ውድ ክርስቲያኖች ብዙጊዜ ግር የሚለኝን ጥያቄ መልስ ብትሰጡኝ ብዬ በማሰብ ጥያቄዬን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ በሴት ሆኖ የተተነበየውን ትንቢት ወይም ቃል በቀጥታ ከማርያም ጋር ይያያዛል ለምሳሌ ትንቢተ( ኢሳያስ ምዕራፍ 60 ቁ 12-15) ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።13 የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፥ ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ። የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
ለምሳሌ በሀገራችን ብዙ ታክሲዮች ላይ እንደምናገኛው የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ እንደሚለው ትንቢት እኔ እንደተረዳሁት ምንም ነገር ከእመቤታችን ጋር የሚያያይዘውን ስላላገኘሁ እባካችሁ ይህ በመጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ በሴት ሆነው የተጻፉት በሙሉ ማርያምን ነው የሚያመለክተው ወይስ ትክክለኛውን አለመረዳት እንደው አንዱን ጥቅስ ብቻ በማውጣት ለማርም ነው የተባለው ማለት ይቻላል እባካችሁ ምላሻችሁን ወይም መጽሃፍ ቅዱሳዊ ማብራርያችሁን ብትገልጹልኝ፡፡ አመሰግናለሁ