ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ይህ ህልም ጥያቄ ፈጥሮብኛል

ወገኖቼ እኔ እስከአሁን ጥያቄዬን ይዤ ነው ያለሁት ለጉአደኛዬ ብቻ ነው የነገርኩት። ጥያቄው እንደሚቀጥለዉ ነው። ባለፍዉ ሁለት ወራት ውስጥ አንድ የሚያስደንቅ ሕልም አየሁኝ፣ እነሆ ሁለት ክብ የሚመስሉ ነጫጭ ነገሮች ተያይዘዉ ወደላይ ሲበሩ አየሁኝ። ከትንሽ ቆይታ በሁአላ ወደፊት ሂደው ተያያዙና አንድ ትልቅ ቀይ መልክ ያለዉ ልብ ሆኑ። ታዲያ ይህ ትልቅ ልብ የሚመሰል ነገር ደግሞ ወደ እኔ በመጠጋት በጣም ንፁህ ፣ሰፊና ጥልቀት ያለው ባህር ውስጥ ስዋኝ አየሁኝ። ወገኖቼ ይህን ሕልም ባለምኩበት ሰሞን ነው የትዳር ጉአደኛዬ ሶስት ዓመት አይሆነም ስትል ቆይታ አሁን ይሁን ያለችኝ። ይህ ሕልም ደግሞ በጣም ጥያቄ እየሆነብኝ ነው ምን ይሁን። እኔ እስከአሁን ለወንድ ጉአደኛዬ ብቻ ነው የነገርኩት ።እናንተ ደግሞ ምን እንደምትሉኝ አላውቅም።
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
May 2, 2012 መንፈሳዊ ታከለ ታደሰ (220 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ህልምህ ምንም ይሁን ምንም እሱን ለመተርጎም በመፈለግ ጊዜ ከመውሰድ ወይም ያንን ትርጉም መሰረት አድርገህ ወደትዳር ለማምራት ከመሞከር ይልቅ ሶስት ዓመት የፈለካትና የጠበካት ጓደኛ እሺ ካለችህ ጥያቄዋን ልትቀበል ይገባል እላለሁ። ምናልባት ከእሷ ጋር ልትነጋገሩ የምትችሉት ነገር ቢኖር ሶስት ዓመት ጥያቄህን ያልተቀበለችበትና አሁን ፈቃደኛ የሆነችበትን ምክንያት ለመረዳዳት ብትሞክሩ ጥሩ ነው። ከዚያ ውጪ አንተ እሷን የመረጥክበት ሚዛን ውጫዊ እይታን የተመረኰዘ ካልሆነና መንፈሳዊ ማንነቷን፣ ብስለቷንና እውቀቷን ለአንተ የትዳር ምርጫህ በመሆኑ የምታምን ከሆነ ፈቃደኝነትህን መንፈግ የለብህም። የአንተን ማንነት የማጥናቱ ጉዳይ በእሷም በኩል ኖሮ ሊሆን ይችል ይሆናል። ይህንንም ከግምት አስገባ። የተፈላለጋችሁበት ጊዜ ማጠርና መርዘም ሳይሆን የተፈላለጋችሁበት መንገድ አንድ ስለመሆኑ መጀመሪያ ለየራሳችሁ አጥኑ፤ ቀጥሎም በጋራ ተነጋገሩ።
ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል ምሳሌ 18፣22
ስለሚል የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጸሎት መጠየቅ ወሳኝነት አለው። ባንተ ያለው መንፈስ ቅዱስ ስለቀሪ የትዳር ሕይወት በውስጥህ ይመስከራልና ይህንን መከተልም ተገቢ ነው። ከዚህ ውጪ ደግሞ ሰውን ማወቅ ከባድ ቢሆንና ለመረዳት የከበደህ ነገር ካለ የትዳር ጠባያትን ከልምድ፤ ከህይወት ተሞክሮና ከመንፈሳዊ እውቀት የተነሳ አንተ ያለህን ወይም ሊኖርህ የሚችለውን ጉድለት እንዲሞሉልህ ምክርና ጸሎት ከቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ለማግኘት ሞክር። በተረፈ መልካም ትዳር እመኝልሃለሁ።
May 2, 2012 ብርሃን (1,840 ነጥቦች) የተመለሰ
አይ ስው ራሱን ደርሶ ባይታዊ ያደርጋል፣ ዋናው ቁም ነገር ፍጽኣሜውን እየው እስኪ እሽ ኣለች ማለት እውነተኛ ሚስትህ ትሆናለች ማለት አደለም
0 ድምጾች
እንግዲህ ሰው እንደህልሙ ነው ስለዚህ ብዙውን ጊዜ እህልም እውነት አይሆንም ይህ ማለቴ ደግሞ የአንተ እህልም ውሸታም ነው ማለቴ ኣይደለም ስለዚህ መወሰን ያለብህ እራስህ ነህ እኔ ተዳር ብልህ ምን አልባት ገንዘብና አቅም የለህ ይሆናል ስለዚህ አቅምህን ወስነህ እቅድህን ምረጥ እሽ
May 4, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...