ብዙዎቹ የመጨረሻው ዘመን መጽሐፍት ብዙ ጥያቄዎችን ቢመልሱም መጽሐፍ ቅዱስን ተመርኩዘው ሳይሆን የጸሐፊውን ግምትና አስተያየት ተመርኩዘው ነው። ስለዚህ መጽሐፎቹ ስናነባቸው ስለቀለሉ ወይም እኛ ያሰብነውን ስላረጋገጡልን ብቻ ጥሩ ናቸው ማለት አይደለም። በእኛ ግምት እያንዳንዱ ነው ብለው የሚናገሩት ዓረፍተ ነገር፤ በመጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ ሊገኝ የሚችል መሆን አለበት።
ለምሳሌ በራእይ መጽሐፍ ላይ የሚገኙት 24ቱ ሽማግሌዎች 12ቱ የብሉይ 12ቱ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ናቸው ካለ አንድ መጽሐፍ፤ ይህን ያለበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ማቅረብ አለበት እንጂ እንዲያው በግምት 24 ሲካፈል ለሁለት 12 ስለሆነ ብቻ ወይም በሰው ግምት ሁለቱንም የኪዳን ሰዎች ኮምፕሮማይስ አድርጎ
(አመቻምቾ
) ለማስገባት ብቻ ወይም 12 የእስራኤል ነገዶችና 12 ሐዋርያት ስለነበሩ ብቻ መሆን የለበትም። እነዚህ ሁሉ 24ቱን ሽማግሌዎች በግልጽ የሚያስረዱ አይደሉም። ስለዚህ መጽሐፉ ግልጽ የሆነና የተነገረውን ዓ/ነገር የሚደግፍ የማያሻማ ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማቅረብ አለበት።
ከዚህ በተጨማሪ ከዘመኑ ክስተት ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚገቡ ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚነሱ መሆን አለባቸው እንላለን። ማለትም የሆነ ጦርነት በተነሳ ቁጥር ወይም አንድ የሆነ ክስተት በዓለም በተፈጠረ ቁጥር ከዛ ክስተት ተነስተው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢትን ሊተረጉሙ የሚሞክሩ ሁሉ ብዙ ጊዜ ይስታሉ። ይሄ በኢራቅ ጦርነት፣ በአውሮፓ ዩኒየን መመሥረት፣ በ2000 ዓ/ም ዘመን መለወጫ ወዘተ የታየ ስህተት ነው።
በእነዚህ መመዘኛዎች ሁሉ ሲመዘን በጣም መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ የመጨረሻው ዘመን ትምህርት ይገኝበታል ብለን የምናምነው መጽሐፍ
Things to Come: A Study in Biblical Eschatology የሚለው የ
Dr.
J.
Dwight Pentecost መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ እጅግ ጠቃሚና መጽሐፍ ቅዱስን ተመሥርቶ ብዙ ጥያቄዎችን የሚመልስ መጽሐፍ ሆኖ አግኝተነዋል።
Dr.
J.
Dwight Pentecost የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት አስተማሪ እንደመሆናቸው፤ መጽሐፉም
scholarly የተጻፈ ነው። ብዙ የዩኒቨርሲቲ መጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ይህንን መጽሐፍ እንደ መሠረታዊ ማጣቀሻ የሚወስዱት መጽሐፍ ነው። እኛም እጅግ ተምረንበታል። ብዙ የተወሳሰቡ የሚመስሉ የመጨረሻው ዘመን ጥያቄዎችን መጽሐፍ ቅዱስን ተመርኩዞ ግልጽ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉን
እዚህ ማግኘት ይቻላል።