ ግር የሚለኝን ጥያቄ መልስ ብትሰጡኝ ብዬ በማሰብ ጥያቄዬን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ በሴት ሆኖ የተተነበየውን ትንቢት ወይም ቃል በቀጥታ ከማርያም ጋር ይያያዛል ለምሳሌ ትንቢተ( ኢሳያስ ምዕራፍ 60 ቁ 12-15) ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።13 የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፥ ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ። የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
ለምሳሌ በሀገራችን ብዙ ታክሲዮች ላይ እንደምናገኛው የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ እንደሚለው ትንቢት እኔ እንደተረዳሁት ምንም ነገር ከእመቤታችን ጋር የሚያያይዘውን ስላላገኘሁ እባካችሁ ይህ በመጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ በሴት ሆነው የተጻፉት በሙሉ ማርያምን ነው የሚያመለክተው ወይስ ትክክለኛውን አለመረዳት እንደው አንዱን ጥቅስ ብቻ በማውጣት ለማርም ነው የተባለው ማለት ይቻላል እባካችሁ ምላሻችሁን ወይም መጽሃፍ ቅዱሳዊ ማብራርያችሁን ብትገልጹልኝ፡፡ አመሰግናለሁ
Mar 5, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 5, 2012 ታርሟል

2 መልሶች

0 ድምጾች
ከቅድስት ማርያም ጋር የሚያያዝ ትንቢት
ትንቢተ ኢሳያስ 7፥14 በብሉይ ኪዳን ብቻ ነው ይህም ።
ጽዮን የእስራኤል ከተማ እንጂ ሰው አይደልችም ትንቢቶቹ ለከተማይቱ ወይም በከተማዋ ላሉ ህዝቦች እንጂ ለ1 ሰው አይደልም።
Mar 5, 2012 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው ብሉይ ኪዳን(አሮጌው ኪዳን) የምንለውና ሁለተኛው ደግሞ አዲስ ኪዳን የሚባለው ነው።
ብሉይ ኪዳን የአካሉ ጥላ ነው። ጥላ ምንጊዜም ቢሆን የአካሉን ቅርጽ እንጂ ማንነት አያሳይም። ደግሞም ጥላ የሚኖረው ብርሃኑ ባልተገለጠበት ስፍራ ነው። ስለዚህም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ እንዲህ ያለው። ዕብ 10፥1
«ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም»
ይህ ብሉይ ኪዳን አገልግሎቱ «እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው» ተሰሎ 2፣17
ስለዚህ ብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር የተሰጠ የጥላው ማሳያና ወደአካሉ የሚመራ አመላካች እንጂ በራሱ ሕይወትን የሚሰጥ ትእዛዝ አልነበረም። ስለሆነም ከብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለማርያም የተነገረ የተብራራና በደንብ የተገለጸ ሳይኖር ይቅርና ቢኖርም እንኳን የአካሉ ገላጭ እንጂ በራሱ የመዳን ቃል ባልሆነ ጽሁፍ ውስጥ የሴት አንቀጽ እየፈለጉ ያንን በመተርጎም ወደማርያም ለማስጠጋት መታገል ቁም ነገር የሌለው ተግባር ነው። የብሉይ ኪዳንን ተልእኰ መዘንጋትና ወደአካሉ የምንደርስበትን መንገድ በመቀየር የመሪውን ፈቃድ በቃላት አውሎ ንፋስ ወደአልሆነ አቅጣጫ በመምራት እክል ማድረስ ይሆናል። ብሉይ ኪዳን ስለሙሴ፣ ስለአሮን፣ ስለኢያሱ፤ስለነገሥታት፣ስለነብያት ብዙ ተጽፏል፣ተነግሯል። እነዚህ ሁሉ የጥላው ሰዎችና ወደአካሉ እስክንደርስ በእግዚአብሔር ምሪት ለእኛ የተስፋው ቃል ወራሾች የተላኩ እነርሱ ግን በመተላለፍ ስር የነበሩ ናቸው።
«እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ» ገላ3፣29 ተብለናል።
ስለዚህ እኛ በክርስቶስ የተስፋው ቃል ወራሾች ከሆንን ሌላ ተስፋ የምናደርግበት ሰው የለንም። ከኢሳ 7፤14 በስተቀር ስለማርያም በስም ተለይቶ የተጻፈ ሳይኖር ይቅርና ብዙ፣ ብዙ ቢኖርም እንኳን በእግዚአብሔር አሠራር እያደነቅን የአዲስ ኪዳኑ አካል ወደሆነው ክርስቶስ « እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ» ኤፌ 1፣13 ከተባልንበት ውጪ ተስፋ በሌላ በማንም የለንም።
Mar 5, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
It really surprise me when Protestants and other dominations other than Catholics and Orthodoxs play down the importance of the Old Testament. forgeting the controveries about St. Mary. Where will you get the answer for how we are created, how the universe is created, who created the universe. I am sure you will see from the book of Genesis, then isn't the book of Genesis in the Old Testament?
On unrelated matter, I am atheist but I am influenced by Ethiopian Orthodox, The other day, One pastor was ridiculing Ethiopia Orthodox for believing the story of a saint who prayed on one foot. If an antheist tell me this, I will burst in laugh, However it was a pastor who most likely believed the story of Jesus walking on water. What is the difference? In the first story, it an African Saint, his story told by Blacks. In the second case, Jesus is Jew and white and his story has been told by white. We, Ethiopians, are poor. We don't have technology, but it doesn't mean we have nothing. If you believe Jesus walking of water story, there is no any reason for not believing about other Saints doing a miracle. anyways I don't believ in neither of them. but I appreciate the Ethiopian Orthodox for Africanizing Christianity.
Mr. Atheist, you must be kidding, ክርስቶስን ከሰው ጋር እወዳደርክ ነው። Did you say? you are influenced by Ethio- orthodox and that lead you to atheist? I am not surprised. instead you should read the word of God the whole Bible and find out for your self. "O taste and see that the LORD is good: blessed is the man that trusteth in him." psalm 34:8
I never said being influenced by teaching of Ethiopian Orthodox church lead me to be an atheist. I grew up in an Orthodox upbringing. For the past 10 years I found that religion is just a human creation and the Bible is just another old book, not a Holy book for me. I defended the Ethiopian orthodox church in lot of ways when other persons specially, Ethiopian protestant, start to attack it and when they considered it as backward. Can you convince me how Jesus is different from a person? I am sure that your source will be the Bible, but wait a minute,I consider it as any book. how is the Bible different from other books of orthodox church(mind you the orthodox church consider the Bible as the main holy book but I consider it as any book). I remember one person saying the book of Henok shouldn't be included in the Bible because it has lots of mistakes and my reply was there are also lots of mistakes in the 66 books. mistakes are mistakes. I don't believe in the story of Jesus walking on water and I don't believe in the story of an Ethiopian Saint praying in one leg for years. To be honest, praying in one leg can be achieved by balancing than walking on water which defies science. If I believe Jesus walked on water, there is no any reason not to believe another story.
The problem I have with you is dissing my God. Making HIM equal with human. But you know what? what should I expect from an atheist, who rather believe he come from ape than created in the image of God. well the Bible is not a myth believing in the word of God is a chose. you have made yours now you lie in it. The next time when you have deepest need don't forget to call on HIM. He is the loving and graceful God He will answer you and it may be sooner that you thought so be ready.
Be ye not unequally yoked together with unbelievers: for what fellowship hath righteousness with unrighteousness? and what communion hath light with darkness?
(2 Cor 6:14)
Believing is not a game of fantasy.

Now the end of the commandment is charity out of a pure heart, and of a good conscience, and of faith unfeigned:
From which some having swerved have turned aside unto vain jangling;
Desiring to be teachers of the law; understanding neither what they say, nor whereof they affirm. (1 Tim 1:5-7)
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...