ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ሰላም ለአናንተ ይሁን

በብሉይ ዘመንና በአዲስ ኪዳን ዘመን ስላሉት ነብያት ልዩነት ላኩልኝ በአዲስ ኪዳን ያሉት ነብያት በበለጠ አገልግሉታቸው አንዲት መሁን አዳልለበት ላኩልኝ ተባረኩ!
Mar 21, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ስለ ነብይ ምንነት፣ማንነትና አገልግሎት በዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን ብዙ እያከራከረ ይገኛል። የብሉይ ኪዳን ዘመን ነብይነት ግን ብዙም አያከራክርም። በሁሉም ዘንድ ማለት በሚቻልበት ደረጃ ሃሳቡና ትርጉሙ የጋራ ተቀባይነት አለው። ከሥነ መለኰት ምሁራንና ሚዛናዊ አስተምህሮ ካላቸው ሊቃውንት ዘንድ ያለንን ግንዛቤ የተሻለ ምላሽ እስክናነብ ድረስ ለመግለጽ እንሞክራለን።
ነብይ ማለት ምን ማለት ነው?
የግሪኩ «ፕሮፌሚ» ቃል ሲሆን ትርጉሙም «አስቀድሞ መናገር» ማለት ነው። ይህም ትንቢቱ ከመፈጸሙ በፊት ትንቢቱ ለተነገረለት ሕዝብ የትንቢቱን ምንነትና የፍጻሜ ሂደት አስቀድሞ ማሳወቅ ወይም ማስተላለፍ ነው።
ብሉይ ኪዳን
ነብይነት ለምን አስፈለገ?
የነብይነት አገልግሎት የተፈለገው የመጀመሪያው ሰው አዳም ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ነው። እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት የተቋረጠ ስለነበር እግዚአብሔር መልእክቱን «አስቀድሞ መናገር» ፕሮፌማ ሰው ስለፈለገ ለዚህ አገልግሎት ከሰው መካከል በመምረጥ ነው ነብይነት የተፈገለው።
መልእክቱ የሚተላለፍበት መንገድ፣
በራእይ፣ በህልም፤ በድምጽና በምልክት ሊሆን ይችላል።
«እርሱም፦ ቃሌን ስሙ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ» ዘኁ 12፤6
«እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው እርሱም፦ እነሆኝ አለ»1ኛ ሳሙ3፣4
«እርሱም፦ በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ፥ የምትናገረኝም አንተ እንደ ሆንህ ምልክት አሳየኝ»መሳ 6፣17
ኢሳይያስ ራእይ አይቶ፣ ኤርምያስ ቃል ሰምቶ፣ሕዝቅኤልም ዳንኤልም ራእይ አይተው ነብይነታቸውን ፈጽመዋል። ሌሎቹም እንዲሁ!
እንግዲህ የብሉይ ኪዳን ነብያት ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ሸክም ወደሕዝቡ በማድረስና የሕዝቡንም ጩኸት ወደእግዚአብሔር በማድረስ የነብይነት አገልግሎታቸውን መካከለኛ ሆነው ፈጽመዋል።
የአዲስ ኪዳን ነብያትስ?

እንግዲህ ነብይ ማለት ምን እንደሆነ፣ ነብያትም ምን እንደሚሰሩና መልእክት እንዴት ተቀብለው ያስተላልፉ እንደነበር ከላይ ካየነው አንጻር ስለአዲስ ኪዳን ዘመንም ጥቂት ልንል የተገባ ነው።
የአዲስ ኪዳን ነብይ ማነው? ነብይ ሆኖ የተመረጠው በማነው? የሚናገረው መልእክት ምንድነው? ብለን እንጠይቃለን። የአዲስ ኪዳን ነብይነት ችግር የሚከሰተው እዚህ ላይ ነው። በአዲስ ኪዳን ነብይ ስለመኖሩ የተጻፈ ቢኖርም አጠቃቀሙና አገልግሎቱ በሰፊው የተብራራ ስላልሆነ እኔ ነብይ ነኝ፣ በኛ ዘንድ ነብይነት አለ፣ የተመረጥኩት ለነብይነት አገልግሎት ነው ወዘተ የሚሉ ድምጾች ከዚህም ከዚያም ይሰማል። ለምሳሌ The later Day Saints ወይም «የኋለኛው ቀን ቅዱሳን» የእምነት ተቋማት የጆሴፍ ስሚዝን ነብይ መሆን ለዚያውም ብቸኛው ነብይ እንደሆነ ከተከታዮቹ ውጪ ለዚህ አገልግሎት የተመረጠ እንደሌለ ሲናገሩ እንሰማለን። በጽሁፎቻቸውም ይህንኑ ይናገራሉ።
ነብይ ማለት«ፕሮፌማ» ወይም አስቀድሞ የሚናገር ከሆነ ስለምን አስቀድሞ ለመናገር? ለማን ለመናገር? የቀረ ነገር ምን ስለነበረ? ብለን ብንጠይቅ ምላሽ የላቸውም።
የኢየሱስ ክርስቶስን የነብይነት ቦታ ለመቀበል ራሳቸውን በመሾምና በስህተት ቦታ ለማስቀመጥ የመጡ ከመሆን አያልፉም።
ኢየሱስ ራሱ ነብይ መሆኑን ተናግሯል።
«ነቢይ በገዛ አገሩ እንዳይከበር ኢየሱስ ራሱ መስክሮአልና» ዮሐ 4፣44
የኢየሱስ ነብነት፣
ራሱ የእግዚአብሔር መልእክት ነበር።
«ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ»ዮሐ 16፣28
መልእክቱ የመጣው ለተወሰነ ሕዝብ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ነው
«የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል»የሐዋ 2፣21
መልእክቱ ማዳን ነው።
«ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና» ሉቃ2፣11
ከዚህ ተነስተን ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ነብይ መባል የተገባው ከመሆኑም በላይ መካከለኛነቱ እንደኦሪቱ ነብያት በመናገር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ማዳንንም በመፈጸም ጥልን አፍርሶ እርቁን የመሰረተ በመሆኑም ጭምር ነው።
በቤቱ ላይ እንደሙሴ ታማኝ ሎሌ ሳይሆን የታመነ ልጅ ሆኖ ያገለገለው ኢየሱስ ነው።
ዛሬ ያሉ ነብያትስ?
በአዲስ ኪዳን ነብይ ነኝ የሚል ካለ ነብይነቱ ለቤተክርስቲያን መታነጽ መዋል አለበት።
1/ እሱ ነብይ እንጂ አስተማሪ አይደለም። የተቀላቀለ አገልግሎት አይደለም።አገልግሎቱ የተለየ ስለመሆኑ ተቀምጧል።
እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል» 1ኛ ቆሮ 12፣28
«እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፣ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ» ሮሜ 12፣6
2/ የነብይነቱ መልእክት በሌሎች የተመረመረ መሆን አለበት።
ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ደግሞ የተነገረውን በጥንቃቄ ይመርምሩ 1ኛ ቆሮ14፣29 ተመርምሮ ትክክለኛ ስለመሆኑ ያልተረጋገጠ ትንቢት ከስህተት መንፈስ ሊሆን ይችላል።
3/ በልሳን መናገርና ትንቢት መናገር በተለያየ ሁኔታ ውስጥ መፈጸም ያለባቸው ስጦታዎች ናቸው። 1ኛ ቆሮ 14፣22-25
ባላመኑ ሰዎች መካከል በልሳን መናገር እብድ ያሰኛል እንጂ ያላመኑትን አያንጽም። ስለዚህ በልሳን መናገር ያመኑ ሰዎች ባለበት ብቻ መሆን አለበት፣አለበለዚያም ይተርጎም!
እንደዚሁ ሁሉ ትንቢት መናገር ባላመኑ ሰዎች መካከል ከሆነ የልባቸውን ሃሳብ በመመርመርና በመግለጥ ስለሚገለጽ ያላመኑትን ሰዎች ያንጻል። ስለዚህ ትንቢት ባላመኑ ሰዎች መካከል ይፈጸም፣ ባመኑ ሰዎች መካከል ከሆነ ትንቢቱ ይገለጥ።
ስለዚህ ይህንን ያላሟላ ትንቢት፣ ትንቢት አይደለም።
4/ትንቢት እጅን በመጫን የሚሰጥ ጸጋ እንጂ በምርጫ የሚይዙት አይደለም። 1ኛ ጢሞ 1፣14
5/ ትንቢት የሚናገር እንዳለ ሁሉ የትንቢቱን መንፈስ የሚለይ መኖር አለበት።
«ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል» 1ኛ ቆሮ 12፣10
6/ በኢየሱስ ስም ትንቢት የተናገሩ ሁሉ እውነተኞች ናቸው ማለት አይቻልም።
«በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል» ማቴ 7፣22
በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያን መካከለኛነት ሳይሆን መታነጽና መስፋት አገልግሎት የሚጠቅም የነብይነት አገልግሎት ያለ ቢሆንም አጠቃቀሙ ላይ የሚታዩ ግድፈቶች መንፈስ ቅዱስ ለቤተክርስቲያን ያለውን ጸጋ ሰዎች በአግባቡ እንዳይጠቀሙ አስቸጋሪ አድርጎታል። እኛም.............እንዲህ እንላለን።
«ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና» ዮሐ 4፣1
Mar 22, 2012 ብርሃን (1,840 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...