ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ወንድሜን በእሳት ያቃጣለውን ብገለውስ??????????????

ወንድሜን በእሳት ያቀጣለውን ብገለው በእ/ር ዘንድ እጣያቅ ይሁን?????? የዛሬ ስምንት ወር በsouth africa እኔና ወንድሜ በምንሳረበት ሱቅ ሁለት የአገሩ ዜጎች የመክና ፔትሮል በመድረግ ወንድሜንና ሱቁን አቃጣሉ። እኔንና ሌሎችን እ/ር በታአምር አተረፌን፤ በእሳት ውስጥ መንገድ ያለ የኛ እ/ር ወንድሜን ፍቱና እጆቹ ታቃጥለው ህይወቱን አተረፌ፤ዛሬ ከስምንት ወር ቡኃለ ከተጣርጣሬዎቹ አንዱ በእጄ ገብቱአል ሰሞኑን ልገለው ወስኝአለው።ግን ልቤ ሁለት ሆኑአል ይህንን ጫከኝ አርመኔ ብገለው መጨረሽዬ ምን ይህን?ህግ እንደትሉ እዝ አገር ህግ ለእኛ የለም ብያስሩም ሁለተኛ ቀን ይፈተል፤መተው አልችልም please እርዱኝ ምን ይሸለል? መጸሐፍ ቅዱስ ለእኔ ምን ድገፍ ይስጣል? ነፍሴ ተጨንቀለች!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
Apr 21, 2012 መንፈሳዊ mehretu (220 ነጥቦች) የተጠየቀ

6 መልሶች

+1 ድምጽ
ወንድሜ በአጭር ቃል "እንዳታደርገው!"! በፍጹም በፍጹም በስሜት ተነሳስተህ ብቻ እስክትሞት ድረስ የሚጸጽትህን ነገር አታድርግ! ጌታ ኢየሱስ ክፉውን አትቃወሙ ያለው እኮ የክፉ አንዱ ባህርይ እኛንም ወደ ክፉነት መለወጡና ክፋትን ማራባቱ ነው። ሰውዬውን የያዘው የሰይጣን ክፋት አንተንም እንዳይዝህና ህይወትህን እንዳይወርስህ አትፍቀድለት።

"ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።" ኦሪት ዘፍጥረት 4፡7

ስሜት ያልፋል እንደየጊዜው ይለዋወጣል፤ አሁን የሚሰማህ የብቀላ ስሜት ከጊዜ በኋላ አይኖርም። እንዲያውም ልትገድለው ያሰብከው ሰው በምን ያህል የሰይጣን እስራትና ጨለማ ውስጥ እንዳለ አይተህ ታዝንለታለህ። ስሜት እንደየጊዜው ተለዋዋጭ ነውና አሁን በሚሰማህ ስሜት ብቻ ህይወትህን አታበላሽ!
Quote:
የሉቃስ ወንጌል 23
32 ሌሎችንም ሁለት ክፉ አድራጊዎች ደግሞ ከእርሱ ጋር ይገድሉ ዘንድ ወሰዱ።
33 ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።
34 ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።
Quote:
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2
20 ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
21 የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና
22 እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
23 ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 5
38 ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
39 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
40 እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤
41 ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ።
42 ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል።
43 ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
44-45 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
46 የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
47 ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
48 እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።

ስለዚህ በጌታ ፍቅር እንደ ወንድም የምመክርህ ነገር ይህ ሰው ራሱ የክፉው እስረኛ ነውና ይልቁንም ከቻልክ መልካም አድርግለት፤ ፍቅርንና በጎን ነገር አሳየው፤ የሚያስፈልገውን ስጠው፤ በምትችለውም እርዳው። እንዲህ በማድረግህ ራስህንም እርሱንም ታድናለህና። እርሱን የያዘው ክፉ አንተንም ከሚይዝህስ ይልቅ በአንተ ያለው መልካምነት እርሱን እንዲወርሰው እርዳው። ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። ደግሞም አስታውስ፤ በቀልና ፍርድ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእኛ አይደለም!
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎችም 12
17 ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
18 ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
19 ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና
20 ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
21 ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

እግዚአብሔርም ይረዳሃል! ጸጋው ከአንተ ጋር ይሁን!
Apr 21, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Apr 21, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
ወንደማችን የጌታ እጂ ባንተ ላይ ናት ሌላ ሰው በሆን እስካሁን ያደርገው ነበር አንተ ግን አላደርግሀው የጌታ ጥበቃ በዝቶልህ ነው። ጠላትህን ወደድ ነው የሚለው ቃሉ አሁን መውደድ አትቸል የሆናል ግን ሰው አትግደል አደራ ህን እደትገደል ይልቁንም የደበሎስን መንፋስ ተቃወም ( በከርስቶስ የሱስ ስም የገዳይ መንፍስ ከወንድማችሀን ላይ አሁን ራቅ) አንተም ከኔ ራቅ በልህ ገስጸው ። በቀል የጌታ ነው እዲያውም ወንደምህ በህይወት ሰላተርፈልህ ጌታን አመስገነህ ይህን ሰው ለጌታ ስጠው በትችል ይቀር በለው ባትችል ግን ይሚያስችለውን ጌታ እብክህ ጸጋህን አብዛለኝ የቅር እንድል በልው። አይዞህ ይህም ያልፋል።
ጌታ በ እጥፍ ይባርካችሃል።
Apr 22, 2012 zk77 (680 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ወንድም ምሕረቱ
የጌታ ጸጋ ይብዛልህ

wongelnet ውስጥ ግባና "የእግዚአብሔር ጸጋ" በሚል ርእስ ፓስተር እንዳልካቸው ሳሕሌ በሰበኩት ስብከት ውስጥ ሰለ ይቅርታ ግሩም የሆነና አንተ ካለህበት ሁኔታ ጋር ተመሳሳይበት ያለው ምስክርነት ታገኛለህ።ብታዳምጠው ይጠቅምሃል ብየ አስባለሁ።

የጌታ ሰላም ካንተ ጋር ይሁን
Apr 23, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ሰላም ምህረቱ
የ እ/ዚ ቃል የሚለውን ላስታወስህ
"አትግደል።" ዘፀአት 20፡13
እንዲሁም
"ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።"ማቲ5፡21
ጌታ የሱስም ይህን አስተምሮአል።
ከሃጥያት ሽሽ
"ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።" ዘፍጥ 4፡7
ሃጥያት አታድርግ። አንተ ግን እንደ ስምህ ምህረትን አድርግ።
ጌታ የባርክህ።
Apr 25, 2012 zk77 (680 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
በእውነት ትገርማለህ!! ሃጢአትን ለማድረግ ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ ምን ድጋፍ አለው ትላለህ እንዴ?ነፍስህን እያስጨነቃት ያለው የሰይጣን ምክር ነውና ተጠንቀቅ።ወንድምህን ቢጎዳውም ሌላ ወንድም ማግጜት ትችላለህ እርሱም ልትገድለው ያሰብከውን ሰው ጥሩ ወንድም አድርገው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ጌታ ይርዳህ
Apr 25, 2012 ችሊ (220 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ለሁሉም እንደየሲራዉ እከፊል ዘንድ ዋጋዉ ከእኔ ጋሪ አለ ይላልና ስለዚሂ ይቅር በለዉ እግዝኣብሔር ይቅር ይልሃልና
HEY BRA,IF YOU FOR GIVE HIM YOU WILL REISEVE SOMETHING FROM GOD THANKS.JOSHUA
May 23, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...