ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 21 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በአዲስ ኪዳን ሰው በመንፈስ ቅዱስ እንዲጠመቅ እንጂ በውሃ መጠመቅ አያስፈልገወም?

በአዲስ ኪዳን ሰው በመንፈስ ቅዱስ እንዲጠመቅ እንጂ በውሃ መጠመቅ አያስፈልገወም የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አጋጥመውኛል። እናም በውሃ መጠመቅ የመጥምቁ ዮሃንስ ነው እንጂ የኢየሱስና የአዲስ ኪዳን መንገድ አይደለም። የአዲስ ኪዳን መንገድ በመንፈስ የመጠመቅ ብቻ ነው ይላሉ። ይህ ምን ያህል እውነት ነው? በእርግጥ በአዲስ ኪዳን በውሃ መጠመቅ አያስፈልገንም?
May 25, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
የውሃ ጥምቀት በኣዲስ ኪዳንም ኣማኞች ሲያደርጉት የነበረ ጉዳይ ነው። ይሄንን ለማረጋገጥ የሃዋርያት ስራን መጽሃፍ ማንበብ ብቻ ይበቃል። በሃዋርያት ስራ ላይ ሁለቱንም ኣይነት ጥምቀት ነው የምንመለከተው። ማለትም የመንፈስንም እንዲሁም የውሃን ጥምቀት። እንዲያውም አንዳንዶች በመጀመሪያ በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቁ በኋላ ነው በውሃ የተጠመቁት። ለምሳሌ የቆርነሌዎስ ቤተሰቦች። በውሃ መጠመቅ ባያስፈለግ ኖሮ ለምን በመንፈስ ከተጠመቁ በኋላ ጴጥሮስ በውሃ እንዲጠመቁ አዘዛቸው?
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 10
44 ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ
45 ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤
46 በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና።
47 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ።
48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።

ምንም እንኳን በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁ ቢሆንም፤ ጴጥሮስ ግን በተጨማሪ በውሃ ደግሞ እንዲጠመቁ አዘዛቸው። እንዲያውም መንፈስን የተቀበሉ የውሃን ጥምቀት ማን ነው የሚከለክላቸው ብሎ ነው ጴጥሮስ የተናገረው።

በሌላ ክፍል ደግሞ መጀመሪያ በውሃ ከዚያ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ እናነብባለን። ለምሳሌ የሰማርያ ሰዎች።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 8
12 ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ
...
14 በኢየሩሳሌምም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው።
15 እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው
16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና
17 በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ

ፊሊጶስ ለሰማሪያ ሰዎች ክርስቶስን በሰበከላቸው ጊዜና እነርሱም ባመኑ ጊዜ ወዲያው ነው በውሃ እንደተጠመቁ ነው በዚህ ክፍል የምናነብበው። ሆኖም ግን ገና በመንፈስ አልተጠመቁም ነበር። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና። እነ ጴጥሮስ ግን እጃቸውን ሲጭኑላቸው መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ይላል ቃሉ።

ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ከመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ በኋላም ይሁን በፊት፤ ካመኑ በኋላ ሰዎች በውሃ ይጥመቁ ነበር።

በሌላ ክፍል ደግሞ እዛው ሃዋርያት ስራ ላይ፤ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሲመጣ ያገኛቸውን የመጥምቁ ዮሃንስ ደቀመዛሙርትን እንዲሁ በውሃና በመንፈስ ቅዱስ እንዲጠመቁ ነው ያደረገው። እንዲያውም በዚህ ክፍል የዮሃንስ ጥምቀትና በክርስቶስ አምኖ የሚጠመቁት ጥምቀት የተለያየ እንደሆነ እናያለን።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 19
1 አጵሎስም በቆሮንቶስ ሳለ ጳውሎስ በላይኛው አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፥
2 አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ። ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን? አላቸው። እርሱም፦ አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት።
3 እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ? አላቸው። እርሱም፦ በዮሐንስ ጥምቀት አሉት።
4 ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው።
5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
6 ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው በልሳኖችም ተናገሩ፥ ትንቢትም ተናገሩ።
7 ሰዎቹም ሁሉ አሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።

በዚህ ክፍል አንደኛ በቅድሚያ በኢየሱስ ስም በውሃ እንዲጠመቁ ነው ጳውሎስ ያደረገው። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ በመንፈስ ይጠመቁ ዘንድ እጁን ጫነባቸው፤ መንፈስ ቅዱስም ወረደባቸው በልሳኖችም ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ። እዚህም ላይ እንግዲህ በግልጽ እንደምናየው በአዲስ ኪዳን የሁለቱም ጥምቀቶችን አስፈላጊነት እንጂ በመንፈስ የተጠመቀ በውሃ አያስፈልገው የሚል ነገር አናይም። ይህ ብቻ አይደለም ጳውሎስ በዚህ ክፍል እንዳለው የዮሃንስ ጥምቀት የንስሐ ብቻ ጥምቀት ነው። በሮሜ 6 ከቁጥር 1 ጀምሮ እንደተጻፈው ግን፤ በክርስቶስ አምነን የምንጠመቀው ጥምቀት ግን፤ ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤው ጋ መተባበራችንን የሚያሳይ ነው። ስለዚህ ሁለቱ በመሰረቱ የተለያዩ ጥምቀቶች ናቸው።

በመጨረሻም ፊልጶስ በውሃ ያጠምቀውን የኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ታሪክ አይተን እናብቃ።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 8
36 በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም። እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው? አለው።
37 ፊልጶስም። በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ።
38 ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም

እዚህም ላይ እንደምናየው፤ ጃንደረበው በኢየሱስ ካመነ በኋላ የመጀመሪያ ነገር ያደረገው በውሃ መጠመቅ ነው።

በተመሳሳይም በበዓለ ሃምሳ ቀን ላይ በጴጥሮስ ስብከት ልባቸው ለተነካውና ምን እናድርግ ብለው ለጠየቁት ሶስት ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ጴጥሮስ የነገራቸው ነገር ተመሳሳይ ነው። "በኢየሱስ ስም ተጠመቁ ከዚያም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ትቀበላላችሁ" ነው ያላቸው።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 2
38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁየመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ
...
41 ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤

እንግዲህ በሃዋርያት ስራ ላይ በግልጽ የተጻፉ ይሄ ሁሉ ስለ ውሃ ጥምቀት የሚመሰክሩ ክፍሎች ካሉ፤ በአዲስ ኪዳን የውሃ ጥምቀት አያስፈልግም ወይም በመንፈስ ከተጠመቁ በውሃ መጠመቅ አያስፈልግም ወዘተ የሚሉት አባባሎችና አመለከካተቾ መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት እንደሌላቸው ግልጽ ነው። የበለጠ ስለ ውሃ ጥምቀት ሮሜ 6 ከቁጥር 1 ጀምሮ ማንበብ ይቻላል። ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር መተባበር ነውና በአዲስ ኪዳን የውሃም ይሁን የመንፈስ ጥምቀት ሁለቱም ያስፈልጋሉ።
May 25, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...