ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የትዳር ጉአደኛዬ ሰው ትፈራልች.

ወዳጆቼ በጣም እወዳችሁአለሁ አላችሁልኝ? ኢኔ እግዚአብሄር ይመስገን ኢንጂ ደህና ነኝ.ጥያቄዬ ይትዳር ጉአደኛዬ በጣም ሰው ትፈራለች. መጽሃፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።ምሳሌ 29:25 በቃ even ሰው ካለ መንገድ ላይ በደንብ ሰላም አትለኝም. የአከባቢው ባህል ነው እንዳልል አይደለም ምን ብዬ ብመክራት ነው የምትሰማኝ?
Apr 23, 2012 መንፈሳዊ ታከለ ታደሰ (220 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
ሰላም ወንድሜ ታከለ

ለፍርሃቷ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩዋት ስለሚችል ትንሽ ብትታገሳት መልካም ነው እላለሁ። ምናልባት ራሷም ገና እርግጠኛ ያልሆነችበት ነገር ሊሆን ይችላል። ራሷ ገና እርግጠኛ ያልሆነችበትን ነገር ምናልባት ሰው ቢሰማው ምን ይላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ለምሳሌ የእድሜዋ ማነስ ውስጧ ገና ለትዳር ዝግጁ ያልሆነ ይሆንና ራሷን አሳምና ሳትጨርስ ሰው ቢሰማ ምን ይላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ወይም አንተ እና እርሷ ለምሳሌ በእድሜ ወይም በሌላ ነገር በጣም ብዙ መበላለጥ ካላችሁ፤ ይህም ሰው ቢሰማ ምን ይላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ወይም ባላችሁ ግንኙነት ላይ ገና ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይኖራትና ገና ልቧ ያልሞላና እርግጠኛ አንተ የትዳር ጓደኛዋ ለመሆንህ ገና ልቧ ያላረፈ ሊሆን ይችላል።

ይህም ይሁን ያ አንተ ጊዜ ልትሰጣትና ልቧ እስኪሞላና እርግጠኛ እስክትሆን ልትታገሳት ይገባል። ሴቶች በመሰረቱ ለትዳር ልባቸው ከሞላና ካመኑበት ማንም አይመልሳቸውም፤ ማንንም አይፈሩም ቤተሰቦቻቸውን ጭምር። ልባቸው ካልሞላና እርግጠኛ ካልሆኑ ብቻ ነው ብዙ ጊዜ እንዲህ ነገሮችን መደበቅ የሚፈልጉት። ለማናቸውም ጊዜ ስጣት፤ በግድ በሰው ፊት አብራችሁ እንድትታዩ ምናምን አትገፋፋት። ማድረግ የማትፈልገውን እንድታደርግም አታስገድዳት።
Apr 23, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
ጌታ ይባርክህ ወንድሜ. በጣም አመሰግናለሁ ተባረከህ ቅር..
0 ድምጾች
ሰላም ታከለ
ባለቤትህን እቤትም እውጭም በስምዋ ሳይሆን እሲ እመቤቴ በልህ ጥራት እና ምን እደሚሆን
እይ።
ታዲያ ስትጠራት ከልብህ የጌታ ስጦታ እደሆነች ሁል ግዜ ልትሸከማት ልትታገሳት እለት እለት በጠራሃት ቁጥር ሁሉ ፍቅርህን እያደስክ እንደ አይናፋር ሳይሆን እንደ ጌታዋ አክብራህ ቀና በላ ማይት እንኻን እንደማትደፍር እያሰብህ አድርገው።
ተባርክ።
የሆነውን ና እና ንገረን።
ትገረማልህ።
Apr 30, 2012 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...