ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መንፈሰዊ እና ማህበራዊ ድህረገጾች Facebook and others ላይ ህዝቡን የሚያጭበረብሩ

መንፈሰዊ ነን እያሉ በተለያዮ ማህበራዊ ድህረገጾች Facebook and others ላይ ህዝቡን የሚያጭበረብሩ እና ለብዞዎች ትዳር እና ዕጮኝነት መፍረስ ምክንያት ስለሚሆኑት ሴቶች እና ወንዶች በመንፈሳዊያን እይታና በመጽሃፍ ቅዱስ ወይም አንድ መንፈሳዊ ሰው እጮኛውን ወይም እጮኛዋን ሚስቱን ወይም ባልዋን አስቀምጣ ከተለያዩ ግለሶቦች ጋር በሚስጥራዊ ድህረገጽ አላስፈላጊ ነገሮችን በመፈጸም ትዳራቸው ወይም ግንኙነታቸው የተቋረጠ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ ለምሳሌ በሀገራችን በተለያዩ መጽሄቶች ላይ ብዙ አንብበናል ባሌን ወይም ሚስቴን በዚህ ምክንያት ልፈታ ነው፡፡ እጮኛዬ ከእኔ ጋር 5 እጮኞች አሉት በድህረገፆች የያዛቸው ስለዚህ ምን ላድርግ ልንገረው ወይም አልንገረው እያሉ የሚጨነቁ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ ታዲያ እነዚህን አይነት መንፈሳዊ ነን እያሉ ሰዎችን ለመሳብ የሚያጭበረብሩ ግን የሰውን ህይወት የሚበጠብጡትን ክርስቲያን ነን ባዮችን ተግባርን እንዴት ታዩታላችሁ፡፡
Mar 14, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
የህንን የፌስቡክን ጉዳይ ሳነብ አስተያየት ላለመስጠት በጣም ወስኜ ነበር ነገር ግን እኔም የጉዳቱ ተጠቂ በመሆኔ እንደው ለናንተ ትምህርት ቢሆን በማለት እስኪ እንደሚሆን እደሚሆን ልንገራችሁ፡፡ እኔ እህታችሁ እጮኛ /የትራዳር አጋር አገኘሁ ብዬ ልቤ እስኪወልቅ ስለፋ ስደክም ለበርካታ ወራቶች አበረን አሳለፍን እንደክርስቲያን አስፈላጊ ለሆኑ የቤተክርስቲያን አባላት አስታወቅን ፡፡ በሠላም እየተጓዝን እኔም እሱም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ነበርን ከዛ ግን አቋረጥን በስምምነት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አጅሬው እጮኛ እራሱን በጣም በክርስትና የሰቀለ እጸልያለሁ፣ እዘምራለሁ አገለግላለሁ እያለ የሚታትር አስመሳይ ክርስቲያን ግን ውስጡ ለካ የመጥፎ የዝሙት መንፈስ ማስፋፊያ ነበርና እና እኔ ሳላውቅ ከበርካታ ሴቶችች ጋር በተለያዬ ማህበራዊ ድህረገጾች ይገናኛል ፣ ይደዋወላል፣ አብሮም ጊዜን ያሳልፋል፡፡ እኔ ጋር እሱ በጣም ክርስቲያን ነው ምን ልበላችሁ ስለሱ መጥፎ ማሰብ አትችሉም መጨረሻ ግን ጉዱ ሲወጣ ይባስ ብሎ የኔኑ ጓደኛ ሲጀነጅን ብይዘው ደህንነት ላስተምራት ነው አለኝና አረፈው ፡፡ ሌላው በሰበብ አስባብ የጋብቻችነን ጊዜ ሲያራዝም የነበረው ለካ በዚሁ ከበርታካ ሴቶች ጋር በጀመረው ግንኙነት ምክንያት ነበር ፡፡ ሆኖም ግን ጊዜዮንና እድሜዬን ለ2 ዓመታት ያህል አባክኖ ተለያን ቤተክርስቲያንም አሳወቅን ፡፡ አሁን ይሀው ጓደኛዬ የኤች አይቪ በሽተኛ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ነበር አሁን ተነስቶ የተለመደ ስራውን በፌስ ቡክ ቆንጆዎችን ለመጨረስ ወስኗል፡፡ ለማጋለጥ ግን ድፍረቱን አጣሁ ምን ትመክሩኛላችሁ
ትእግስት፡

5 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም
ይህ ከአለማዊ እንኻን የማይጠበቅ ነው። ይህን ሰው/ሴት ጌታን እደማያውቅ ፍርሃ እግዚአብሄር እደሌለው መቁጥር ተገቢ ነው። ሰው ሰራ ማን ነቱ ይተርካል እና
በቻል ሰውዬውን/ሴትዬዋን ብግል መምከር ካልሆነ ሌሎችን ጨምሮ አብሮ መምከር እንቢ ካለ ደግሞ በዘህ ነገር አብረው ለተሳሰሩት በግልጽ መናገር እና ቤተክርስቲያ እድትገስጸው ማድረግ እንደቃሉ መረማመድ ነው እና ።እንዲህ አይነቱ በደል አንድ ሰው ብቻ ሳይሆን የክርስቶስ አካልን ነው።

ማቲ18፡ 15-17 "ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።"
Mar 14, 2012 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ፋስቡክ ሆነ ሌላ ኮምኒኬችን የምናደርግባቸው ድህረግጽ ሲመሰርቱ ልጥሩ ነገር ተብለዉ ነው ግን የሰውልጅ ሰው ስለሆነ የክፍትን ነገር ይመርታል ዳግም ካልተውለደ በስተቅር የፋስቡክ ነገር በሃሁኑ ግዘ ብዙ ሃወዛጋቢ ነገር ፍጥሮዋል ብዙ ይምንሰማቸው የምናያችው ድርጊቶች እየትፈጽሙ ይግናሉ ብዙዎችም ሲታለሉ አይተናል ሰምተናል ከትዳር መፍታተ ጀምሮ እስከሌላም ድርስ ክርስቲያነን ብለዉ በክርስቲያን ስም ልሚሰሩ ከአንድ ክርስቲያን የማይጠበቅ ድርጊት ነው እንደዚ ለሚያርጉ ሰወች የእግዚያብአርን ስራ እያፈረሱ መሆኑን ማወቅ አለባቸው ቤተሰበ ፈረሰማለተ አንድ ቤተክርሰቲያን እንዳፈረሱ ይቁተሩት በሌላ መልኩ ደግሞ የዳቢሎስን እቅድንና አላማዉን ማከናወኣ እቃ ይሆናሉ ማለት ነው እባካቹ ፋስቡክን ሆነ ሌላ ድረግጽ ለሚጤቀሙ ሰወች የጌታን ስራ ስሩብት!
Mar 16, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
አዎ ይህ የስራ ፈቶች መድረክ ነው መሰለኝ እኔ እንኳን አልጠቀምም ገን ጓደኞቼ ስራቸውን ፈተው እዛ ላይ ተተክለው ከተለያዩ ሴቶች ጋር ሲጀናጀኑ ይገርሙኛል ፡፡ ደግሞ እኮ አንዱ ባለትዳርና የ1 ሴት ልጅ አባት ነው ላፕቶፑን ታቅፎ ነው የሚውለው እኔ እንጃ እኔም ልግባ እንዴ!! አላደርገውም የስህተት ባህርማ አልገባም
አዎ በተለይ ፊስቡክማ እያሳሳቀ የሚወስድ ውሃ ነው!!!! በተለይ ለስጋዊያንማ እንዲትይመቻል! ለመጥቀምም ሆነ ለመተቀም መንፈሳዊ አቅምን ይጤይቃል!!!!
0 ድምጾች
Please see those links if you wont about Facebook and other social network

http://www.youtube.com/watch?v=okG8CqLk1KY
http://mashable.com/2010/04/10/facebook-dating/
http://www.nbcbayarea.com/blogs/press-here/Facebook-Causes-Divorce-121123344.html
Mar 16, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የህንን የፌስቡክን ጉዳይ ሳነብ አስተያየት ላለመስጠት በጣም ወስኜ ነበር ነገር ግን እኔም የጉዳቱ ተጠቂ በመሆኔ እንደው ለናንተ ትምህርት ቢሆን በማለት እስኪ እንደሚሆን እደሚሆን ልንገራችሁ፡፡ እኔ እህታችሁ እጮኛ /የትራዳር አጋር አገኘሁ ብዬ ልቤ እስኪወልቅ ስለፋ ስደክም ለበርካታ ወራቶች አበረን አሳለፍን እንደክርስቲያን አስፈላጊ ለሆኑ የቤተክርስቲያን አባላት አስታወቅን ፡፡ በሠላም እየተጓዝን እኔም እሱም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ነበርን ከዛ ግን አቋረጥን በስምምነት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አጅሬው እጮኛ እራሱን በጣም በክርስትና የሰቀለ እጸልያለሁ፣ እዘምራለሁ አገለግላለሁ እያለ የሚታትር አስመሳይ ክርስቲያን ግን ውስጡ ለካ የመጥፎ የዝሙት መንፈስ ማስፋፊያ ነበርና እና እኔ ሳላውቅ ከበርካታ ሴቶችች ጋር በተለያዬ ማህበራዊ ድህረገጾች ይገናኛል ፣ ይደዋወላል፣ አብሮም ጊዜን ያሳልፋል፡፡ እኔ ጋር እሱ በጣም ክርስቲያን ነው ምን ልበላችሁ ስለሱ መጥፎ ማሰብ አትችሉም መጨረሻ ግን ጉዱ ሲወጣ ይባስ ብሎ የኔኑ ጓደኛ ሲጀነጅን ብይዘው ደህንነት ላስተምራት ነው አለኝና አረፈው ፡፡ ሌላው በሰበብ አስባብ የጋብቻችነን ጊዜ ሲያራዝም የነበረው ለካ በዚሁ ከበርታካ ሴቶች ጋር በጀመረው ግንኙነት ምክንያት ነበር ፡፡ ሆኖም ግን ጊዜዮንና እድሜዬን ለ2 ዓመታት ያህል አባክኖ ተለያን ቤተክርስቲያንም አሳወቅን ፡፡ አሁን ይሀው ጓደኛዬ የኤች አይቪ በሽተኛ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ነበር አሁን ተነስቶ የተለመደ ስራውን በፌስ ቡክ ቆንጆዎችን ለመጨረስ ወስኗል፡፡ ለማጋለጥ ግን ድፍረቱን አጣሁ ምን ትመክሩኛላችሁ
ትእግስት
Mar 16, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
ምን ትጠቢቂ አለች የሌሎች ህይወት እስኪበላሽ ነው ወይ? ጌታስ ምን ይልሻል ሃጥያትን /በደልን አውቀሽ ዝም ስትይ?
ወንድሜ ሆይ የሚያደርጋቸውን ነገሮች በጥንቃቄ እያሰባሰብኩ ነው በዚህ ድህረገጽ ብቻ ሳይሆኑ አሉ በተባሉ ክርስቲያ መጽሄቶች ላይ ለማውጣት አስቤአለሁ ገን ከዚህ ድርጊቱ እንዲያቆም በየጊዜው በማስጠንቀቅ ላይ ነኝ፡፡ የሚገርማችሁ ቸርች በየወሩ ይቀይራል ዛሬ እዚህ ነው ስትል ነገ ሌላ ቦታ ነው በጣም በየሚሄድባቸው ቸርቾች አገልጋይ ቢጤ ነው በተለይ በልግስና ያለውን ገንዘብ በመስጠት የሚሆነው ያዲያ ይህን እኔው ራሴው ካላጋለጥኩ ማንም አያውቅበትም ፡፡ ጸልዩልኝ
ትእግስት
0 ድምጾች
አሂሂ ለዚህ እንኳን እኔ መልሴ የሚሆነው መንገድ የሚከፍቱት የኛው ኢትዮጵያዊ ሴቶች ናቸው የሚገርማችሁ በፌስ ቡክ ላይ እኔ የእግዚአብሔር መንግስ አገልጋይ ነኝ፣ ኳየር ነኝ ……….ብላ ትዘረዝረና ፓስት የምታደርገው ፎቶ ግነ የቡና ቤት ሰራተኛ ነው የምትመስለው እእእእእ እእ ይዘገንናል እነአጅሬ አገልጋይ ነኝ እያልሽ ሞዴል የመሰለውን ፎቶሽን ለጥፈሽ የስንቱን እጮኝነትና ትዳር የሚትበጠብጡ የፌስቡክ ሰቴቶች አስቡበት!!!!!!!!!
Apr 6, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...