ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጾታየ ወንድ ሲሆን ብልቴ በጣም ትንሽ መሆኑ በወደፊት ትዳር ህይዎቴ ላይ ያለው ተጽኖ ምንድን ነው?

Apr 13, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም

በእርግጥ ነው የብልት ሁኔታ የትዳርን ህይወት የሚነካ መሰረታዊ ነገር ስለሆነ፤ በዚህ ጉዳይ ማሰብህ ትክክል ነው። ሆኖም በቅድሚያ አንድ ልጠይቅህ የምፈልገው "ትንሽ" ስትል ከኖርማል ውጭ የሆነና የጫጨ ማለትህ ነው? ማለትም የአካል ጉድለት ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነው ወይስ ምንም እንኳን ትልቅ ባይሆን ኖርማል የሆነ፤ ነገር ግን አንተ በራስህ አስተያየትና ግምት እጅግ ትንሽ ሆኖ የሚሰማህ ነው?

የአካል ጉድለት ማለትም እጅግ በጣም ትንሽና የጫጨ ከሆነ ሃኪሞችን ብታማክር መልካም ነው እላለሁ። በአሁኑ ዘመን በተለይ በዚህ በምእራቡ አለም ለዚህም የህክምና መፍትሄ ሊኖር ስለሚችል ሃኪሞችን እንድታማክር እመክርሃለሁ።

የአካል ጉድለት ያልሆነ፤ ነገር ግን ኖርማል ትንሽ ሆኖ አንተ በአስተሳሰብህ ብቻ በጣም የጫጨ ሆኖ የሚሰማህ ከሆነ ምናልባት የአስተሳሰብ ችግር ሊሆን ይችላል። ይህንንም ለመለየት ሃኪም ዘንድ ብታሳይ መልካም ነው።

የአካል ጉድለት ካልሆነና የአንተ የአስተሳሰብ ችግር ብቻ ከሆነ ለትዳር ችግር ላያመጣ ይችላል። የአካል ጉድለትና መጫጨት ከሆነ ግን ትዳር ላይ ችግር ማምጣቱ ስለማይቀር በቅድሚያ መፍትሔ ማግኘቱ መልካም ነው። ይህም ሆነ ያ ግን በፍጹም በፍጹም ይህንን ከወደፊት እጮኛህ ደብቀህ ወደ ትዳር እንዳትገባ በጌታ ፍቅር አሳስብሃለሁ። የብልት ትንሽነት ለአንዳንድ ሴቶች ምንም ችግር የለውም፤ ለአንዳንዶች ደግሞ በጣም ትልቅ ችግር ነው። ስለዚህ የወደፊት እጮኛህ ይህንን ጉዳይ አውቃ እንድትገባ እውነቱን መናገር አለብህ። ደባብቀህ ገብተህ መፋታቱ ከዚያም እርሷ የተፋታችበትን ምክንያት ለሰዎች ሁሉ ማውራቱ ወዘተ ለአንተም ይሁን ለእርሷ አይረባምና እውነቱን ከትዳር በፊት እንድትነግራት አደራ እልሃለሁ።

ጌታ በነገር ሁሉ ይርዳህ!
Apr 17, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
ሰላም ጥያቄውን የመለስከው/ሽ ከእጮኛው ጋር ገና ሳይጋቡ እንድሞካከሩ ነው የምትመክርው? ወይም ብልቱን አውጥቶ እንድያሳየት ነው?
ሰላም አስተያየት የሰጠኸው ሰው፦ እኔ ሳይጋቡ እንዲሞካከሩ ወይም ብልቱን እንዲያሳያት አላልኩም። ሆኖም ልክ ለእኛ ብልቱን ሳያሳይ ችግሩን እንደነገረን ሁሉ ለወደፊት ሚስቱም እንዲሁ በዚህ ረገድ ችግር እንዳለ በግልጽ ሊነግራት ይገባል። ከሁሉም በላይ የወደፊት የትዳር ጓደኛውን በአንደኛ ደረጃ የሚመለከት ጉዳይ ስለሆነ ችግር እንዳለ ማሳወቅ ይኖርበታል። ኑሮውን የምትገፋው እርሷ ናትና፤ በዚህ አቅጣጫ ችግር መኖሩን አውቃ ልትገባባት ወይም ካልተስማማት ሳይጋቡ ልትተወው ይገባል። ተጋብቶ በዚህ ጉዳይ መፋታቱ ለእርሷም ይሁን ለእርሱ ከጉዳት በስተቀር ምንም ትርፍ የለውምና። የአሁኑ ዘመን ሴቶች ደግሞ እንደ ጥንቱ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ ትልቅ ችግር ይዘው አፋቸውን ዘግተው ይኖራሉ ብሎ ማሰብ በጣም ሞኝነት ነው። ያለ ጥርጥር ሁሉም ሴቶች አውቀውበት ካልገቡ በስተቀር በዚህ ጉዳይ መፋታታቸው አይቀሬ ነው። ደግሞም እነርሱ ላይ መፍረድም ትክክል አይደለም።
0 ድምጾች
ወንድሜ ምንም ችግር የለዉም ፡ የኔም በጣም ትንሽ ነው፡ ግን ትዳር አድርጌ ልጅ ወልደናል
ለፍቅር እና ስሜት ችግር አልሆነብንም። ጌታ አብዝቶ ይባርክህ
May 5, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ 1 ሪፖርት
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...