ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ቃኤል ወንድሙን ገሎ ሲሄድ ያገኙኝ ሊገለኝ ይችላሉ ያለው ከየት የመጡ ሰወች ናቸው

ኦሪት ዘፍጥረት 4፡14
አነሆ፡ዛሬ ከምድር እባረርከኝ ከፊትህም እሰወራለሁ በምድርም ላይ ስደተናና ተንከራታች እሆናለሁ እንግዲህ ማንም ሰው ቢያገኘኝ ይገለኛል
Mar 7, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
መጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረት ሂደት ከመጀምሪያ እስከ መደምደምያው ድረስ ቁልጭ አድርጎ ይነግረናል። እግዚአብሔር ከአዳምና ከሔዋን ሌላ ሰዎች አልፈጠረም። ቃኤል ከየት እንዴት እንደምጣ ባይገባውም አቤል ታናሽ ወንድሙ ተወልዶ በቤተስቡ ውስጥ አብሮት ሲያድግ አይቶታል። ያዩኝ ሁሉ ይገድሉኛል ባለበት በዚያን ጊዜ ከወላጆቹና ውንድሙ በስተቅር ሌላ ሰው ስላልነበር አያቅም ነበር።

ይህ ጥያቄ በዘፍጥርት 2፡7 ላይ እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ክምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ የሚልውን ቃል እንድናይ ያደርገናል። ቃኤል "መግደል" የሚባል ነገር ጭራሽ አይቶም ሰምቶም አያቀም ነበር ግን አዳምን በማሳት የእግዚአብሔር መልካም ዕቅድን ያበላሸው ጠላት አሁን እንደ ፈለገው እንዲሰራ ዕድል አግኘ በተለያዬ መልኩም ይፈትናቸው እንደ ነበረ የኛውን ሕይወት ማሰብ ይበቃል።

ታድያ ከፍ ብለን ያነበብነው ጥቅስ የሚነግረን ሁላችን የምናውቀው ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳለው ነው ይህም መንፈስ ከክፉ ስራ ጋር አይተባበረም ምክንያቱም የቅዱስ እግዚአብሐር መንፈስ ስለሆን። ከዚህ በፊትም አባቱ አዳም "ድፅህን ሰማሁ ዕራቁቴን ስለ ሆንሁ ፈራሁ ሲል ለእግዚአብሔር ገና ከገነት ሳይባረር መልስ ሰጥቶአል። ቃኤልም ያለው በውስጡ የነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ መተላለፉን ስላሳዬው ነው ክጭንቀት በዛት የመጣ ነው አስባለሁ።

ቢሆንም የሚገድል ሰው ብቻ እንዳልሆነም ማሰቡ በጣም ተገቢ ነው። አራዊቶችም ዓይን አላቸው ያያሉ። ያ የእግዚአብሔር ነብይ የተባለውን ትንቢት ተናግሮ ሲመልስ እግዚአብሄር የሰጠውን መስጠንቀቂያ ችላ ብሎ ሆዱን ለሞምላት ጎራ ብሎ ሲመልስ እመንገድ ቆይቶ አንበሳው አህያውን ትቶ እሱን ገድሎ ነው መንገድ ዳር የተወው። አባቶቻችን ሲቀፈኝ የሚሉት ጉዳይ ህሊና ሲወቅስ ነውኰ። ሰው ከህሊናው ጋር ቢስማማ ይህች ምድር እንዴት ያለች ቆንጆና መልካም የቫከሽን ቦታ ትሆንልን ነበር። አሁንም በተለይ አማኞች ህሊናችን የሚለንን ቀይ መብራቱን ሲያበራብን መጣሱ አያዋጣንም።

ጌታ ይባርካችሁ
Mar 8, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 8, 2011 ታርሟል
ለምን አይጠቅመግኝም ምክንያቱም የያዝከው መጽሃፍ ቅዱስ ትክክለግኛነት ያጠራጥረግኛል።66 አሃዱ ላይ ዘፍ 5፤17 ቃየንም ሚስቱን አወቃት ይላል
የቃየን ሚስት ከየት እንደ መጣች መጽሃፍ ቅዱስ ገልጠህ ታስረዳኛለህ?
መጠራጠር መብት ነው። ለሰዎች ጥርጣሬ ሁሉ ዓለም መልስ የላትም። በእምነት ውስጥ ደግሞ ማመን በጥርጣሬ ከተደገፈ መጨረሻው ክህደት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ ጥናታዊ ጽሁፍ ወይም የአንድ ወቅት የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ አይደለም።
ብዙውን ታሪክ ትተን ከአቤል ሞት በኋላ ለአዳም የተወለደለት ልጅ «ሴት» የተባለው ነው። አዳምም ሴትን የወለደው በ230 ዓመቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
«አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራ» ዘፍ 4፤3
በ230 ዘመኑ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተዘረዘሩና ስላልተጠቀሱ ሌሎች ልጆችን አልወለደም ወይም አልነበረውም ልንል አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ ዓላማው የዘር ሐረግን ወይም የቤተሰብን ዝርዝር መተረክ ሳይሆን ከቀዳማዊው አዳም እስከ ደኀራዊው አዳም ድረስ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ዓላማ መናገር መሆኑን መረዳት ይገባል። የዓላማውን መስመር ተከትሎ እስከ ክርስቶስ ያለውን ይዞ የሚወርድና በተወሰነ ደረጃም ግራና ቀኝ ያሉትን ሀረጎች በመጥቀስ የሚጓዝ እንጂ እያንዳንዱን ትውልድ የሚናገር መጽሐፍ አይደለም። ማቴ 1፣1 እንደዚሁ ሁሉ ሰሎሞን ንጉሥ ሚስቶቹና ቁባቶቹ 1000 ይደርሱ እንደነበር ተጠቅሷል። የአንድ ሺውም ስም መዘርዘር መጽሐፍ ቅዱስ ዓላማው አይደለምና መናገር አላስፈለገውም። ትውልዳዊ ነጥቡን ቤርሳቤህ ላይ አድርጎ ወደ ቀጣዩ ያልፋል። ስለዚህ አንድ ነገር አለመጠሱ የነገሩን አስፈላጊ አለመሆን እንጂ የነገሩን አለመኖር አያረጋግጥም።
በሌላ ቦታም የላሜህ ሚስት «ሴላ» ከነሀስና ከብረት እየቀጠቀጠ ብረት የሚሰራውን ቱባልቃይን መውለዷን ተጽፎ እናገኛለን። ዘፍ 4፣22 ይሁን እንጂ ነሀሱንና ብረቱን ከየትና እንዴት እንዳገኘው አልተብራራም፤ መጽሐፍ ቅዱስ ቱባልቃይን ነሀስና ብረትን ከየትኛው ቦታ ቆፍሮ እንዳወጣውና እንዳነጠረው ባለመዘርዘሩ ስህተት ነው ልንል አንችልም። ከመቀጥቀጡ በፊት እንዴት እንዳወጣውና ከየት እንዳገኘው መናገር ነበረበት አንልም። ዓላማው የላሜሕን ልጅ ቱባልቃይን ምን ይሰራ እንደነበረ አመልክቶ ወደቀጣይ ትውልዶች ዝርዝር መግባት ስለነበረ የእያንዳንዱን ሰው የሙያ ብቃት መናገር አስፈላጊው አይደለምና አልተናገረም። ከዚህ የተነሳ ስለሌለ ብረትና ነሀስ ያወራል ልንለው አንችልም። ይህ ጥቅስ ከነሀስና ከብረት ቀጥቅጦ መስራት ስለመቻል ሲናገር የመጀመሪያው ነው። አንዳንድ ጥያቄዎቻችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ ያፈነገጠ እና ከ «ሀ» እስከ «ፐ» ድረስ እያንዳንዷን እየተረከ እንዲናገር የምንጠብቀው ካደረግን ከአዳም ጀምሮ እስካሁን ያለውን የእግዚአብሔር አሰራር በመጽሐፍ ማስቀመጥ ውቅያኖስን በጭልፋ ቀድቶ ለመጨረስ የመሞከር ያህል እንዲያውም የበለጠውን ከባድ ነገር ማሰብ ይሆንብናል።
ሐዋርያው ዮሐንስን ያለው ይህንን ነው።
«ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል» ዮሐ 21፤25
ወንጌል ላይ የተጻፈልን ለእኛ በክርስቶስ ለምናምነው በቂ የመዳኛ ቃል ስለሆነ ብቻ ነው እንጂ ክርስቶስ በ33 ዓመቱ ሁሉ ያደረገው ወንጌል ላይ የተጻፈው ብቻ ነው ማለት እንዳልሆነ ያረጋግጥልናል።
ስለዚህ ወንድሜ ቃየን ያገባት ሴት ልጅ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባለመጠቀሷ አዳም ከቃየንና ከአቤል ውጪ በ 230 ዓመቱ ውስጥ ሴት ልጅ አልወለደም ልንል አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የሌለችን ልጅ ለቃየን ሚስት አድርጎ አይሰጥም። ከላይ እያየን እንደመጣነው ሁሉንም ትውልድ በነቂስ መዘርዘር የመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማው ስላይደለ፤ ስማቸውን ካልዘረዘራቸው ልጆቹ አንዷ እንደሆነች እንገምታለን። ከዚያ ውጪ ቃሉን ስህተት አድርገን አንመለከትም።
ወንድሜ ለሰዎች ጥርጣሬ መልስ የሌላት አለም ሳትሆን ውሽት ናት።ምክንያቱም እውነት ማረጋገጫ አትፈልግም ብትፈልግም ማረጋገጫዋ እውነት እራስዋ ናት። የያዝከው መጽሃፍ ቅዱስ እውነት ከሆነ በእርሱ አረጋግጥልኝ አልኩህ እንጂ ስለ እኔ እምነት እን ክህደት አረጋግጥልኝ አላልኩህም።ወደ እምነት እና ክህደት ከመጣህም ደግሞ እራስህን በ 15ኛው ክ/ዘመን መስታዎት ተመልከት።እየሱስ ክርስቶስ በስጋ በተገለጠ ግዜ በመጨረሻው ዘመን ከዳተኞች ይመጣሉ እንጂ ያለው እውነተኛው ሃይማኖት ይመጣል አላለም።ብሎል እንዴ?ወንድሜ ትክክል ነህ መጽሐፍ ቅዱስ ዓላማው የዘር ሐረግን ወይም የቤተሰብን ዝርዝር መተረክ ሳይሆን ከቀዳማዊው አዳም እስከ ደኀራዊው አዳም ድረስ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ዓላማ መናገር ነው።ነገር ግን አንተ ይህንን አባባል ያውቃል ለመባል ያህል ተናገርከው እንጂ ምንም አታውቅም እየጠይኩህ ያለሁት ስለ ዘር ሃረግ ሳይሆን ስለ እውነት እና ክህደት (ውሽት)ነው።ያልኩህ እኮ የዘር ሃረግ በተራ ፍልስፍና ቁጠርልኝ ሳይሆን የቃየን ሚስት ከየት መጣች ነው?ይህንን አይነት ጥያቄ መመለስ አልችልም እያልከኝ ክሆነ ወይ መጽሃፍ ቅዱስህን አታውቀውም ወይ ደግሞ የያዝከው መጽሃፍ ቅዱስ ትክክለግኛነት ክማጠራጠር አልፎ የጎደለው አለ ማለት ነው።ለነገሩ አይገርመኝም ምክንያቱም በስተመጨረሻው እንኮን መጽሃፍ ቅዱስ መቅደስ ያፈርሳሉ ተብሎ ተጽፎል።ወንድሜ መጽሃፍ ቅዱስ የተጻፈው ለሚያምኑ ብቻ ሳይሆን ለማያምኑም ጭምር ነው ለማያምኑት ደግሞ ማረጋገጫ ይፈልጋሉ ስለዚህ አንተ ትክክለኛዉን የእግዚአብሔርን ቃል እናገራለሁ ካልክ የተሞላ መጽሃፍ ቅዱስ ይዘህ መቅረብ አለብህ እንጂ ተራ የ15ኛዉን ክ/ዘመን የቼዝ ፍልስፍና ይዘህ አይደለም።አንድ ጥያቄ ልጨምርልህ ወዳጄ?ቢመርህም እጨምርልሃለሁ።1ሳሙ 2፤25 ሊያብራሩልግኝ ይችላሉ

"ሰውስ ሰውን ቢበድል እግዚአብሔር ይፈርድበታል ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው? እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊገድላቸው ወድዶአልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።"
ወስብሃት ለእግዚአብሄር
ወንድሜ ተረጋጋ፡ አትበሳጭ። ለብዙዎቹ ጉንጭ አልፋ ክርክሮችህ ጊዜን አላባክንም።በአጭሩ፤
የ21ኛ ክ/ዘመን የመልስ ችግረኛ፤የ15ኛውን ክ/ዘመን ፍልስፍናን የምትንቅበት እውቀትህ የት ነው ያለው? ስለ ቃየን እህት መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረቶችን ለመልስ ማያያዣ አቅርቤአለሁ። ለመቀበልም ሆነ ለመካድ መብቱ ያንተ ነው። ወይም ሌላ ተረት አንተ እስክትነግረን ያለኝ ይኼ ነው። በ1ኛ ሳሙኤል 2፤25 ላይ ያቀረብከው ጥያቄ ምን ለማለት እንደፈለግህ የሚገባው አንተን ብቻ ነው። ፈልጋችሁ አግኙ የምትል ከሆነ ለቃላት ቁፋሮ ጊዜ የለኝም።
የድንጋይም መቅደስ ይሁን የሰው (ስጋው) መቅደስ ድሮም ፈርሷል። ዛሬም እየፈረሰ ነው። አንተ ያለህበትን ፍልስፍናን ስለመብለጡ የምትመካበት መቅደስ የት እንዳለ እስክትነግረን እንጠብቃለን። በተረፈ ለማወቅ እንጂ ለመፈተን አትጠይቅ። ከዚያም ባለፈ አትመጻደቅ።ለማወቅ ወይም ከምታውቀው ለማጋራት ሞክር።
ወዳጄ የቀጥተኛዋ እምነት ተከታይ ነኝ ካላወቅከኝ።ብስጭት አላውቅም ክርስቶስን በ30ዲናር የሸጠው ይሁዳም የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ይል ነበር።ጉንጭ አልፋ ክርክር አልካቸው እንጂ ያነሳኹዋቸው ነጥቦች እንኮን መራራ እውነቶች ናቸው በ21ክ/ዘመን መልስ መስጠት ያቃተህ አንተ እንጂ እኔ አይደለሁም የ15ኛውን ክ/ዘመን ፍልስፍና የምትመጻደቅበት ከሆነ ተጨማለቅበት።አማርኛ ካልቻልክ በምሳሌ ላስረዳህ "አበበ በሶ በላ" የሚል ጽሁፍ ቀርቦልህ "አበበ____በላ" ስትባል "ጠላ" እያልከኝ ነው ያለኸው ለምን ጠላ አልክ ብልህ ደግሞ ጠላም ከገብስ ስለሚሰራ እያልከኝ ነው ያለኸው እንጂ ምንም የማይገጣጠም መልስ ነው እየሰጠኸኝ ያለኸው ካቃተህ አላስገድድህም።በ1ኛ ሳሙኤል 2፤25 ላይ ያለው ግልጽ እን ግልጽ ነው የቃላት ቁፋሮ ብታውቅ
ስለቀጥተኛዋም፤ ስለአበበም፤ ስለበሶና ጠላም፤ ስለሁሉም እውቀቶችህ አመሰግንሃለሁ።
0 ድምጾች
ከመቂ
ይህን መልስ ብታውቅ ምን ይፈይድልሃል?
ይልቅስ ህይወት የሚሆንህን መርምር!
Mar 12, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mr, Teyaki betam bado sew timeslegnaleh, irasihin awiqalehu bileh yimitasib dedeb neh.
@ deje igiziabiher yibarkih
ከመተቸት መልስ እንስጥ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...