ሰላም ወንድሜ ታከለ
ለፍርሃቷ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩዋት ስለሚችል ትንሽ ብትታገሳት መልካም ነው እላለሁ። ምናልባት ራሷም ገና እርግጠኛ ያልሆነችበት ነገር ሊሆን ይችላል። ራሷ ገና እርግጠኛ ያልሆነችበትን ነገር ምናልባት ሰው ቢሰማው ምን ይላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ለምሳሌ የእድሜዋ ማነስ ውስጧ ገና ለትዳር ዝግጁ ያልሆነ ይሆንና ራሷን አሳምና ሳትጨርስ ሰው ቢሰማ ምን ይላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ወይም አንተ እና እርሷ ለምሳሌ በእድሜ ወይም በሌላ ነገር በጣም ብዙ መበላለጥ ካላችሁ፤ ይህም ሰው ቢሰማ ምን ይላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ወይም ባላችሁ ግንኙነት ላይ ገና ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይኖራትና ገና ልቧ ያልሞላና እርግጠኛ አንተ የትዳር ጓደኛዋ ለመሆንህ ገና ልቧ ያላረፈ ሊሆን ይችላል።
ይህም ይሁን ያ አንተ ጊዜ ልትሰጣትና ልቧ እስኪሞላና እርግጠኛ እስክትሆን ልትታገሳት ይገባል። ሴቶች በመሰረቱ ለትዳር ልባቸው ከሞላና ካመኑበት ማንም አይመልሳቸውም፤ ማንንም አይፈሩም ቤተሰቦቻቸውን ጭምር። ልባቸው ካልሞላና እርግጠኛ ካልሆኑ ብቻ ነው ብዙ ጊዜ እንዲህ ነገሮችን መደበቅ የሚፈልጉት። ለማናቸውም ጊዜ ስጣት፤ በግድ በሰው ፊት አብራችሁ እንድትታዩ ምናምን አትገፋፋት። ማድረግ የማትፈልገውን እንድታደርግም አታስገድዳት።