ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በአልጋ አንድ ከሆኑ ብኋላ ቢጋቡስ ምን ይሆናል እንደ ክርስቲያን

የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የእ/ር ቤተሰቦች ይህን ጥያቄ እኔ በአንድ ጓደኛዬ ተጠይቄ በቂ መልስ አልሆነልኝም ስላለችኝ ወደ እናንተ ለማቅረብ ተገደድኩ ፡፡ ጥያቄው እርስዋ እጮኛ አላት ለመጋባትም ወስነዋል ቸርችም አሳውቀዋል ግን ከመጋባታቸው በፊት በአልጋ አንድ ሆነዋል፡፡ ታዲያ ስለምንጋባ እኔም እሱም ወደሌላ ስለማንሄድ ሀጢያት አይሆንብንም ነው የምትለኝ ፡፡ እናንተስ ምን ትላላችሁ
Mar 8, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

5 መልሶች

+2 ድምጾች
የቤተ ክርስቲያን ጋብቻ የ እ/ግ አገልጋዮች እና የ እ/ግ ህዝብ ይባርከን ይጸልይልን ይወቅልን በማለት እርስ በራስ በቃልኪዳን መታሰር ነው። የሰርግ ሚስጥሩ ቤ/ክ ክርስቶስን በንጽህና ያለጭርምት ያለ ነውር መጠበቅዋ ነው የራሱ የሆነውን እንደሌባ መጥቶ ፍሬዋን አይበላም ነገር ግን እራሱን አሳልፎ የሰጠላትን ፍቅሩን እርሱ በክብር ተገልጾ እርሱአንም አክብሮ ወደራሱ መውሰዱ ነው። የወደፊት ሚስቱን የማያከብር እራሱን መግዛት ያቃተው ሰው የክርስቶስ ምሳሌ መሆን ያቅተዋል የክርስቲያኖች ተዳር ለ አለም የሚለየው የህ ነው ትልቁን ቁም ነገር እርስተውታል እ/ግ መምሰል ማትረፊያ እንጂ ኪሳራ አይደለም ።በመጀመሪያ 1ሰው ከ1ሴት ጋር ሲተኛ እራሱን እራስዋን በትዳር አስረዋል በእ/ግ ፊት አዳም እና ሄዋን ለሎችም ሚስቱን አወቀ ነው የሚለን ቃሉ ከዛውጭ የሚደረግ ነገር ሁሉ ግን ዝሙት ነው ሃጥያት ነው። ሚስቱን ካወቀቦሃል ግን ሰርግ ሰረግ አይልም። ሚስቱን ከማወቁ በፊ ግን በፊታችሁ ከርሱዋ ጋር ዘመኔን ሁሉ ለኖር በክፉ በደጉ በፍታችሁ ቃል እጋብላታለሁ/ህ ነው። የነሱ አሁን ቤ/ክ መሄድ ለሰርግ ለምን የሆን? በቅድስና ቆይተናል እና ባርኩን? እርሱ ውሸት ነው ሰው ለራሱ ዋሽቶ በ እ/ግ በህዝቡ ፊት ሊዋሹ???? የበደል በደል ነው ምስክርነታችን እኮ ጌታን ማሳያ ነው። የአዋቂ አትፊ ማለት የህ ነው። ለቤ/ክ ሄደው እኛ ቸኩለናል እንደእ/ግ ቃል መስክር የሚሆን ህይወት የለነም እና በህዝቡ ፊት መቆም አንችለም በደለናል በቅድስና አልተመላለስንም ጌታ ምህረት እዲያደርግልን ጸልዩልን ከ አሁን ቦሃል በፈታችሁ ቃል ኪዳን እንገባልን በልው መጠየቅ እና ለሰርጉ የሚወጣውን ገንዘብ ለሌላ ነገር አውለው በአገልጋዮች ፊት ቃልኪዳናቸው አድርገው አረፈው የኑሩ ባይ ነኝ። የምነረሳው ነገር አለ ያለመታዘዝ የራሱ የሆነ እርግማ አለው። Our life belong to God not to us. we need to live to honer HIM. By walking on our ways we never honor HIM. ይህን ከልብ በሆነ ጸጸት ውስጥ ሊያስገባን የገባል። ከልብ ከተጸጸቱ እና ይቅርታን ጌታን ከጠየቁ ግን እርሱ ሊምራቻው የታመነ ነው።
Mar 8, 2012 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 8, 2012 YaelD ታርሟል
0 ድምጾች
እኔ የምመክራቸው አንዴ መቼም ወድቀዋልና ለመጋባትም ተስማምተዋልና ምንም ጊዜ ሳይወስዱ ይጋቡ። ሆኖም ግን ይህንን ደብቀውና ዋሽተው በቤተክርስቲያን አያድርጉት። ይህ እርግማን ሊያመጣባቸው ይችላል። በመጽሃፍ ቅዱስ ለነገሩ በቤተክርስቲያን መጋባት የሚባል ነገር የለም። ስለዚህ ይሄን ያህል በቤተክርስቲያን ለመጋባት መዋሸትና ማታለል አያስፈልግም። ወገኖቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰብስበው ራሳቸው ሰርግ አድርገው ይጋቡ። አለቀ በቃ።

ሌላው የማስጠነቅቀው ለቤተክርስቲያን ሄደው ያደረጉትን ይናዘዙ የሚባለውን አልቀበልም። በሌላ ነገር ቢሆን ልክ ነው ነገር ግን በተለይ በሃበሾች ዝሙት ከሁሉ የተለየ የማይማር ኃጢአት ተደርጎ ስለሚቆጠር፤ ማንም ለዘላለም ይቅር አይላቸውም። እግዚአብሔርም እንኳን ይቅር ቢላቸው እንደ ክርስቲያን እስከ ወዲያኛውም አይቆጠሩም። በዚህ ላይ የሰው ህግና ሥርዓት የሆነ ከባድ ሸክም ሊጭኑባቸው ይችላሉ። ማለትም በቃ ቆዩ አንድ አመት አራዝሙ፣ ተረግዞ አልተረገዘ እንደሆነ ለማየት ቆይ አንድ ዓመት እንያችሁ ምናምን እያሉ ይባስ ወደ ሌላ ፈተና ሊጥሏቸው ይችላሉ። ስለዚህ ለቤተክርስቲያን ይህንን ኃጢአታቸውን መንገር ከጉዳት በስተቀር ምንም በመንፈሳዊ ህይወታቸው ላይ የሚጨምረው ነገር የለም።

ይልቁኑ በእግዚአብሔር ፊት ንስሃ ይግቡና ነገሩን ለራሳቸው ብቻ ይዘው ከቤተክርስቲያን ውጪ ሰርጋቸውን አድርገው ይጋቡ። መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ በቤተክርስቲያን የተጋባ አማኝ የለም። ማጋባትም የቤተክርስቲያን ስራ አይደለም። ሰርግ አድርጎ መጋባት የራሳቸው የተጋቢዎች ጉዳይ እንጂ ለቤተክርስቲያን የተሰጠ ሥራና ሃላፊነት አይደለም። ስለዚህ በቤተርክርስቲያን የግድ መጋባት አለብን ብለው መጨነቅ አያስፈልጋቸውም። እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ተጋቡ ወይም ቤተክርስቲያን ካላጋባች እኔ ትዳሩን አልቀበልም አላለም። መዋሸትና አታልሎ በመድረክ መቆም ግብዝነት ነው፤ እግዚአብሔርም ይጠላዋል።
Mar 8, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
+1 ድምጽ
ጋብቻ ማለት እናትና አባትን ትቶ በአንድ ጥላ ስር ፣አንድ ስጋ ሆኖ መኖር ማለት እንጂ በአንድ አልጋ ላይ መተኛት ማለት አይደለም።
« ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን?» ማቴ 19፣5
ይህ በአልጋ ላይ ከጋብቻ በፊት ተራክቦ መፈጸም ማንም በስጋ የሚኖር ያልዳነ ሰው ሁሉ የሚፈጽመው ተግባር ነው። በክርስቶስ አለሁ የሚል ይህንኑ ከፈጸመ ከስጋውያን መለየቱ ምኑ ላይ ነው?ለመጋባት ወስነዋል የሚለው ጥሩ ዜና ነው። ግን ደግሞ አልተጋቡም። ቤተክርስቲያኗም ጋብቻቸውን አልፈጸመችም። እናስ ከጋብቻ በፊት የስጋ ልምምድ ወይስ ከቤተክርስቲያን ጋብቻ በፊት የሚደረግ የሙከራ ጋብቻ? ጋብቻቸውን በነገሯት ቤተክርስቲያን በኩል እስኪያጸኑ ድረስ እነዚህ ሰዎች ሁለት ናቸው እንጂ አንድ አይደሉም።
አንድ ስጋ የሚሆኑት ጋብቻ ሲፈጽሙ ብቻ ነው።
«ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም» ማር 8፣10
ጋብቻቸውን የሚፈጽሙት መቼ ነው? ነገ? የዛሬ ወር? ወይስ የዛሬ ዓመት? እስከዚያስ ሙከራው ይቀጥላል? ይህ ጥሩ ያልሆነ ነገር ነው። እስከቀጠሮ ጊዜው መቆየት ያልቻለ ምነው በምኞትና በስጋ ፈተና ከመቃጠል ጋብቻቸውን አሁን የማያደርጉት? ላላገቡና ለመበለቶች እላለሁ እንዳለው ጳውሎስ
1ኛ ቆሮ 7፥9
ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ።
ለማንኛውም መጸለይ፣ የራስን ፈቃድ ለእግዚአብሔር መስጠት፣ መታገስ፣ ንስሃ መግባት መልካም ነው። ምክንያቱም «እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ» ሮሜ 8፣5 ስለተባልን በእኛ ያለው የአሸናፊው ኃይል ለሥጋ ፈቃድ እንድንሸነፍ አይተወንምና በእሱ ላይ እንጣበቅ!!
Mar 8, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
በርግጥ ይህ ነገር መልካምና ምቹ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን ጥያቄው ከጋብቻ በፊት ግንኙነት እንጀምር ሳይሆን ጀምረናል የሚል ነው። ይህን እንደ ዴኖሚኔሽን ዶክትሪን ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ስንመልሰው እንደሚከተለው ይሆናል።
1ኛ፤ በብሉይ ኪዳን የነበረው ህግ እንደሚያዘው ከሆነ አንድ ሰው የሌላውን ሚስት ወይም እጮኛ በግብረ ስጋ ቢገናኝ ተስማምተው ከሆነ ሁለቱንም ፥ አስገድዶ ከሆነ ደግሞ ወንዱ ብቻውን ይወገርና ይሙት ነው የሚለው። አስተውሉ፤ ይህ እንግዲህ ያገባችውን ወይም የታጨችውን ነው ሚለው።
2ኛ፤ ሁለት ለማንም ቃል ኪዳን ወይም የጋብቻ ትስስር ያላደረጉ ወንድና ሴት በግብረ ስጋ ቢገናኙ እንደላይኞቹ ይወገሩ ሳይሆን የሚለው ይጋቡ ብሎ ነው የሚያዘው።
3ኛ፤ በአዲስ ኪዳን መጀመሪያ ላይ የምናገኛቸው እጮኛሞች ማርያምና ዮሴፍን ነው። እንግዲህ ማርያምን ጻድቅ ሆኖ ሊያጋልጣት አልፈለገም የሚለን ሁለቱ ግንኙነት ሳያደርጉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸንሳ በመገኘቷ ነው። ከዚህ ክፍልም የምንረዳው ቢኖር ግንኙነት ኣድርጋ የጸነሰችው ገና ካልተጋቡት ከ እጮኛዋ ከዮሴፍ ቢሆን ኖሮ በርሷ ላይ የሚደርስ ፍርድ አይኖርም ማለት ነው። ነገር ግን መልአክ ለዮሴፍ ጌታን እንደጸነሰች ነግሮት ነው አምኖ የተቀበለው።
ስለዚህ ምንም እንኳን በእጮኝነት ሳሉ ተከባብረው ራስን በመግዛት እስከጋብቻ ቀን እንዲታገሱ ብመክርም ለእነዚህ ወንድምና እህት የምመክረው በቶሎ እንዲጋቡ ነው። ጋብቻቸውን እስካጸኑ ድረስ ስለ ሰው ወግ ሲል ጌታ አይረግማችሁም። ግንኙነት ካደረጋችሁባት ቀን ጀምሮ አንድ ስጋ በጌታ ፊት ኦናችኋልና ባልና ሚስቶች ሆናችኋል። ባታገባት ግን ከዚህ ሃጢኣት የተነሳ ዋጋ ትከፍልበታለህ። ምክንያቱም ወደ ሞኞች ሴቶች ሾልከው የሚገቡና የሚያታልሉ ወንዶች እንዳሉና ጌታም እንደሚበቀላቸው ተጽፏልና። ሴቶችም ቢሆን እንደ ኤልዛቤል በዝሙት ሱስ ፥ እንደደሊላ ወንዶችን በማሳት የምታጠምዱ ከሆነ የጌታ ቃል ጋለሞታ ይላችኋልና ከጋለሞታነት ተጠበቁ። ወንዶችም ስለጋለሞታ ክፋት ከመጽሃፈ ምሳሌ አንብቡ። በቤተ ክርስትያን ብዙ ጋለሞቶችና ውሾች አሉ። የእግዚኣብሔርን መንግስት አይወርሱም። ስለዚህ ወንድሜና እሕቴ ከነዚህ ኃጢአታቸው ካልተገለጠ ጋለሞቶች እናንተ ንጹሃን ናችሁና ጋብቻችሁን ቤቃል ኪዳን አጽኑ ብዬ እመክራለሁ። ጌታ ይባርካችሁ።
Apr 23, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ጥያቄውን ስመለከተው ሁለቱ ሰዎች በሁኔታ ተሳስተው የአንድ ቀን ክስተት ተፈጥሮ የተጨነቁ አይመስሉም። ነገር ግን አመለካከታቸው አንዳቸው ከአንዳቸው ውጪ እስካልሄዱ ድረስ ችግር የለውም ብለው ነው የተቀበሉት። ጥያቄውን ሥለ ጋብቻ በአጭሩ በማብራራት ልጀምር።

በመጀመሪያ ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም ማለት ጋብቻ ማለት አይደለም። ጋብቻ ለመሆን ሁለት ደረጃ ይቀረዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመለከት በጋብቻ ውስጥ እግዚአብሔር ያስቀመጠው የራሱ የሆነ መደዳ (ፓተርን) አለው። እርሱም
1- እናትና አባትን መተው
2- ከትዳር ጓደኛ ጋር መተባበር
3- አንድ ስጋ መሆን ናቸው።

አንድ ሥጋ መሆን በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንጂ መጀመሪያው አይደለም። በሌላ አገላለጽ ሰው እናትና አባቱን ሳይተው፣ ከትዳር ጓደኛው ጋር ሳይተባበር፣ አንድ ሥጋ በመሆን መጀመር የእግዚአብሔር መንገድ አይደለም። በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ የምንመለከተው ሰው ከእግዚአብሔር መንገድ ውጪ ሲሄድ መጨረሻው አያምርም።

በሌላኛው አንጻር ግን ይሄንን መደዳ መከተል ጥቅም አለው። ከእናትና ከአባት ጥላ ሥር መውጣት ሃላፊነትን መሸከምንና የራስ ቤተሰብን መመስረትን ያመላክታል። ከትዳር ጓደኛ ጋር መተባበር መሰጠትን (ኮሚትመንትን) ያሳያል። እነዚህ ሁለቱ ያለበት ትዳር ሁልጊዜም የጸና ነው። አንድ ሥጋ መሆን ሥጋዌ ሩካቤ ሲሆን በትዳር ውስጥ የጠለቀ የሥሜትንና የአካል መተሳሰርን እንደሚፈጥር ሳይንስም ያረጋግጣል። ይሄንን መደዳ ተከትሎ የተደረገ ግንኙነት እርካታውም ይጨምራል። በዚህ መሃል የሚፈጠሩ ልጆችም ተስማሚ ቤተሰብ ይኖራቸዋል።

በእነዚህ እጮኞች መካከል በቀላሉ የምመለከተው ችግር እራሥን ያለመግዛት ችግርን ነው። እስከ ትዳራቸው ቀን ድረስ ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ሳይፈጽሙ እራሳቸውን ገዝተው መቆየት አቅቷቸዋል። ሃጥያት የሚያድግ ነገር ነው። በምኞት ጀምሮ እስከ መግደል ያድጋል። የተመኘ ለታ ሞተ አይልም ነገርግን ካደገ ይገድላል። በዚህኛውም ስናይ ዛሬ ከእጮኛ ጋር እራሥን ያለመግዛት ችግር ካልተስተካከለ ነገ አድጎ ከሌላ ሰው ጋርም እራሥን ያለመግዛትን ችግር ያመጣል። ያደግሞ የነገውን ትዳር ወደመፍረሥ ያደርሰዋል። ምክንያቱም በትዳር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳያመነዝሩ የሚኖሩት በሌላ ሰው ሳይፈተኑ ቀርተው አይደለም ነገር ግን ፈተናው ሲመጣ እራሳቸውን ገዝተው ለፈተናው እምቢ ስለሚሉ ነው። ዛሬ የወሲብ ስሜትህ/ሽ ወደ እጮኛህ/ሽ ሲገፋህ/ሽ እምቢ ማለት ካልቻልክ/ሽ ነገ ይሄው ስሜት ወደሌላ ሰው ሲገፋ እምቢ ማለት አይቻልም።

ሥለዚህ ለእነዚህ እጮኛሞች የምመክረው ዛሬ እራሳቸውን መግዛት እንዲለማመዱ ነው። ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ “እግዚአብሔርን ለመምሰል እራስህን አስለምድ” እንዳለው ስሜታቸውን መግዛትን ለራሳቸው ከዚህ ነገር በመታቀብ እንዲያስለምዱ እመክራለሁ። ያለዚያ ነገ አድጎ የተበላሸ ትዳርን ያመጣባችኋል። እሺ ብትሉ ግን የእግዚአብሔር ምህረት ዛሬም ጽኑ ነው።
May 14, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
May 14, 2012 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...