ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ራሳቸውን ስላጠፉት ሰዎች መ/ቅዱስ ምን ይላል?

ራሳቻውን ስላጠፉት ሰዎች መ/ቅዱስ ምን ይላል? አንድ ዘመዴ በጌታ ጥሩ ህይወት ነበረወ፤ ግን ባልታወቀ ሁኔታ ተሰቅሎ ሞቶአልና መንግስቴ ሰማይ ልገባ ይችላል? እባካችሁ በዝህ ጉዳይ በጣም ተቸግሪያለሁና ርዱኝ፡፡
Mar 28, 2012 መንፈሳዊ ያዕቆብ ደበላ (120 ነጥቦች) የተጠየቀ
ሰላም ያቆብ
በመጀመሪያ ሃዜኔን ለገልጽልህ እፈልጋለሁ እንዲሁም ደግሞ የጌታን እጅ በመልካም ነቱ እየመራህ ስለ ሆነ ጌታን አመሰግናለሁ።
ያቆብ ጌታን አባቴ የት ነው በለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? እስቲ እርሱን እራሱን ጠይቀው እርገጠኛ ነኝ መልሱን አንተ በሚገባህ ነገር በህልምሆነ በራእይ እርሱ በፈቀደው የገልጽልሃል። ሰላሁሉም ጸጋ ይብዛልህ።
እራሱን ያጠፋ(የገደለ) ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳል አይወርስም ከሚል አራት ነጥብ የደፋ መልስ ከመስጠቴ ይልቅ በቅዲሚያ የአእምሮን ጤንነት በተመለከተ ልናውቅ የሚገባን ጉዳይ ይመስለኛል። ምክንያቱም ማንኛውም የሰውነታችን ክፍል እንደሚታመም ሁሉ አእሮአችንም ሊታመም ይችላል። በዚህ ሁኔታ ላለ ሰው ዳኝነቱን ለእግዚአብሔር እንተወው ካለማመን ወይም በመመረር የመጣ ሳይሆን ከህመም የተነሳ የተፈጸመ ድርጊት ሊሆን ስለሚችል።
በተረፈ ግን ለሁላችንም የሚሆን ነገር እውነቱን መነጋገራችን ነው። በቃሉ ተብሎ ከተጻፈ ከተጻፈው ይልቅ የኛ ነገሮችን መሸፋፈን ሰውን አያጽናናም ሊመጣ ካለውም ክፍ አያስመልጠውም። መልሳችን ምናልባት የዚህ ነገር ጥያቄ ያላቸውን ሰዎች ጥያቄ ይመልሳል ቛሚውንም ሰው ይጠብቃል። በዘፀአት 20፡13 ላይ "አትግደል" በመቀጠልም 1ኛ ዮሀንስ መልክት 3፡15 "ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።" ሰው ሰውን ሲገድል ሰውን ገደለ እንላለን። እራሱን ሲገድል ደግሞ እራሱን ገደለ እንላለን። እንዲህ ከሆነ ሰው ለላ ሰውንም ይሁን እራሱ ከገደለ ነፈሰ ገዳይ ነው ማለት ነው። በምናልፍበት መንገድ ሁሉ የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዲበዛልን እያለመንን በምህረቱ ብዛት የተሰጠንን እድሜ ኖረን እግዚአብሔር በእኛ የቃደውን የተወለድንበትን አላማ ኖረን በፈቃዱ ወደመንግስቱ እስኪሰበስበን መጠበቅ ነው። እግዚአብሔር ቸር ነውና።

2 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም ያዕቆብ

ይህ እጅግ ከባድ ጥያቄ ነው፤ እውነቱን ለመናገር አጥጋብ መልስ ከሰው የምታገኝ አይመስለኝም። ራሱን ያጠፋ ሁሉ ሲኦል ይገባል ብለው ቢመልሱልህም አንተን አያጽናናም፤ እንዲሁም ምንም አይሆንም አይዞህ ቢሉህም አንተን አያረጋጋም፤ ምክንያቱም እርግጠኛ መልስ እንዳለሆነ አንተም ስለምታውቀው ማለት ነው።

ስለዚህ እኔ የምመክርህ፤ ዘመድህን የፈጠርከው አንተ ሳትሆን እግዚአብሔር ነው። ከማህጸን ጀምሮ የምታውቀው አንተ ሳትሆን አምላኩ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ጨካኝ አምባገነን ሳይሆን ጻድቅ ፈራጅ ነው። ስለዚህ በእርሱ ጻድቅ ፍርድና ትክክለኛነት ተማምነህ፤ ከአንተ የበለጠ ዘመድህን የሚያውቀው እርሱ እንደሆነ አምነህ፤ ነገርህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል።

እኛ ሁሉን በማወቃችን ላይ ሳይሆን እረፍትና ሰላም ያለን፤ በእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት እንዲሁም ጻድቅ ፈራጅነት በመደገፍና በመታመናችን ነው። ነገሩን ለጌታ ስጥ፤ ይህ ከሰው በላይ ነውና። በዚህ ጥያቄ የሰው መልስ ምንም ቢሆን ምን የልብህ ደርሶ አያረካህም።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 11
33 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።
34 የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው?
35 ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?
36 ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

Romans 11
33 O the depth of the riches and wisdom and knowledge of God! How unsearchable are his judgments and how inscrutable his ways!
34 "For who has known the mind of the Lord? Or who has been his counselor?"
35 "Or who has given a gift to him, to receive a gift in return?"
36 For from him and through him and to him are all things. To him be the glory forever. Amen.
Mar 28, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ስለዘመድህ ታንቆ በመሞቱም ይሁን ብዙ ጊዜ ታንቀው ስለሚሞቱ ሰዎች በጣም አዝናለሁ። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳችን ታንቀው የሞቱ ሰዎች ዋጋቸው ምን እንደሆነ በግልጽ ስለማያስቀምጥ ይህ ያላሳሰበው ሰው ምን ሊያሳስበው ይችላል? አንተም በዚህ የተነሳ ስለዘመድህ ታንቆ መሞት መቸገርህን ገልጸሃል። ይሁን እንጂ ታንቆ ቢሞት ወይም በሌላ አደጋ ቢሞት ወይም ታሞ ቢሞት፣በእርጅና ቢሞት የነፍሱ የመዳን ዋስትና በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር እጅ በመሆኑ እገሌ ይኰነናል ወይም እገሌ ሊጸድቅ ይችላል የሚል ሃሳብ በመያዝ ዋስትና ለማግኘት አትሞክር። የሰው ልጅ ዋጋው በእግዚአብሔር እጅ ነው።
የሰው ድርሻው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስር መኖር ነው።
«እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ» ራእ 22፣12
አንዳንድ ሰዎች ከእግዚአብሔር ሃሳብ ውጪ ኖረው ሳለ አሟሟታቸው ያለስቃይና ህመም በጤናማ ሙሉ ሰውነት ውስጥ ሰላማዊ ሊሆን ይችላል። እንደዘልማድ አባባል «አሟሟቴን አሳምርልኝ» ስላሉ ሳይሆን ወይም ለአሟሟታቸው ሰላማዊነት የሰዎቹ መልካምነት ተመዝኖ ከእግዚአብሔር እንደተሰጠ ዋጋ መቆጠር የለበትም።
ኢዮብ ይህን ይጠይቃል።
«ስለ ምን ኃጢአተኞች በሕይወት ይኖራሉ? ስለ ምንስ ያረጃሉ? በባለጠግነትስ ስለ ምን ይበረታሉ?ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው፣ቤታቸው ከፍርሃት ወጥቶ የታመነ ነው፥ የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም» ኢዮብ 21፣7-9

ሌላው ሰው የእግዚአብሔርን መልካም ነገር አይቶ ሳይቀምሰው ሊሞት፤ ሊሰቃይ፤ ሊታመም ይችላል። የኢዮብም ሕይወት የሚያሰተምረን ይህንን ነው።

«ሌላውም ሰው መልካምን ነገር ከቶ ሳይቀምስ በተመረረች ነፍስ ይሞታል» ኢዮብ 21፣25
ክዚሀ አንጻር አሟሟትን አይተን የነፍስን እጣ ፈንታ መናገር አንችልም።

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ታንቀው ስለሞቱ ሰዎች ማንነት የሚነግረን ነገር አለ።
ስለአኪጦፌልና ከሐዋርያት አንዱ ስለነበረው ይሁዳ። እነዚህ ሁለት ሰዎች የቀደመ ግብራቸው መጥፎ ነበር። ከዚህ ግብራቸው ለመሸሽ መታነቅን አማራጭ አደረጉት። ይሁን እንጂ መታነቃቸው የቀደመ ስራቸውን የሚሸፍን አይሆንም።
2ኛ ሳሙ 17፣23 ማቴ 27፤5
ሰው ከእግዚአብሔር አሳብ ሲወጣ ነፍሱን እንደሚጥላት ይታወቃል።
«ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል» ምሳ 19፣16
በዚህም ዘመን ብዙ ሰዎች ከሚከታተላቸውና ከሚያሳስባቸው ጭንቀትና ውጥረት ለመገላገል መታነቅን እንደአማራጭ ይጠቀሙታል። እንደዚሁ ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታነቁትን ሰዎች ስንመለከት መታነቅ የመልካም ሞት አንድ አካል ሆኖ ስለማይታይ አሳሳቢነቱ አይካድም።
ሰው በአፍንጫው ውስጥ ያለች ነፍሱን ራሱ ያጠፋት ዘንድ እንደሚገባ የተቀመጠልንም ነገር የለም።
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሳያውቀው የሚሆን ሞት የለም። ከሞት በኋላም ሲኦል የሚያወርድም፣ የሚያወጣም እሱ ብቻ ነው።
«እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል» 1ኛ ሳሙ 2፤6
በግሌ ግን በእግዚአብሔር በጎነትና ደግነት ለሚታመኑ ክርስቲያኖች ታንቆ በመሞት ራስን በራስ ማጥፋት ተገቢ ነው ብዬ አላስብም።
Mar 29, 2012 ብርሃን (1,840 ነጥቦች) የተመለሰ
ስለ ሰጠሄኝ መልስ አመስግናለው።ጥሩ ነገር ያሌብህ ይመስለኛል፤ስለ አገልግሎት የ እግ/ርን ፍቃድ እንደት ማወቅ ይቻላል ያልኩትን ግን አልመለስክም።ይህም ለን ተ ማገል ገል ነውና ብትመልስልኝ።ይህን ያልኩት ማገልገል ስለሚፈልግ ነው።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...