ወገኖቼ እኔ እስከአሁን ጥያቄዬን ይዤ ነው ያለሁት ለጉአደኛዬ ብቻ ነው የነገርኩት። ጥያቄው እንደሚቀጥለዉ ነው። ባለፍዉ ሁለት ወራት ውስጥ አንድ የሚያስደንቅ ሕልም አየሁኝ፣ እነሆ ሁለት ክብ የሚመስሉ ነጫጭ ነገሮች ተያይዘዉ ወደላይ ሲበሩ አየሁኝ። ከትንሽ ቆይታ በሁአላ ወደፊት ሂደው ተያያዙና አንድ ትልቅ ቀይ መልክ ያለዉ ልብ ሆኑ። ታዲያ ይህ ትልቅ ልብ የሚመሰል ነገር ደግሞ ወደ እኔ በመጠጋት በጣም ንፁህ ፣ሰፊና ጥልቀት ያለው ባህር ውስጥ ስዋኝ አየሁኝ። ወገኖቼ ይህን ሕልም ባለምኩበት ሰሞን ነው የትዳር ጉአደኛዬ ሶስት ዓመት አይሆነም ስትል ቆይታ አሁን ይሁን ያለችኝ። ይህ ሕልም ደግሞ በጣም ጥያቄ እየሆነብኝ ነው ምን ይሁን። እኔ እስከአሁን ለወንድ ጉአደኛዬ ብቻ ነው የነገርኩት ።እናንተ ደግሞ ምን እንደምትሉኝ አላውቅም።
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!