ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መንፈስ ቅዱስ አለመሞላት እድል ፈንታ ነው?

በ1996 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በቅርብ ዘመዴ በኩል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመስክሮልኝ ወደ ጉባኤ መጥቼ አመንኩ ተከታታይ ትምህርት ተሰጥቶኝ ተጠመቅሁ የሚያስተምረኝ ወንድም ሲለየኝ የመንፈስ ቅዱስ ጥማት እንዲኖረኝ አሣስቦኝ በቃሉም በፀሎትም እንድተጋ መክሮኝ አምነሽ ተጠምቀሽ ብቻ መቅረት የለብሽም መዳንሽን ሙሉ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ስትሞዩ ነው መንፈስ ቅዱስ መሞላት የግድ ያስፈልጋል ብሎ ጥማት ይኑርሽ በሚል አስጠንቅቆኝ ተለየኝ፡፡ እኔም ከዚያ ቀን ጀምሮ አጥብቄ መንፈስ ቅዱስን እሻ ጀመርኩ ስለሱ ያላሰብኩበት ጊዜ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ለየ አገልጋዩ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንዳልተሞላሁ እያሳሰብኩ እጃቸውን ጭነው እንዲፀልዩልኝ ባደርግም ምንም የለም መንፈስ ቅዱስ ባለመሞላቴ ውስጤ ባዶነት ይሰማኛል ተፈትቼ ባመልክም ስላለመሞላቴ ሳስብ ኩምሽሽ እላለሁ፡፡ እሸማቀቃለሁ በማያቋርጥ ልቅሶ ውስጥ ራሴን አገኘዋለሁ፡፡ ውስጤ መልስ ባጣሁላቸው ጥያቄዎች ይሞላል፡፡ ሐጢያቴን እቆጥራለሁ ዘርዝሬ ስለማልጨርሰው እግዚአብሔር እንደጠላኝ፣ እንደተጠየፈኝ፣ ለእኔ የሚሆን ምህረት እንደሌለው ራሴን አሣምነዋለሁ፡፡ ይህ ደግሞ የክርስትና ጉዞዬን ወናምከንቱም ያደርግብኛል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለመሞላት የሚፀለይላችሁ ሲባል ተሽቀዳድሜ እንዳልወጣሁ አሁን ይህንን ለማድረግ አቅም የለኝም፡፡ በዚህ አይነት ህይወቴ ምስቅልቅል ያለና መሐል ቤት እየሆነ መጣ በህብረት ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች በመንፈስ ቅዱስ ሲሞሉ፣በልሣን ሲፀልዩ ሕፃናት ሣይቀሩ በመንፈስ ቅዱስ ሲዳሰሱ አይኔ ያያል፡፡ እኔ ግን የዚህ እድል ፈንታ አካል ባለመሆኔ ሁሌ እቆዝማለሁ፡፡ ግን ለምን? ለዚህ መልስ አላገኘሁም ሁሌም ያስጨንቀኛል እዚህ ምድር ላይ መኖሬ ከንቱ እንደሆነ ይሰማኛል ራሴን ለማጥፋት አንድ ሁለቴ ሞከርኩና ከዚህ ውጥረት ብገላገል ሌላ እንደሚጠብቀኝ ስረዳ ተውኩት፡፡ ስለመንፈስ ቅዱስ መሞላት የተሰበኩ ስብከቶች፣ የተለያዩ የመፅሔትና የመፅሐፍ አይነቶችን ሆን ብዬ ሰብስቤ አነበብኩም ሰማሁም መንፈስ ቅዱስ መሞላት እንዳለብን አበክረው ይመክራሉ ለመሞላትም ውስጣችን ጥማት መኖር እንዳለበት ያስረዳሉ፡፡ ከእነሱ ያገኘሁት እውቀት ደግሞ የግድ በአገልግሎት የምበረታው፣የምመሰክረው፣ሸክምም የሚኖረኝ፣ ህይወቴን ሙሉ ማድረግ የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተረዳሁ፡፡ መረዳቴ ብቻውን ግን ምን ያደርጋል… ይኸው እስከዛሬ እብሰለሰላለሁ ያገኘሁትን ፀልዩልኝ እላለሁ፡፡ እናንተስ ምን ትሉኛላችሁ? እንደ ሐዋርያው አንቺስ ከዚህ ነገር እድል ፈንታ የለሽም?
Apr 22, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ክርስቶስን የምታምኝ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በውስጥስ እንዳለ ማመን አለብስ።ይህ ከሆነ ደግሞ እንደዚህ ያለው ለቅሶ ምን ያስፈልጋል?ወይስ የመንፈስ ቅዱስ አሰራር ግድ ሰወችን በመጣልና በማንደፋደፍ ብቻ መስሎ ከታየስ ተሳስተሳል፡ እንደኔ አመለካከት ደግሞ ልሳን መናገር የመንፈስ ቅዱስ መሞላት ምልክት ቢሆንም ልሳን የተናገረ ሁሉ በመንፈስ ኪዱስ ተሞላ ማለት አይደለም ስለዚህ እንዳልስው ካለስ ትልቅ ጥማት አንጻር የክፉ ልሳን ተናጋሪ እንዳትሆኝ ልትጠነቀቂ ይገባል።እህቴ መንፈስ ቅዱስ ውስጥስ አለ ስሚው።
Apr 22, 2012 ችሊ (220 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ውድ እህታችን በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና አለመሞላት የተመለከተ በጥቂቱ በመግለጽ ለጥያቄሽ እመልስ ዘንድ እሞክራለሁ።
1/ መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ነው። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ደግሞ የሌለበት ዘመንና ጊዜ የለም። ያ ማለት መንፈስ ቅዱስ ምንጊዜም ከእኛ ጋር አለ ማለት ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን ከሌላ የሚመጣ ወይም የሚሄድ አካል አድርገን መመልከት የለብንም። ስለመሞላትና አለመሞላት ስንናገር እንደወጪና ገቢ አካል አድርገን የማሰብ አስተውሎት ከያዝን መንፈስ ቅዱስን አላወቅንም ማለት ነው።
ስለኢየሱስ ተመስክሮልሽና አምነሽ ለመጠመቅ የበቃሽው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጂ በማንም አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይለናል።
«ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ» 1ኛ ቆሮ 12፣3
ስለዚህ ኢየሱስ ጌታ ነው ብለሽ ያመንሽው በአንቺ ውስጥ በሚመሰክርልሽ መንፈስ ቅዱስ ኃይል ሆኖ ሳለ ሌላ መንፈስ ቅዱስ የምትጠብቂው ከየት ነው?
ባመንሽ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ታትመሻል።
«እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ» ኤፌ 1፣13

እናም የታተምሽበት የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በውስጥሽ ሳለ ሌላ መንፈስ ቅዱስ ለመጠበቅ መሞከር ትልቅ ስህተት ነው።
2/ መንፈስ ቅዱስ በውስጥሽ መኖሩን እንደ እግዚአብሔር ቃል ካየን ስለመንፈስ ቅዱስ አሰራር ደግሞ ጥቂት መመልከቱ ሳይጠቅም አይቀርም።
መንፈስ ቅዱስ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ያስተምረናል። መንፈስ ቅዱስ ቃሉን ይተረጉምልናል። መንፈስ ቅዱስ ያጽናናናል። ይመክረናል፣ ይገስጸናል። ሉቃ 12፣12 ሉቃ 10፣21 የሐዋ 5፣32 ሮሜ 8፣26 2ኛ ጢሞ 1፣14
መንፈስ ቅዱስ በአዲሲቱ ኪዳን ውስጥ ስለክርስቶስ የሆነውን ሁሉ በልዩ ልዩ ስጦታና ጸጋውን በማደል ኃይሉን ይገልጻል።
ውድ እህታችን ያልጨበጠችው ነጥብ መንፈስ ቅዱስ በውስጧ መኖሩን አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ስጦታዎችን አለማግኘትም የመንፈስ ቅዱስ አለመገለጽ አድርጋ እንድታስብ መገደዷ ነው።
በልሳን መናገር ወይም ትንቢት ወይም ፈውስ ወይም ስብከት ወይም ሌላ የቤተክርስቲያን የጸጋ ስጦታዎች ሁሉ፣ ለሁሉ የሚሰጡ አይደሉም። ሰዎች ለሌሎች መንፈስ ቅዱስ የሰጠውን ስጦታ ሁሉ እንደሚያገኙ ወይም ሊሰጣቸው እንደሚገባ ካሰቡ መንፈስ ቅዱስን አላወቁም ማለት ነው። እነዚህን ስጦታዎች ካላገኙ ደግሞ እንዳልዳኑ ወይም ድነታቸው ሙሉ እንዳልሆነ ማሰብ ሌላው አደገኛ ነገር ነው።
ይህ ሲባል ግን ሰዎች ለመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ራሳቸውን ማዘጋጀት የለባቸውም ማለት አይደለም። ዋናው ነገር እኛ ማደሪያ የሆንበትን ስጋችንን ከሚያጎድፍ ኃጢአት መጠበቅ ይገባናል።
« 1ኛ ቆሮ 6፥19-20 ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ»

እግዚአብሔርን በሚያከብረው ሥጋችን መንፈስ ቅዱስ ለሚፈልገው አገልግሎት በሚፈልገው ስጦታ ሊገለጽብን ይችላል። ስጦታው ልዩ ልዩ ነው። «የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው» 1ኛ ቆሮ 12፣4 እንግዶችን መቀበል ራሱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ድሆችንም መርዳት ቢሆን «ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ» ገላ 2፣10
ሮሜ 12፣4 -21

በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥
እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤
አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤
የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤

እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች ናቸው። ክርስቲያን ራሱንና ቤተክርስቲያንን የሚያንጽበት ስጦታዎች ናቸው። መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ከሌለ አንዱንም ሊያደርግ አይችልም።
ማጠቃለያ፤
ብዙ ጊዜ ሰዎች አምነው እንደተጠመቁ በልሳን መናገር ወይም ልሳን ካልተገለጠላቸው መንፈስ ቅዱስ እንዳልሞላባቸው ይታሰባል።
ጳውሎስ ግን ይህን ይቃወማል። እንዲህ ሲል በመጠየቅ!
«ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን?» 1ኛ ቆሮ 12፣30 ስለዚህ በልሳን መናገር ለሁሉም የሚሰጥ እንደሆነ ልናስብ አይገባም።
እኔም በግሌ ሁሉ አማኝ በልሳን መናገር እንዳለበት የሚያስቡትን ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ መረዳት እንዳልሆነ አድርጌ አስባለሁ።
ስለዚህ እህቴ ሆይ መንፈስ ቅዱስ በውስጥሽ መኖሩን እመኚ። የተሰጠሽ ግን ያልተረዳሽውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መርምሪ። መንፈስ ቅዱስ አማኞቹን ሁሉ በተለያዩ ስጦታዎች እንደሚጎበኝ አውቃለሁ። አማኝ አድርጎ ያለምንም ስጦታ በፍጹም አልተወሽም። ሰዎች የሚያስቡትና የሚገምቱት የግድ የስጦታ ፎርሙላ ያለ ሲመስላቸው ያንን ሲጠብቁ የተሰጣቸውን ሳይረዱት ይቀራሉ። መንፈስ ቅዱስን በበለጠ እንዳይሰራ ባለማወቃችን መንገዱን እንዘጋለን። አማኝ ከሆንሽበት ሰዓት ጀምሮ መንፈ ቅዱስ ማደሪያው መሆንሽን እወቂ። ይህንና ሌሎች መገለጦችን ለመረዳት በጾምና በጸሎት ጠይቂ።
የተደረገልሽን ነገር ደግሞ አንድ ቀን እንደዚሁ መስክሪልን። ለዚሁም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ኃይሉንና ጸጋውን ያብዛልሽ።
Apr 22, 2012 ብርሃን (1,840 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...